2022-07-26 12:45:33
<< አ በ ባ አ ይ ተ ሽ ታ ው ቂ ያ ለ ሽ >> ²
U getting flowers but no can't getting hearts ምንአልባት በደመቁ ነገሮች መደብዘዛችን መሸፈን እንወዳለን፤ ከውድ ልብሶቼ አንዱን ለበስኹ አንገቴን ቀና በማረግ ከአደባባይ ቆምኩኝ ፈገግታዬም የሰዎች እንባ ነበር . . . አለሜ መሆኑ ነው ውድ ሳልሆን ውዴን መፈለጌ. . . ወደኔ መጣች አንዲት እርጥብ ፅጌ. . . ከዓይኗ ዓይኔን ከከንፈሯ ከንፈሬን ከልቧ ግን ውብ ቃሌን አስለመድኳት።
" ከእኔ አትራቂ ከአንገትሽ እሰሪኝ ከልብሽም ጽላት ጻፊኝ" እሳቱን ዘነጋች ነበልባል ቃሌን አመነች።
ይህ'ቺ ሴት ለቅጽበት ከልቤ ኖረች። የማታቀውን ሁሉ አወቀች። ለእኔ የቅጽበት ህይወት ለርሷ ግን ዘላለማዊነት። አንድ'ለት ተመለከትኳት ከሰጠዋት አበባ ቀድማ ከስማ ነበረ፤ እያየዋት መዳፌ ላይ ልጅነቷ ጠቁሮ ለመኖር ጣረ ፤
ልቤም እኔን ጠየቀኝ ''ከእንግዲ ከ'ርሷ ምን ቀረ . . . ¿''
ሰውነቴ ለጋ አምሮት ካልተነካች ሴት ጭን ስር ነው። ከስጋ ደግሞም ከአፍ መቅደሴን አፍርሻለው፤ እኔ ድንግል ባልሆንም ከድንግል አድርያለው።
. . .
ምንአልባት በደመቁ ነገሮች መደብዘዜን መሸፈን እወዳለው. . . yes 𝔦'𝔪 romantic! what did you except, I read classic literature for fun. ምንም ማረግ አይቻልም ያ'ንተ ገነት ቢጨልም በሌሎች ውስጥ በርቶ ታገኘዋለህ።
@poems_essay
1.1K viewsሞገስ ዘአምድ [Guru], 09:45