Get Mystery Box with random crypto!

ኖኅ Book Delivery

የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የሰርጥ አድራሻ: @noahbookdelivery
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.84K
የሰርጥ መግለጫ

The first and the only book delivery service in Ethiopia. Order books all over the world with fair price & fast delivery
Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-29 22:25:04
ቆየት ካሉ መጽሐፍ ግብዣ
" ወንጀል እና ቅጣት "
ዶስቶቭስኪ
ትርጉም፦ ካሳ ገ/ህይወት እና ፋንቱ ሳህሌ

"ማንኛውም ሰው ወንጀል ሲፈፅም መጀመሪያ የሚጎዳው ራሱን ነው። ይኸውም የራሱን ምርጥ ባህሪ ማውደሙ ነው"

በአይን የሚታይ ጥቂት ነገር ለማትረፍ በአይን የማይታየውን አለሙን ከስሩ ነቅንቆ በማፈራረሱ ነው። ወንጀል ፈፃሚው ወንጀሉ ሳይደረስበት ሊቀር ይችላል። ከራሱ ግን ተደብቆ የሚቀር አንዳች ነገር የለም። ሌሎችን ሊያሞኝ _ ይችላል፡፡ እራሱን ግን ማታለል አይችልም፡፡
ሀቀኛ ሰው ወንጀል የማይፈፅመው ሊደረስብኝ ይችላል ብሎ በመፍራት ሳይሆን ለራሱ ታማኝ በመሆን፣ ለህሊናው ተገዢ በመሆን ነው። ፖሊስና ህግን ማምለጥ ቢቻል እንኳን ህሊናን መሸንገል አይችልም።

ዶስቶቭስኪ በወንጀልና ቅጣት ውስጥ አንድ ወንጀለኛ ወንጀል ከፈፀመ በኋላ ስለሚኖረው የመንፈስ ሁኔታ አእምሮ ውስጥ ድረስ ዘልቆ በመግባት ይተርክልናል፡፡ ዶስቶቭስኪን የምታደንቀው ይኼኔ ነው፡፡ ደራሲው በምናብ የሚወስድህ ፖሊስ ጣቢያ ወይም ፍርድ ቤት አይደለም፡፡ ቀጥታ የወንጀለኛው አእምሮ ውስጥ ገብቶ የሃሳብ ፍትጊያውን፣ የህሊና መቋሰሉን፣ እረፍት ማጣትን ይነግርሃል። የመጨረሻው ረቂቅ መቼት አእምሮ ነው፡፡ ዶስቶቭስኪም የሚወስደን እዚሁ ረቂቅ ቦታ ነው።
Fyodor Dostoyevsky

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
2.0K viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 08:42:21
በጣልያን ናፖሊ ከተማ ድግሱ ተጧጧፈ ጠርሙስ ተከፈተ ብርጭቆ ሞላ መልሶ ጎደለ ሞላ ጎደለ ጩኸት በዛ።ኔፕልሶች ከ33 አመት በውሃላ የሴሪያውን ዋንጫ ማንሳታቸው ነበር። ከጣልያኗ ከተማ እብደት ጀርባ ያሳበዷት የአንድ ቤተሰብ እንባ ነበር። የማወራው ስለኳስ አይደለም።

በምስሉ ላይ የምታዩት ኦሽሜን ሲሆን ከአጠገቡ ያለችው እህቱ ነች። የቤቱ 6ተኛ እና የመጨረሻ ልጅ ነው። ጥሩ እድል ይዞ ወደቤተሰቡ አልተቀላቀለም የመጫወቻ እድሜው ሲደርስ እናቱ ሞተች በ3ኛው ወር አባቱ ከስራ ተባረረ። ኦሽሜ እና ወንድሞቹ ሰፈራቸው ውስጥ ውሃ እየዞሩ መሸጥ ጀመሩ። "መሞት የለብንም" የቤተሰባቸው መፈክር ሆነ ሊመሻሽ ሲል ኦሽሜን እግርኳስን ከእኩዮቹ ጋር ይጫወት ነበር።

ታሪኩ ሚጀምረው እዚህ ጋር ነው። ለናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን ከ17 አመት በታች ቺሊ በምታዘጋጀው ዓለም ዋንጫ ምልመላ ለመሳተፍ ተጫዋች ይመረጡ ጀመር። ኦሽሜን የትራንስፖርት ገንዘብ ስላልነበረው ወደ ዋና ከተማዋ አቡጃ በእግሩ ተጉዞ ከ9 ሰአታት በውሃላ ደረሰ።መልማዮቹ ወደዱት ቡድኑን ተቀላቀለ።ከዛች ቀን በውሃላ የህይወት መስመሩ ያማረለት ኦሽሜ ቤልጅየም ዎልፍስበርግ ቀጥሎም ጣልያን ናፖሊ አረፈ። 30 ጎሎችን አስቆጠረ ናፖሊዎችን አሳበደ።

ዛሬ ላይ ኦሽሜ ሚሊየር ብቻም ሳይሆን ጣልያኖችም ከፓስታ ሞኮሮኒያቸው እኩል ያውቁታል። በህይወት ውስጥ ከቤተሰቡ የቤተሰቡን ችግር እስከመጨረሻው የሚቀርፍ አንድ ሰው አይጠፋም። ያንተን ቤተሰብ የችግር ሰንሰለት ምትበጣጥሰው አንተ ብትሆንስ?

#ንቃንቃ_ማከክ_ይብቃ
#የሰኞአነቃቂ
ፕሮፌሰር ሄኖክ አረጋ እንደፃፈው

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
2.0K viewsኖኀ መፅሐፍ, 05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 16:11:45
አስራ አምስተኛው የአ.አ.ዩ ፕሬስ የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይ እና ሽያጭ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ግቢ ውስጥ  እየተካሄደ ይገኛል ። የአ.አ.ዩ ፕሬስን ጨምሮ አዲስና ያገለገሉ መጻሕፍትን የሚሸጡ  ከሰላሳ በላይ መጻሕፍት ነጋዴዎች በአንድ ላይ በአንድ ቦታ ይገኛሉ :: መጥተው ይጎብኙን :: መግቢያው በነጻ ነው ::

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
839 viewsኖኀ መፅሐፍ, 13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 07:46:41
እታቲዬ ጋሼ ከሞተ በኋላ አረቄ ውስጥ መሸገች።

ትንሽ ቀማምሳ እቤት ትመጣና....

"ዕድሌ" ትለኛለች

ወዬ እታቲዬ

"በጣም ጎበዝ፣ በጣም ተንከባካቢ፣ በጣም ጀግና እና ታታሪ እንዳታገቢ እሺ... ድንገት ካጣሺው ትዝታው እና እጦቱ አያራምድሽም"

እሺ እታቲዬ

"ዕድሌ ...."

አቤት እታቲዬ

"ስታገቢ ተራ ከስሙ የተለየ ጉብዝና ያላየው.... የትም የሚገኝ... የትም ያለ... ከብዙ ሰው የማይለይ.... መርሕ እና ግብ ያልታጨቀበት አግቢ እሺ.... ብታጪው እንኳን ማንነትሽ አይናድም.... እሺ ዕድሌ"

እሺ.... እሺ ....እታትዬ

አዎ! እሱ ጋር ያመኛል !

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.3K viewsኖኀ መፅሐፍ, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 07:22:54
ስብሀት ወዶ አይደለም!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ስብሀት የማይለው፣
ወይ ትርጉም አቶ ነው፣ ወይ አግኝቶለት ነው።

"ጋሽ ስብሀት ወደህ አይደለም አይደል.....?"

"አዎ ልጄ።..... ወድጄ አይደለም።"

"አስቲ ተረት አውራልኝ..?"

"ተረት..?"

"አዎ ተረት"

"እኔ ተረት አልችልም።"

"ያው ትፅፍ የለ..?"

"ተረት...?"

"አዎ ተረት"

"ተረት እኮ አይደለም"

"እና ምንድነው ..?"

"ህይወት ነው"

"ህይወት ይፃፋል እንዴ...?"

"ሁሉም አይደለም እንጂ...."

"ለምን ሁሉም አይፃፍም..?"

"ሁሉም አይገኝማ ልጄ።"

"ታድያ ጎዶሎ ህይወት አለ...?"

"ለዚህ እኮነው ተረት ያላኳት።"

"ማንን...?"

"ህይወትዋን...."

"አይ ጋሼ..."

"አይ ልጄ..."

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እንዲህ የሚፅፈው፣
ሰውን አንዳይመረው ነው፣ እሱን የመረረው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ድሀ ድሀ ያለው፣
አሄን ድህነት፣ ገልጦ ስላየው ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ጋሽ ስብሀት ባለጌ ነህ አይደል...?"

"ሰው ብቻውን አይባልግም"

ማለቴ የምትፅፈው እርቃንን ነው..?"

"ታድያኮ እሱ እውነት ነው።"

"ፅሁፍህ ሁሉ እውነት ነው ማለት ነው..?"

"አይደለም ውሸትም አለበት አንዳንዴ እኮ ሰዎችን ልብስ አለብሳቸዋለሁ።"

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እርቃንን የፃፈው፣
አዳምና ሄዋን፣ ትዝ ብለውት ነው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ወሲብ ወሲብ ያለው፣
የጉድ መፈልፈያ መሆኑ፣ ገብቶት ነው።
ደረጄ ደስታ

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.1K viewsኖኀ መፅሐፍ, 04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 14:49:27
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" ፍኖተ መድሀኒት "
በባየ አከለ

ስለመጽሐፉ ...

የሰው ልጅ የሺህ ዘመናት ጉዞን በመድሀኒት በኩል ለማሳያት ይሞክራል፡፡

ሰው ልጅ በሽታ የፈጣሪ ቁጣ ነው ብሎ ያምን ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ አሁን ላይ እንዴት የዘረ መል ህክምና እንደደረሰ ለማሳየት ይሞክራል፡፡

የፍልስፍና ጥማት ካለብዎ፣ ከቀደምት የግሪክና የሮማ እና ከአረብ ፈላስፋዎች  ጋር ያስተዋውቃል፡፡

መድሀኒት በዘመናዊ መንገድ ለማግኘት የሚያልፍባቸው ሳንይሳዊ መንገዶች በዝርዝር ያስቃኛል፤ የተመረጡ መድሀኒቶች ከየት ተነስተው የት እንደደረሱ ያመላክታል፤ የሰው ልጅ ለሳይንስ ያለውን ቁርጠንኝት ያደንቃሉ፤ይደማመሉ፡፡

መድሀኒቶች ለማግኘት ገፊ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይፈተሻሉ፡፡ ምን አይነት ማህበራዊና ኢኮኖሚ ሁነት ስለነበር ነው መድሀኒቶቹ ሊገኙ የቻለው የሚለውን ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

የፖለቲካ ጥማት ካለብዎ ሶሻሊዝም፣ ካፒታሊዝምና ዮጄኒክስ አስተሳሰብ/እንቅስቃሴ ከመድሀኒት ጋር ተላቁጠው ቀርበዋል፡፡ ከናዚ እስከ ታሊባን፣ ከከቴዎዶር ሩዝቬልት እስከ አዶልፍ ሒትለር፣ ከአዶልፍ ሒትለር እስከ ሙላህ ኡመር እና ኦሳማ ቢላደን ተቃኝተዋል፡፡

መድሀኒት በተመለከተ የሚነሱ ሀይማኖታዊ እና ፖቲካዊ ሙግቶች/ክርክሮች፣ የሞራል ተጠየቆች በሚገባ ከታሪካዊና ሳይንሳዊ ጉዳዮች ጋር ተሰናስለው ቀርበዋል፡፡

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.1K viewsኖኀ መፅሐፍ, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 06:28:19
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" መጽሐፈ መሠረት "
ዲ/ን ዶ/ር ከሣቴ ብርሃን ገ/እየሱስ

መምህር ዘበነ ለማን ጨምሮ ብዙ መምህራንን ያፈሩት የሊቁ አለቃ መሠረት ተሰማን ሥራዎች ያካተተው "መጽሐፈ መሠረት" ገበያ ላይ ውሏል።

ምን ይዟል?
-ሥነ ፍጥረትን ይተነትናል።
-አእማደ ምሥጢርን ያመሠጥራል
- ዜና ማርያምን ያስነብባል።
-ልሣነ ግእዝን ያለማምዳል
-ለብዙ አንገብጋቢ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
የሊቁንና የሌሎች ሊቃውንትን የሕይወት ታሪክ ይዟል።

ጥርት ያለ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ከምንጩ መጠጣት ለናፈቀ ይኼን መጽሐፍ ማንበብ ይገባዋል።

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.2K viewsኖኀ መፅሐፍ, 03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 07:33:29
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" አዎ! እሱ ጋር ያመኛል! "
አድኃኖም ምትኩ

<<.....ድከመቴን የማታጎላብኝ፤ መውደዷ የማይወላውል፣ እንደምወዳት ማስረጃ የማታስስ፣ ተዝረክርኬ ዝንጥ እንዳልኩ የምታሰማኝ፤ ሕመሜ የሚያማት፤ ስኬቴ ከሁሉ በላይ የሚያስፈነድቃት፣ ነገሬን ሁሉ ጉዳዬ ነው የምትል፤ እንደምወደድ እስትንፋሴ ዓለም ላይ ካረፈ ጀምሮ እያሳየች የመሰከረችልኝ።

እምወደድ እንደሆንኩ ልቤ ላይ ያሰረጸችልኝ፤ መወደድን የሚያክል ምንም በረከት እንደሌለ በምርቃት እና በጸሎቷ ያሰማችኝ።

ጥንካሬዋን ፈተና የማይበግረው፤ በደል ሆነ መከፋት የማይሽረሽረው ትሕትና የተላበሰች፣ በየቀኑ ስለልጇ ከአምላኳ ጋ የምታወራ አመስጋኝ፣ ስጉ ፍጥረት ናት።

እስክንጠግብ የማይርባት፤ አሟት በድካም የምታሳብብ፤ እየረገመችን የምትጸልይልን፣ አንደበቷ ከእውነቷ ጋ የማይገጣጠም ድብቅ ፍጡር ናት።

ፍላጎቷን አሽሻ፣ የምትፈልገውን አጣጥላ ለምንወድው ነገር ፍላጎቷን የሰዋች፣ ለልጆቿ ቸር፣ ለራሷ ስስታም ናት።

የልጇን ፊት እንደዳዊት ዘወትር የምታነብ፤ ስትናፍቅ፣ ስናረፍድ በስጋት የምትቃዥ እናት፤ የፍጡር ፍቅር ጥግ ናት....>>
                      ከመፅሃፉ የተወሰደ

     መልካም የእናቶች ቀን 

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.3K viewsኖኀ መፅሐፍ, 04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 22:32:27
መጽሐፍ ጥቆማ
" ከሞት ባሻገር "
በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2ተኛ እትም

_ ከልብ የፈለቀ መዝሙር _

"የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና
ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር”

ይህ ታላቅ ሕዝባዊ የአንድነት ዝማሬ መቼ የተጠና ዝማሬ ነው? ይህ ሁሉ ሕዝብ አንድ መዝሙር ለመዘመር ልምምድ የጀመረው መቼ ይሆን? ይህ ልዩ የሆነ የአቀባበል ሥነ ሥርዓትስ መቼ የተማሩት ነው? የሥራ ክፍፍል ያደረጉትስ መቼ ነበር? እናንተ ልብስ አንጥፉ ፣ እናንተ ከፊት ቅደሙ ፣እናንተ ዘንባባ ያዙ ብሎ ሥራ ያከፋፈላቸው የመዝሙሩን
ሥርዓት የምስጋናውን ወግ ያሳያቸው ማን ነው? ድንገት ሕዝብ ሁሉ አንድ አንደበት ሊኖረው እንዴት ይችላል?

ጌታ ሆይ የአንተን ፊት ያዩ ሰዎች የምስጋና
ትምህርት ቤት አያስፈልጋቸውም፡፡ ምስጋና እንዲሁ ዝም ብሎ ከአንደበታቸው ይፈልቃል። ከሕፃናትና ከሚጠቡት ሰዎች አፍ ለራስህ ምስጋናን ታዘጋጃለህ፡፡ የማይተዋወቁ ሰዎች ያለ ልምምድ አንድ መዝሙር ይዘምሩልሃል፡፡ ዳግም ስትመጣ በቀኝህ አቁመን እንጂ እኛም የማናውቀው አዲስ ምስጋና እናቀርብልሃለን። ፊትህን ለማየት አብቀን እንጂ ልብሳችን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም እናነጥፍልሃለን።

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
1.3K viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:00:03
#ነፍስ_ኄር

* ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች

በዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው በብዙ ኢትዮጵያዊያን በዘፈኖቿ የምትወደደው ~ የድሮዋ ዘፋኝ ፤ የአሁኗ ዘማሪት ሂሩት በቀለ በ80 አመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል ፡፡

ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል ፡፡

የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ80 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ፡፡

ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት ፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።

#ታዲያስ አዲስ
663 viewsኖኀ መፅሐፍ, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ