Get Mystery Box with random crypto!

አርምሞ🧘🏽‍♂️Official ️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ rasnflega — አርምሞ🧘🏽‍♂️Official ️ ️️
የቴሌግራም ቻናል አርማ rasnflega — አርምሞ🧘🏽‍♂️Official ️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @rasnflega
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.55K
የሰርጥ መግለጫ

ጥቂት ምናኔ 🧘🏽‍♂️

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 22:09:21
አ ዳ ም ረ ታ

@rasnflega
147 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], edited  19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:00:29
"ቅ ሬ ታ ዎ ች ለ ሰ ይ ጣ ን ጸ ሎ ት ነ ው።"

B o b M a r l e y

በ ም ስ ጋ ና ኑ ሩ

@rasnflega
241 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:35:44 መ ል ካ ም  እ ለ ተ  ሰ ን በ ት   አ ዲ ስ   ት ን ፋ ሽ
152 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:00:51
282 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:00:51 ደስታ በግድ ማንቁርቱን ይዘህ የምታመጣው አውራ ዶሮ አይደለም። ደስተኛ ለመሆን ጥረት የሚያሳዩ ሰዎች ጥንቸል ላይ የከባድ መኪና ጡሩንባ እያንባረቁ ጥንቸሏ ከእቅፋቸው እንድትገባ የሚናፍቁ ናቸው።

ይህን የሚሉት ተመራማሪዎች ደስተኝነት እየራቃቸው የሚሄዱ ሰዎች ደስተኝነትን አብዝተው የሚያስቡቱ ናቸው ሲሉም ደምድመዋል።

የደስታን ጅራት የጨበጠ እጁን ያውጣ

ለብዙዎች ደስታ የምርጫ ጉዳይ ነው። በእነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ ደስተኛነት የጥረት ፍሬ ናት። ደስተኛ ለመሆን የፈለገ ልክ በፈተና እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚታትር ተማሪ ቀን ተሌት መልፋት መድከም አለበት።

ጎበዟ ደራሲ ኤልዛቤት ጊልበርት ከዓመታት በፊት ዓለምን አነጋግሮ በነበረውና "Eat, Pray, Love" በተሰኘው የአንድ ወቅት መጽሐፏ ይህን ብላ ነበር፦

"ደስታ የጥረት ውጤት ነው። ትታገላለህ፣ ትሟሟታለህ፣ አንዳንዴም ተነስተህ ፍለጋ ትወጣለህ፤ አገር፣ አህጉር፣ ባሕር ታቋርጣለህ። በረከትህን ለመቀበል ቁጭ ብለህ አይሆንም፤ መቃረም አለብህ። ልክ የደስታን ጅራት ስትጨብጠው እንዳልትለቀው ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርብሃል። በሐሴት የተነጠፈ የዋና ውሀ ላይ ለመንሳፈፍ የምትችለውን ሁሉ ማድረግ አለብህ፤ አለበለዚያ ትሰጥማለህ።"

እንዲህ ዓይነቱን "ደስታን በባትሪ ፈልጋት" የሚለው ምክር የብዙዎች ቢሆንም አዳዲስ ጥናቶች ግን "ኧረ በፍጹም" ይላሉ። "ፍለጋ ከወጣህ ባዶ እጅህን ትገባለህ፤ እመኑን ደስታ በፍለጋ አትገኝም" ይላሉ።

ከዚያም አልፈው ደስታ ፍለጋ የወጡ ሰዎች ለጭንቀት፣ ለብቸኝነት፣ ለድብታ እና ለውድቀት ነው የሚዳረጉት ብለዋል።

ይህ ጥናት እግረ መንገዱን በየአውዳመቱ ድብታ ውስጥ ስለሚገቡ ሰዎች አዲስ ፍንጭም ሰጥቷል።

በገና፣ በአዲስ ዓመት፣ በኢድ አንዳንዴም በገዛ የልደት ቀናቸው ከባድ የድብርት ቅርቃር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ደስታን ካልጨበጥናት ሞተን እንገኛለን ስለሚሉ ነው። ደስታን በትግል፤ ቀን ጠብቀው ሊያገኟት...

"ደስተኛ ሁን!" የሚሉ ብሽቅ መጻሕፍት

በካሊፎርኒያ ባርክሌይ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆነችው አይሪስ ማውስ ስለ ደስታና ደስተኝነት ስታጠና እግረ መንገዷን አነቃቂ መጻሕፍትን ታዝባቸዋለች።

ባለፉት ሁለት አሥርታት በአሜሪካ እነዚህ የንሸጣ መጻሕፍት አገሩን አጥለቅልቀውት ነበር። እነዚህ መጻሕፍት አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ስለደስታ ያላቸው ምልከታ ነው። በሕይወት ለመቆየት ደስታን መጎናጸፍ የግድ ነው ይላሉ።

ሁሉንም ስትገልጣቸው "ደስተኛ ካልሆንክማ ለምን ትኖራለህ? እንዴትም ብለህ እራስህን ደስተኛ ማድረግ አለብህ እንጂ" እያሉ አንድ ሁለት ሲሉ አቋራጭ መንገዶችን ይዘረዝራሉ።

በዚህ የተነሳ ጤነኛ ሰው በሰላም እየኖረ ሳለ ልክ እነዚህን መጻሕፍት ሲያነብ 'አሃ! ለካ ሁልጊዜ ደስተኛ መሆን አለብኝ...' ሲል ማሰብ ይጀምራል። እንደውም አሁን ደስተኛ አይደለሁም "በጣም ደስተኛ መሆን ነው ያለብኝ..." ሲል ከራሱ ጋር አዲስ የቅራኔ ውል ይፈራረማል።

ተመራማሪዋ አይሪስ እንደምትለው አንድ ሰው ራሱን "ምን ያህል ደስተኛ ነኝ ግን?" ብሎ የጠየቀ 'ለታ ከደስታ ጋር ፍቺ ፈጽሟል።

ማነው ታዲያ ደስተኛ?

ይህ የነ አይሪስ ጥናት ብዙ ክፍሎች ነበሩት።

ከመሪር ሃዘን በቅርብ የወጡ ሰዎችን ጭምር አካቶ ይዟል። ፊልም እንዲመለከቱ የተደረጉም ነበሩ። ደስተኛ ስለመሆን የሚያወሱ መጻሕፍትን አንብበው የጨረሱ ሰዎችም ዋንኛ የጥናቱ አካል ተደርገዋል።

በሚገርም ሁኔታ ሌሎች ይዘት ያላቸውን ጽሑፎች ካነበቡት በተለየ አነቃቂ መጻሕፍትን ያነበቡት "ደስተኛማ መሆን አለብኝ" በሚል አዲስ መብሰልሰል ውስጥ ገብተው ተገኝተዋል።

እነዚህ ሰዎች መጻሕፍቱን ካገባደዱ በኋላ ስለ ደስታ የነበራቸው ስሜት በመናሩ ያሉበትን ሁኔታና ሕይወታቸውን መንቀፍ ነበር የያዙት።

ይህ ተመሳሳይ ስሜትና ከፍተኛ ደስታን መሻት ሙሽሮች ላይም ተስተውሏል። ለሰርጋቸው ከፍ ያለ ቦታን በመስጠታቸው፤ በሰርጋቸው ማግስት በደስታ ባሕር እንደሚቀዝፉ በማመናቸው ለበለጠ ድብርት ተዳርገው ተገኝተዋል።

ይህ ስሜት ብዙ ሰዎች ያጋጥማቸዋል፤ ውድ የሽርሽር ቦታ አቅደው የሄዱ ሰዎች በማግስቱ ባዶነት ይሰማቸዋል። ነገር ግን በድንገት ወይም ባልተጠበቀና ባልታቀደ ሁኔታ አንድ ቦታ ብትሄዱ ላቅ ያለ ደስታን ልታገኙ ይቻላችኋል።

የባርክሌይ ዩኒቨርስቲ ጥናት ታዲያ "ይህ የሚነግረን ደስታ በቁፋሮ እንደማትገኝ ነው" ይላል።

ለምን ከተባለ ደስታን ስለማግኘት ቀን ተሌት መጣር ስሜታችንን በአላስፈላጊ ደረጃ ማዳመጥን ያስከትልብናል። ስለራሳችን አብዝተን እንድንጠበብ ያደርገናል። አካባቢያችንን ይጋርድብናል። ተፈጥሮን መገንዘብና ማድነቅ እናቆማለን። ሳር ቅጠሉ ሁሉ ስለኛ መሆን እንዳለበት ያሳስበናል።

ሌላው ተመራማሪ ማግሊዮ ከካናዳ አንድ ተጨማሪ ነጥብ አንስቷል።

ፌስቡክን የመሰሉ የማኅበራዊ ትስስር ድረገጾች ላይ የተጠመዱ ሰዎች ደስተኝነታቸው የሚያሽቆለቁለው የሚያዩት ነገር ስለራሳቸው ስለሚነግራቸው ነው። እኔ እንደ እከሌ ደስተኛ መሆን አለብኝ እያሉ ለማሰብ ይገደዳሉ።

ጥናቱ ረዥም ነው። የጥናቱን ውጤት ግን እንዲህ ብሎ መደምደም ይቻላል።

ደስታን ማሳደድ ማለት ያለበረቱ የተገኘ ቀንዳም በሬን እንደማሳደድ ነው።

@rasnflega
328 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:55:39 ሰዎች ቢያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህን ስትሆን አትስራው።
"

-ረሱል ﷺ"

@rasnflega
274 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:53:23 . . . ሰ ው   ያ ለ ው ን   ነው  የ ሚ ሰ ጠ ው . . .

ለራሳቸው ፍቅር መስጠት የተሳናቸው ሰዎች ሌሎችን በመጉዳት ይታወቃሉ፤ እነዚህ ሰዎች በውጭው አለም psychopath የሚል የበሽታ ስያሜ ተሰ'ቷቸው ይኖራሉ፤ ይህም ማለት እብድ ሆነው ሌሎችን በመጉዳት ወንጀል የሚሰሩ ግለቦች ማለት ነው።

"ራስህን በትክክል የምትወድ ከሆነ ሌላን የምትጎዳ አይነት ሰው አትሆንም "

ይህ የ gutema_buddha አባባል መሰረቱ የሚያደርገው ለራስህን የምትሰጠው የስሜትና የቃል መልዕክት ነው ወደሌሎች ሰዎች የምታንጸባርቀው።

ስለዚህ አንድ ቀላል የምትረዳው ነገር ሌሎችን በመጉዳት የሚታወቁ ሰዎች ልናዝንላቸው የተገባ መሆኑ ነው።

@rasnflega
283 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:02:57 ው ዳ ሴ ከ ን ቱ አ ይ ደ ለ ም ሰ ው በ 'መሆን' ህ አ መ ስ ግ ን! ምን አ ል ባ ት ትኋን ሆ ነ ት ፈ ጠ ር ነ በ ር
281 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], edited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:51:01
['ያለተሳትፎ ንቁ መሆን'] ፬

s ɪ ʟ ɴ ᴄ ᴇ

እኔ ፀጥታ ይምለው ግን ሙሉ በሙሉ በዓይነቱ የተለየ ነው። ሁከትን ወደሌላ ነገር ማዞር አይደለም፤ አዕምሮን በግድ በሆነ ነገር እንዲጠመድ ማድረግ አይደለም። የማንትራ ማደንዘዣም አይደለም። ይህ እናንተ ያለተሳትፎ ንቁ ስትሆኑ የሚከሰትላችሁ ፀጥታ ነው፤ ምንም ነገር ሳትሰሩ፤ መቁጠሪያችሁን ሳታንቀሳቅሱ ሙሉ ለሙሉ የማትሳተፉና ንቁ ስትሆኑ የሚከሰትላችሁ ፀ ጥ ታ።

አስታውሱ! ምክንያቱም አለመሳተፍ እንቅልፍ ሊሆን ይችላል። 'ንቁነት' የሚለው ቃል ላይ ያተኮርኩትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ያለተሳትፎ ስትሆኑ እንቅልፍ ውስጥ ልትገቡ ትችላላችሁ። እንቅልፍ ደግሞ ተመስጦ አይደለም፤ ነገር ግን ከእንቅልፍ የተወሰደ አንድ ጥሩ ነገር አለ፤ አንዲት ጥሩ ነገር ያም ተሳታፊ አለመሆን ነው። አንድ ከንቃት የተወሰደ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ያም ደግሞ ንቁ መሆን ነው፤ እንደተኛ ሰው ዘና ብላችሁ እንዳልተኛ ሰው ደግሞ ንቁ ትሆናላችሁ።

ካለማንቀላፋት ንቁነትን ፥ ከእንቅልፍ ደግሞ አለመሳተፍን እናገኛለን፤ እነዚህ ሁለቱ ተመስጦን ያመጣሉ። ነገር ግን በተገላቢጦሽ ከእንቅልፍ ንቁ አለመሆን ያለእንቅልፍ ደግሞ በነገሮች መጠመድን ከወሰዳችሁ እብድ ትሆናላችሁ፤ ያንንም ነው ምታደርጉት።


ተሳታፊ አለመሆንና ንቁነት ተመስጦአዊ ያደርጋሉ፤ ቡድሃ² ያደርጋሉ። ያኔ opened ክፍት ትሆናላችሁ፤ ክፍት በሆናችሁም ጊዜ ፍጹም ደስተኛ የምትሆኑት በውስጣችሁ የሚንሰራፋው ፀጥታ በእናንተ ተግባር የሚመጣ አይደለም። ይህ ክስተት ነው ፡ በራሱ ጊዜ ወደ እናንተ የሚመጣ መለኮት።

አ በ ቃ


፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

²ቡድሃ፦የበራለት

@rasnflega
375 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 13:29:01 ['ያለተሳትፎ ንቁ መሆን' ] ፫








ብዙ ሰዎች ወደኔ በመምጣት ይህን ይናገራሉ"ማንትራ እየሰራን ነው፤ መጀመርያ ላይ ይረዳን ነበር፤ አሁን ግን ምንም እያገኘንበት አይደለም፤ ምንም ነገር አይሰማንም፤ አሰልቺ ስራ ሆኖብናል አሁን የምንሰራው እንደ ግዴታ ነው፤ ፍቅራችን ጠፍቷል ካልሰራነው አንድ ነገር እንዳጣን ይሰማናል፤ ስንሰራው ደግሞ ምንም ነገር አናገኝበትም።" ይሉኛል።

ሱስ ማለትም ያ ነው። ስትፈጽሙት ምንም አታገኙበትም፤ ሳትፈጽሙት ስትቀሩ ደግሞ አንድ ነገር እንዳጣችሁ ይሰማችኋል።አንድ ሲጋራ አጫሽ የሚሰማው ይህ ነው። ሲያጨስ ምንም ጥቅም እንደማያገኝ ያውቀዋል። አንድ የጅል ፥ የደደብ ስራ እየሰራ ነው፤ ጭስ ወደውስጥ ማስገባትና ማስወጣት። ያ ራሱ ግን ልክ እንደመቁጠሪያ ነው፤ ጭሱን ወደ ውስጥ ታስገባላችሁ ከዚያም ታስወጣላችሁ ፣ ማስገባት ፥ ማስወጣት መቁጠሪያ ይሆናል። ዶቃዎችን መቀያየራችሁን ትቀጥላላችሁ፤ ' 'ማንትራ' ማድረግ።

ማንኛውም ያለማቋረጥ ልትደጋግሙት የምትችሉት ነገር ማንትራ ይሆናል። ማንትራ ማለት የአንድ ቃል ወይም ድምፅ ወይም ማንኛውም ነገር ድግግሞሽ ማለት ነው። ማንትራ አይምሮአችን በአንድ ነገር እንዲጠመድ ይረዳል፤ ማንትራ አሻንጉሊት ነው ረብሻው ስለሚቆም ለጥቂት ደቂቃ ጥሩ ስሜት ይሰማችኋል። በሆነ ነገር ስለተጠመዳችሁ አዕምሮአችሁ ስራውን ሊያቆም ይችላል፤ ይህ በግድ የሚፈጠር ፀጥታ ነው!። የጤና ስላልሆነ ጥሩ አይደለም፤ አሉታዊ እንጂ አዎንታዊ አይደለም። ይህ ፀጥታ በመቃብር ቦታ እንዳለ ፀጥታ ነው፤ የሞት ፀጥታ።




@rasnflega
344 viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], edited  10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ