Get Mystery Box with random crypto!

['ያለተሳትፎ ንቁ መሆን'] ፬ s ɪ ʟ ɴ ᴄ ᴇ እኔ ፀጥታ ይምለው ግን ሙሉ በሙሉ በዓይነቱ | አርምሞ🧘🏽‍♂️Official ️ ️️

['ያለተሳትፎ ንቁ መሆን'] ፬

s ɪ ʟ ɴ ᴄ ᴇ

እኔ ፀጥታ ይምለው ግን ሙሉ በሙሉ በዓይነቱ የተለየ ነው። ሁከትን ወደሌላ ነገር ማዞር አይደለም፤ አዕምሮን በግድ በሆነ ነገር እንዲጠመድ ማድረግ አይደለም። የማንትራ ማደንዘዣም አይደለም። ይህ እናንተ ያለተሳትፎ ንቁ ስትሆኑ የሚከሰትላችሁ ፀጥታ ነው፤ ምንም ነገር ሳትሰሩ፤ መቁጠሪያችሁን ሳታንቀሳቅሱ ሙሉ ለሙሉ የማትሳተፉና ንቁ ስትሆኑ የሚከሰትላችሁ ፀ ጥ ታ።

አስታውሱ! ምክንያቱም አለመሳተፍ እንቅልፍ ሊሆን ይችላል። 'ንቁነት' የሚለው ቃል ላይ ያተኮርኩትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ያለተሳትፎ ስትሆኑ እንቅልፍ ውስጥ ልትገቡ ትችላላችሁ። እንቅልፍ ደግሞ ተመስጦ አይደለም፤ ነገር ግን ከእንቅልፍ የተወሰደ አንድ ጥሩ ነገር አለ፤ አንዲት ጥሩ ነገር ያም ተሳታፊ አለመሆን ነው። አንድ ከንቃት የተወሰደ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ያም ደግሞ ንቁ መሆን ነው፤ እንደተኛ ሰው ዘና ብላችሁ እንዳልተኛ ሰው ደግሞ ንቁ ትሆናላችሁ።

ካለማንቀላፋት ንቁነትን ፥ ከእንቅልፍ ደግሞ አለመሳተፍን እናገኛለን፤ እነዚህ ሁለቱ ተመስጦን ያመጣሉ። ነገር ግን በተገላቢጦሽ ከእንቅልፍ ንቁ አለመሆን ያለእንቅልፍ ደግሞ በነገሮች መጠመድን ከወሰዳችሁ እብድ ትሆናላችሁ፤ ያንንም ነው ምታደርጉት።


ተሳታፊ አለመሆንና ንቁነት ተመስጦአዊ ያደርጋሉ፤ ቡድሃ² ያደርጋሉ። ያኔ opened ክፍት ትሆናላችሁ፤ ክፍት በሆናችሁም ጊዜ ፍጹም ደስተኛ የምትሆኑት በውስጣችሁ የሚንሰራፋው ፀጥታ በእናንተ ተግባር የሚመጣ አይደለም። ይህ ክስተት ነው ፡ በራሱ ጊዜ ወደ እናንተ የሚመጣ መለኮት።

አ በ ቃ


፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

²ቡድሃ፦የበራለት

@rasnflega