Get Mystery Box with random crypto!

ኖኅ Book Delivery

የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የሰርጥ አድራሻ: @noahbookdelivery
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.84K
የሰርጥ መግለጫ

The first and the only book delivery service in Ethiopia. Order books all over the world with fair price & fast delivery
Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-12 14:43:52
ኬቨን ሃርት የተባለው ኮሜዲያን። እዚህ የስኬት ጫፍ ላይ ከመድረሱ በፊት ብዙ መከራ ያሳለፈና አትችልም ተብሎ የተገፋ ሰው ሲሆን፣ ከሲንግል እናቱ ቤት ሥራ ፍለጋ ሲወጣ እናቱ የሰጡት ስጦታ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር። ኬቨን አንድ ቀን የሚመገበው አጥቶ በጣም ቸግሮት ለእናቱ ይደውላል፣ ማሚ ስራ ማግኘት አልቻልኩም እባክሽ እርጂኝ አላቸው? እናቱም የሰጠሁህን መጽሐፍ ቅዱስ አንበብክ ወይ ? እርሱም ራበኝ እያልኩሽ የምን መጻሕፍ ነው የምትይው አላቸው። ልጄ አሉት የሰጠሁህን መጻሕፍ ቅዱስን አንብበህ ቢሆን ኖሮ እኮ አይርብህም ነበር አሉት።

ኬቨን እናቱ አንብብ ያሉትን መጻሕፍ ቅዱስ ሳያነብ እናቱ በማኅፀን በር ካንሰር ያርፋሉ፣ እርሱም በዓለም ምርጡ ኮሜዲያን ውዱ አከተርም ከሆነ በኃላ፣ አንድ ቀን የልጅነት ፎቶግራፎቹን ለፊልም ፈልጎ ሲበረብር ያንን እናቱ የሰጡትን መጻሕፍ ቅዱስንም ገለጠው፣ ውስጡ እናቱ ለስራ መፈለጊያና መጠነኛ ቤት መከራያ እንዲሆነው የተውለትን 1ሺ ዶላር አገኘ። ገንዘቡ ለአሁኑ ኬቨን ምንም ብትሆንም እናቱ ግን ንብረታቸውን ሸጠው ነበር ለልጃቸው የሰጡት። መጻሕፍት ውስጥ ብዙ መልሶች አሉና መጻሕፍትን እናንብብ። ቀና ብሎ በዕውቀት ለማውራት ብዙ አጎንብሶ ማንበብን ይጠይቃል።

ፍፁም አብርሃም

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
213 viewsኖኀ መፅሐፍ, 11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 21:19:23
የአልበርት አነስታይን ድንቅ ንግግሮች
~~~~
1.“ምንም የተለየ ተሰጥኦ የለኝም። በልዩ ጥልቀት የሚንጠኝ ጉጉት ከመያዜ በስተቀር።”

2.“ከሌላው በተለየ ብልህ ኾኜ አይደለም። ግን ውስብስብ ችግሮች ሲገጥሙኝ ብዙ እቆይባቸዋለሁ።”

3.“ምናብ ሁሉም ነገር ነው። ሕይወት ይዛቸው የምትምጣቸው ማራኪ ኹነቶች ቅድመ ምልከታ ማለት ነው። ምናብ ከእውቀትም የበለጠ ኃይል አለው።”

4.‹‹ ስህተት ሠርቶ የማያውቅ ሠው ምንም ነገር ሞክሮ አያውቅም ማለት ነው፡፡ ››

5.‹‹ ሁሉም ሠው ብሩህ ጭንቅላት አለው፡፡ ነገር ግን አሣን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሣ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ››

6.“እብደት ምንድን ነው ብትሉኝ አንድን ነገር ደጋግመው እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው እላችኋለሁ።”

7.ስለወደፊቱ አላስብም። ተጣድፎ መምጣቱ መች ይቀራል!”

8.“በመጀመርያ የጨዋታውን ህግጋት መማር አለብህ። ከዚያ ድግሞ ከማንም በተሻለ መጫወትን ልመድ።”

9.‹‹ ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡ ››

10.‹‹ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር፡፡ ››

(Menur Yassin እንዳጋራው)

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
816 viewsኖኀ መፅሐፍ, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 22:51:59 " የታንጕት ምስጢር "
ብርሃኑ ዘሪሁን
ይዘት፦ታሪካዊ ልብ-ወለድ
የገጽ ብዛት፦228
የኅትመት ዘመን:1958

በሀገራችን ከተፃፉ ታሪካዊ ልብወለዶች መሀከል እጅግ ተወዳጅ ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች የአማርኛ ስነፅሁፍ ማስተርፒስ ይሉታል። በሀገራችን በአፄ ቴዎድሮስ ህይወት ዙሪያ ከተፃፉት 2 ታሪካዊ ልብወለዶች ( አንድ ለናቱ & የታንጉት ምስጢር ) የተሻለ ቦታ የሚሰጠውም ይህ መፅሀፍ ነው።

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
190 viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 15:06:13 #Psychodynamics

3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ለፈተና በቂ ዝግጅት ስላላደረጉ ለመሸወድ ፈለጉ። በዚህም ምክንያት አንድ መላ ዘየዱ። ራሳቸውን ግሪስ ቀቡና ራሳቸውን በሚገባ በማቆሸሽ ከሌክቸረሩ ፊት በመቅረብ እንዲህ ሲሉ ምክንያታቸውን አቀረቡ፦

ኢንስትራክተር በጣም እናዝናለን፤ ፈተናውን ለመፈተን የማያስችል እንከን ገጥሞናል። ምክንያታቸውን አስከተሉ፦

አንድ ሰርግ ላይ ታድመን ነበር፤ እናም ከፕሮግራሙ በኋላ በመመለስ ላይ እያለን በመንገዳችን ላይ መኪናችን ብልሽት ገጠማት። የመኪናችንን ብልሽት ለመጠገን እንደምትመለከተን በአስቀያሚ ሁኔታ ቆሽሸናል።

#ሌክቸረሩም ከምክንያተቸው በመነሳት ተረዳቸውና ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለፈተና ዝግጅት 3ት ቀን ሰጣቸውና አሰናበታቸው።

ከ3ት ቀን በኋላ ለተዘጋጀላቸው ፈተና በበቂ ሁኔታ አጥንተውና ተዘጋጅተው መጡ።

ሌክቸረሩ አንድ ውሳኔ ወሰነና እንዲህ አደረገ ...

ሶስቱም ተራርቀው የተለያየ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ተማሪዎቹም በጣም ተራርቀው ተቀመጡ፤ የፈተና ወረቀትም ተሰጣቸው። ጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፦

ጥያቄ ቁጥር 1 - ማን ነበር ያገባው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 2 - የት ነበር የሠርግ ፕሮግራሙ የተካሄደው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 3 - መኪናዋ የተበላሸችበት ትክክለኛ ቦታ የት ነው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 4 - የተበላሸችው መኪና ሞዴሏ ምን አይነት ነው ? (25% ማርክ)

ከጥያቄዎቹ መጨረሻም #ማስጠንቀቂያው እንዲህ ይላል - መልሳችሁ የግድ ተመሳሳይ መሆን አለበት !!!
___
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
775 viewsኖኀ መፅሐፍ, 12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:59:37
ቡርሐን አዲስ እና ቴዎድሮስ ተ/ አረጋይ

ቴዎድሮስ፦..ከሁላችንም ነፍስ ደስታን ተነጥቀናል።ቀና ብለን አንሄድም።ምሬት መለያችን ሆኗል።ጥሩ ገቢ ያለው ነጋዴ "ስራ እንዴት"ነው?ስትለው"ምንም አይልም" ነው የሚልህ።አፋችን በረከት የለም።ምስጋና የለም።"ምንም አይልም"ምሬት ነው።ማጉተምተም ነው።እነዚህ ስሜቶች ውስደው የት ያደርሱናል? ምንድ ነው ራሳችንን የምንመክረው?

ቡርሐን፦አንባቢዎቻችን አማኝ ስለሆኑ ከየመጽሐፎቻቸው አንዳንድ ምሳሌ መጥቀስ ብንችል መልካም ነው።ከአዲስ ኪዳን በጣም የምወደው ቆንጆ ጥቅስ አለ።"አዕዋፋት ነገ ምን እንበላለን? ብለው አያስቡም።አበቦችን እዩዋቸው።ምን እንለብሳለን ብለው አያስቡም።ግን በህበረ ቀለማት አሸብርቀው፣ተውበው ታዩዋቸዋላችሁ"ይላል።ነብዩ ሙሐመድ ከተናገሩት ሌላ ጥቅስ ጋር ደግሞ ላያይዝልህ።"ሐብታም ማለት ባለው ነገር የሚብቃቃ ነው።የሰው ልጅ አንደ ሸለቆ ወርቅ ቢሰጠው ሁለተኛው ይጨመርልኝ ይላል።ሐብታም ማለት ባለው የሚብቃቃ ነው"የሚል ሐሳብ ነው።

የተባሉት ሁሌም አይሰሩም ነበር።በረው መስራት እንዳለባቸው ያውቃሉ።ይበራሉ።ዓላማህን እስከፈለከው ድረስ የሚያስፈልግህን አታጣም ነው ጭብጡ።እፅዋትም ውበታችውን በመስጠታቸው ነው የሚራቡት።አበቦች ዘራቸውን መቀጠል የሚችሉት በውበታቸው ነው።መብቃቃት ማለት ያለህንና የሚጎልህን ማሰብ ነው።አንድ ነገር ኢንዲኖረኝ ስፈልግ ለምንድን ነው እንዲኖረኝ የምፈለገው?በዋንኛነት ራሳችንን አጥተነዋል።ራስን መሆን።የራስን አለም መፍጠር፣በራስ ወሰን ልክ ማሰብ።በራስ መደሰትና ደስታ የልብ እንጂ የጭንቅላት አለመሆኑን ማመን ያስፈልጋል።የመኖርን ዋጋ ለማወቅ የምንኖርበት ምክንያት ማወቅ።ይህን ነው ዛሬ ድረስ የማስበው።
ቴዎድሮስ፦ነገስ?

ቡርሐን፦ነገ ላይ ስደርስ ነው መመለስ የምችለው።
ፍልስምና 4

Join us @noahbookdelivery
1.0K viewsኖኀ መፅሐፍ, 04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 20:08:01
መጽሐፍ ጥቆማ
" አበረታች መድኃኒት "
፪ኛ እትም
በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

ሙሉ ገቢው ለአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የልማት ኮሚቴ ለሚያሰራው ሁለገብ ሕንፃ ማሰሪያ ድጋፍ የሚውል።
መምህር ሆይ ጸጋው ያብዛልህ ዕድሜ ከጤና ይስጥልን።

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.1K viewsኖኀ book delivery, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 19:38:59 "የሰዎችን አዕምሮ የማንበብ ጥበብ"
THE CAVE OF THE ANCIENTS
ደራሲ፦ ዶ/ር ትዩስዴይ ሎብሳንግ ራምፓ
ትርጉም፦ ናሚ
የገጽ ብዛት፦160
#ሼር

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.4K viewsኖኀ መፅሐፍ, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 05:27:45
ለውብ ቀን! 
      
መምህሯ ዩሱፍ ከተባለው ተማሪ ወላጅ አባት ጋር በልጁ ጉዳይ ለመምከር ቀጠሮ ያዘች። አባት በቀጠሮው ሰዓት በትምህርት ቤቱ ተገኘ። መምህርቷም «ልጅህ በትምህርት ክፍለ ጊዜ ተማሪዎችን ያውካል። ትምህርቱን በንቃት አይከታተልም። የትኩረት መሰለብና የመቅበጥበጥ ህመም የሚስተዋልበት ስለሆነ Ritalin የተባለውን መድሃኒት የግድ መውሰድ እንዳለበት ማወቅ አለብህ» አለችው።

መምህርቷ ዩሱፍ የመምህራን ክፍል እየገባ ክኒኑን ከወሰደ በኋላ በተጨማሪም ለርሷ ቡና በማምጣት ትምህርቱን እንዲከታተል አስተያየት አቀረበች። ዩሱፍም ያቀረበችውን አስተያየት ተቀብሎ ለአንድ ወር ያህል የተባለውን ፈጸመ። መምህርቷ የዩሱፍን ወላጅ አባት
ዳግም በመጥራት «ዩሱፍ በትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚያሳየው እንቅስቃሴ ሰከን ብሏል። አስደናቂ የባህሪ ለውጥ አምጥቷል» በማለት አደነቀችው። ወላጅ አባትም የመምህርቷን አድናቆት በመስማቱ ተደሰተ። ወደ ልጁ ዘወር ብሎ በፈገግታ «ከቀድሞ በተሻለ ሁኔታ ላይ እንዳለህ ከመምህርህ መስማት እጅጉን ያስደስታል።ያሳለፍከውን የለውጥ ሂደትና የስኬትህን ሚስጥር እስኪ አጫውተኝ» አለው።

ልጁም « አባቴ ጉዳዩ እጅግ በጣም ቀላል ነው። ሁሌም ወደ መምህራኖቹ ክፍል አመራለሁ። ቡናውንም ለመምህርቷ አቀርባለሁ። ግና
እንድወስድ የታዘዝኩትን መድሂኒት መምህርቷ ከምትጠጣው ቡና ውስጥ እጨምረዋለሁ። ለዚህ ነው መምህሯ ይበልጥ የተረጋጋችና በተገቢው ሁኔታ ማስተማር የጀመረችው»
ብሎት አረፈ።

የመልዕክቱ መቅኔ :- አንዳንዴ እኛ ራሳችን ለውጥ የምንሻ ሆነን እያለ ሌሎች
እንዲለወጡ ወቀሳ ማቅረብ ፋይዳ የለውም - የሚል ነው።

             ውብ ቀን!

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.5K viewsኖኀ መፅሐፍ, 02:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 16:31:02
መጽሐፍ ጥቆማ
" ሚተራሊዮን "
በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ

ጩኸት  ከውጪ ብቻ አይደለም፡፡ ጩኸት ከውስጣችንም አለ፡፡ አንዳንዴ ምንም እንኳን አካባቢያችን ፀጥ ረጭ ሲልም ውስጣችን በጩኸት የተሞላ ከሆነ ሰላምና ጸጥታ አይሰማንም፡፡ እንዲያውም ዝም ባልን ቁጥር አካባቢው ጭር ባለቁጥር የውስጣችን ጩኸት ጎልቶ ይሰማናል፡፡ የውስጥ ጩኸታችንን ላለማዳመጥ የውጪ ጩኸት እንሻለን፡፡ እናም የሚጮህ ሙዚቃ፣ ጫጫታ፣ሁካታ የበዛበት ስፍራ መገኘት እንፈልጋለን፡፡ እኔ ዘመኔን በጩኸትና በሁካታ ነው የኖርኩት ጭር ሲል አልወድም የሚሉት ትውልድ አባል ነኝ፡፡ ሁሉ ነገር እንዲጮህ እንሻለን፡፡ ሚዲያው፣ ቴሌቪዥኑ፣ ሬዲዮው፣ ታምቡሩ ሌላው ቀርቶ ስብከቱ ሁሉ ጩኸት ሆኗል፡፡ በአካባቢያችን የሚጮኸ ብናጣ እንኳን የሚጮህ ታኮ ያለው ጫማ እናደርጋለን፡፡ ቋ….ቋ….ኳ….ኳ…. መጥቻለሁ፣ ደርሻለሁ፣ ሄጃለሁ፣ ወጥቻለሁ ይላል ጫማችን እኛን ተክቶ እየጮኸ!

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.4K viewsኖኀ መፅሐፍ, edited  13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 21:45:52
ይችን ውብ ግጥም ተጋበዙልን።

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.6K viewsኖኀ መፅሐፍ, edited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ