Get Mystery Box with random crypto!

#* *#1 ያለፉ ፈገግታዎች . . . /እኔን ብሎ ርዕስ ሰጪ / የማር ጠብታ ምታክል ሩ | ትዝታዊ🐣

#*
*#1 ያለፉ ፈገግታዎች . . . /እኔን ብሎ ርዕስ ሰጪ /


የማር ጠብታ ምታክል ሩቢ ወደኔ ድክ ድክ ትላለች. , አቀፍኳት . . . እሩቅ አልመስልህ አለችኝ
ማውቀው አይን. . . በዘመኔ እርቀት የማይጨልምብኝ ፍክት ያለ ገፅ . . .

ትንንጥ ጣቶቿን በየተራ ሳምኳቸው . . .

"ማነው ሽምሽ. . ."

አይኗቿ ተንከራተቱ . . . ስሟ በዝቶባት ነው ብዬ ገመትኩ . . .. የቱን እንደምትነግረኝ ግራ ገብቷት መሰለኝ . . .ወይ አታውቀውም . .. . . ፈተናዋ የሷን አለማወቋ ብቻ አይደለም የአባቷንም ነው ብዬ አሁንም ገመትኩ . . .

"እናትሽ የታለች . . ."

ፈለገቻት . .. አልታየቻትም


አሰብኩ. . . የቱ ነው ከባዱ የህይወት ምዕራፏ.. . አሁኗ ወይስ በኋላዋ ?


ትናንሽ ነፍሶች ምርጫ የላቸውም. . . ከዝናቡ መርከፍከፍ በሱም መራስ ወይስ ሙቅ ፍራሽ ተብለው አልመረጡም ወላጅ ሳይፈጥራቸው በፊት የመረጠውን ለመኖር ይገደዳሉ . . .

እምቡጥ የወይን ፍሬ የመሰለ እግሯ ጫማ የለውም ከመሬቱ እርጥበት ጋር ተስማምተዋል ፣ ለመክዳት ጥቂት ሰበበ የሚፈልጉ ጨርቆች እዛም እዚህ አካላቷ ላይ ተበታትነዋል ፣ ከእግዜር ካፍያ በስተቀር በሰው እጆች ያልታጠበ ፀጉሯ በግንቦት ፀሃይ እንደተኮማተሩ ቅጠሎች ደክሞዋል. . .፣ ከሚያውቁት ደረቅ ጡት ጋር የታገሉ ከንፈሮቿ ብሶተኛ የጨለማ አበቦች ይመስላሉ፤
ሆዷ በእንቁልልጭ መመገብ ለምዷልና ላለማልቀስ እንደሚቀምስ ያስታውቃል. . .

ብዙ

ብዙ

ብዙ

የማታውቃቸው ስቃዬች አሏት ምን አልባት ለነገ ያሴሩባት. . . .

ከዝች ትንጥዬ ነፍስ ውስጥ የሚነፍሰው ብቸኛ ነገር ፍልቅልቅ ልጅነት ብቻ ነው . . ያልገባትን የምትኖር የበርሃ አደይ . . . የበርሃ ምንጭ . ..

'
'
"ኑኑ . . . "

ወደጠራት ድምፅ ከመሄዷ በፊት እጇን ዘረጋችልኝ . . .

"ባቦ. . " አለችኝ ጆሮን ሰርስሮ ልብን በሚያቃጥል ጥንጥዬ አንደበት

የጠራትን ማንነት ለማየት ዙርያዬን ቃኘው ለሷ ብር መስጠት ጨዋነት አልመስልክ ብሎኝ. . ርሃብ ግዴታው በሆነ የሰው ዘር ፊት ጨዋነት ሚለውን እቃቃ ለመጫወት ያፈረ አእምሮ አልነበረኝም /ምን አልባትም ጭራሱኑ የለኝም /

ኪሴ ውስጥ የነበሩትን ገንዘቦች ጥቅልል አረኩና

"ይኼን ለማማ ብቻ ስጭያት እሺ"

"እሲ ናልያም ትስት" ብላኝ ከእቅፌ ብን ብላ በረረች. . ..

ለሽርፍራፊ የደቂቃ ግማሾች ከቦታው ላይ ተከዝኩ. . መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ወደፊት ሳዘው ወደኋላ የቀረ እኔ ነበረ. . . ተመለስ ሚለኝ
"ኑኑ" የሚል ሙቅ ድምፅ . . በተስፋ መቁረጥ የምትጣራ ለስላሳ እናት . . . . . የት ይሁን ይኼን ድምፅ ማውቀው . . . ? የት ቦታ ? መኪናዬ ወደፊት እኔ ወደኃላ . . ...

/ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
@tiztawe
@tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ