Get Mystery Box with random crypto!

' ተፈጥሮ ባንቺ በኩል ትዋባለች. . ፊትሽን የመለስሽላቸው ነፍሶች ይለመልማሉ. . .በፈገግታሽ | ትዝታዊ🐣

" ተፈጥሮ ባንቺ በኩል ትዋባለች. .
ፊትሽን የመለስሽላቸው ነፍሶች
ይለመልማሉ. . .በፈገግታሽ ከሃዘን
ቁር ይላቀቃሉ . . .ከገፅሽ ብርሃን
ይፈልቃል. . .ከትንፋሽሽ ጋር
ሰላም ይነሰነሳል . . . የህይወት
ጠዋቴ ነሽ ዘውትር ምትነጊልኝ. . .
የምነፃብሽ ንሰሃዬ. . .የነፍሴን
እውነት የምኖርብሽ. . . የማፈቅርሽ "

/ዘካርያስ/

. . .

". . . የውቂያኖስ ውሃ በሙቀት እየተነነ
ነው ፣ በጨረቃ ፉጨት ፀሃይ አንቀላፍታለች
ከዋክብት ይተነፍሳሉ ፣ በዝች ቅዱስ
ውበት በወረራት ምሽት ልቤ ካንተ ልብ
ተንተርሳ እውነቷን ትሰማለች . .
ኦ . . . እንዴት ያለህ ፍቅር ነህ ?!. . . "

/ትዝታ/

| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ