Get Mystery Box with random crypto!

['ያለተሳትፎ ንቁ መሆን' ] ፫ ፀ ጥ ታ ብዙ ሰዎች ወደኔ በመምጣት ይህን ይናገራሉ'ማን | አርምሞ🧘🏽‍♂️Official ️ ️️

['ያለተሳትፎ ንቁ መሆን' ] ፫








ብዙ ሰዎች ወደኔ በመምጣት ይህን ይናገራሉ"ማንትራ እየሰራን ነው፤ መጀመርያ ላይ ይረዳን ነበር፤ አሁን ግን ምንም እያገኘንበት አይደለም፤ ምንም ነገር አይሰማንም፤ አሰልቺ ስራ ሆኖብናል አሁን የምንሰራው እንደ ግዴታ ነው፤ ፍቅራችን ጠፍቷል ካልሰራነው አንድ ነገር እንዳጣን ይሰማናል፤ ስንሰራው ደግሞ ምንም ነገር አናገኝበትም።" ይሉኛል።

ሱስ ማለትም ያ ነው። ስትፈጽሙት ምንም አታገኙበትም፤ ሳትፈጽሙት ስትቀሩ ደግሞ አንድ ነገር እንዳጣችሁ ይሰማችኋል።አንድ ሲጋራ አጫሽ የሚሰማው ይህ ነው። ሲያጨስ ምንም ጥቅም እንደማያገኝ ያውቀዋል። አንድ የጅል ፥ የደደብ ስራ እየሰራ ነው፤ ጭስ ወደውስጥ ማስገባትና ማስወጣት። ያ ራሱ ግን ልክ እንደመቁጠሪያ ነው፤ ጭሱን ወደ ውስጥ ታስገባላችሁ ከዚያም ታስወጣላችሁ ፣ ማስገባት ፥ ማስወጣት መቁጠሪያ ይሆናል። ዶቃዎችን መቀያየራችሁን ትቀጥላላችሁ፤ ' 'ማንትራ' ማድረግ።

ማንኛውም ያለማቋረጥ ልትደጋግሙት የምትችሉት ነገር ማንትራ ይሆናል። ማንትራ ማለት የአንድ ቃል ወይም ድምፅ ወይም ማንኛውም ነገር ድግግሞሽ ማለት ነው። ማንትራ አይምሮአችን በአንድ ነገር እንዲጠመድ ይረዳል፤ ማንትራ አሻንጉሊት ነው ረብሻው ስለሚቆም ለጥቂት ደቂቃ ጥሩ ስሜት ይሰማችኋል። በሆነ ነገር ስለተጠመዳችሁ አዕምሮአችሁ ስራውን ሊያቆም ይችላል፤ ይህ በግድ የሚፈጠር ፀጥታ ነው!። የጤና ስላልሆነ ጥሩ አይደለም፤ አሉታዊ እንጂ አዎንታዊ አይደለም። ይህ ፀጥታ በመቃብር ቦታ እንዳለ ፀጥታ ነው፤ የሞት ፀጥታ።




@rasnflega