Get Mystery Box with random crypto!

'አባ...አንድ ነገር ልነግርህ ነበር' 'ምን' ከሚቀጠቅጡት ጫማ አይናቸውን ሳያነሱ... አቤኔዘ | ትዝታዊ🐣

"አባ...አንድ ነገር ልነግርህ ነበር"

"ምን" ከሚቀጠቅጡት ጫማ አይናቸውን ሳያነሱ...

አቤኔዘር ዝምታው ውስጥ ጨለመ

ደጀኔ የአቤኔዘር አባት ዝምታው እንደ ጥልቅ ጉርጓድ አስደንግጧቸው ወደ ልጃቸው ሲዞሩ የአቤኔዘር በድን ሲባጎ ላይ ተንጠልጥሉ "አባ" አላቸው...

ይህን አይተው ከቅዠታቸው ባነኑ... ትንፋሻቸው ይቆራረጣል... አንገታቸው ስር ላብ አጥሞቋቸዋል... አይናቸው እንባ ሞላ... በዝግታ ከደኑት ... ትኩስ የእንባ እንክብሎች በዝምታ ረገፉ... ሲረጋጉ የባለቤታቸው ሲቃ ተሰማቸው...

"ተዋቡ?” አሉ ድምፃቸውን ገታ አድርገው።
ተዋቡ የታፈነ ለቅሶዋቸውን ለቀቁት... ሰውነታቸው እየተርገፈገፈ አለቀሱ ... ባለቤታቸው ደጀኔ ልባቸው ራደ... ክንዳቸውን ዘርግተው ተዋቡን ከለሏቸው ... የተዋቡ የንባ ጎርፍ ከደጀኔ ደረት ሸለቆ ውስጥ ሰጠሙ... ተዋቡ የባለቤታቸውንም ጨምረው አነቡ።


/ዘካሪያስ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ