Get Mystery Box with random crypto!

ኖኅ Book Delivery

የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የሰርጥ አድራሻ: @noahbookdelivery
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.84K
የሰርጥ መግለጫ

The first and the only book delivery service in Ethiopia. Order books all over the world with fair price & fast delivery
Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 43

2022-07-12 07:55:07
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
"የመካክለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ
ከዓፄ ይኲኖ አምላክ-ዓፄ ሱስንዮስ"
ደራሲ፦ሞርዳኻይ አቢር
ትርጉም፦ማውሮ አዛሪዮስ

ታሪክ ተጠንቶና መሰረታዊ እውነታውን ሳይለቅ ሲፃፍ እጅጉን ደስ የሚልና መልካም የተሞክሮ ማሳያ ነው።ለዚህም በአይሁዳዊው ፕሮፌሰር ሞርዲኻይ አቢር የተፃፈው የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ እጅጉን ድንቅ ምስክር ነው።
መጽሐፉ የመካከለኛውን ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በጥሩ አተያይ የሚያትት አዲስ መጽሐፍ ሲኾን የሰለሞናዊውን ሥርወ መንግሥት ከአነሳሱ እስከ ውድቀቱ እና በቀይ ባህር ክልል የነበረውን የሙስሊሙንና የአውሮፓውያንን ፉክክር የሚዳስስ በእስታኤላዊው ፕሮፌሰር ሞርድኃይ አቢር የተፃፈ የምርምር ውጤት ሲሆን በበሳል የአተረጓጎም ብቃት በማውሮ አዛሪዮስ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፉ አስቸጋሪውንና ውስብስቡን የመካከለኛውን ዘመን ታሪክ የሚተነትንንና የዘመኑን የታሪክ ክፍተት የሚሞላ እንዲሁም የእስልምና ኃይሎች መነሳትን የኦሮሞን መስፋፋት፣የሰለሞናዊው መንግስት የውድቀት ምክንያቶች፣በቀይ ባህር ዳርቻ የነበሩት የትግራይ ሹማምንቶች የአውሮፓውያንን ሽርክና በተጓዥነት ስም የሚመጡ አውሮፓውያን ስውር ፍላጎት ጭምር ተንትኖ አቅርቧል።
ተርጓሚው በውጭ ቋንቋወች ጥናት B.A በታሪክና ኢኮኖሚክስ ጥናት B.A.ያላቸው ሲሆን ከስድስት በላይ የውጭ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩና ለዚህም ታላቅ የትርጉም ስራ ከትክክለኛው በውጭ ቋንቋ የተፃፉ ቅጅወች[ከጀርመንኛ፣ጣሊያንኛ፣ፈረንሳይኛ፣እንግሊዝኛ]ጋር በማዛመድና በማመሳከር ተርጉመው ለገበያ አቅርበውታል። ዶ/ር በኃይሉ ገብረመድህን አርአያ

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
2.1K viewsኖኀ መፅሐፍ, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:27:37
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
"ወደ ኢትዮጵያ ሰዎች"
በተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም

ደራሲው በመጽሐፉ መግቢያ አዲሱ ስራውን አስመልክቶ ባሰፈረው ጽሑፍ "እናንተ የሀገሬ ሰዎች፤ ይኽንን ድምጽ እንደ አንድ የራሴን ልጩኽ ብሎ እንደወጣ ድምጽ ቁጠሩት፡፡ በምድረ በዳ ሳይኾን በመካከላችሁ እንዳለ ድምጽ ቁጠሩት፡፡ የምትሰሙትን ደግሞ እንዲሚጮኽ፣ የምታምኑትን እንደሚክድ፣ የምትፈልጉት እንኳን ቢኾን እንደማይፈልግ፤ ደግሞ ፍላጎታችን ከገጠመ ደስ እንደሚለው መናኝ ነፍስ ጥሪ አስቡልኝ፡፡ ለኢትዮጵያ ሰዎች የተጻፈ ነው፡፡ አንዳንዱ ምሬት፤ የሚመለከተውን ይሞግታልና ሌላው ቦታ ያገባኛል ባይነት፤ መባል የለበትም ያለውን ይጸየፋል፡፡የሚመኘው ይናፍቃል፡፡ መድረሻው የጋራ ሀገር ናት፡፡" ይለናል፡፡

ከዚህ ቀደም "የመንገድ በረከት"፣ "ጎንደርን ፍለጋ" እና "ሀገሬን" የተባሉ ሦስት የጉዞ ማስታወሻ መጻሕፍትን ያበረከተልን ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ዛሬ በገበያ ላይ የዋለው አዲሱ ስራው ታሪክ፣ ተፈጥሮ፣ ሥልጣኔን ጨምሮ በጉዞው ለደረሰባቸው የሰደዳቸው መልእክቶች ስለ ሀገራችን ብዙ ይነግሩናል፡፡ ሃያ አራት ምዕራፎች ያሉትና በተለየ አጻጻፍ የቀረበው መጽሐፍ 190 ገጾች ሲኖሩት በ"ራዕየ ኢትዮጵያ" ክፍሉ ይቋጫል፡፡ ሄኖክ ስዩም ባለፉት አሥራ አምስት አመታት በኢትዮጵያ የቱሪዝምና ባህል ጋዜጠኝነት መስክ በርካታ ስራዎች የሰራና ሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽንን መስርቶ የኢትዮጵያን ጂኦግራፊክ መረጃ መረብን እውን ያደረገ ነው፡፡ በመደበኛነት ጉዞ ኢትዮጵያ የተባለ ሳምንታዊ የቴሌቨዥን ዘጋቢ ፊልም እያሰናዳ አየር ላይ ያውላል።

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
2.4K viewsኖኀ መፅሐፍ, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:09:25
በመላው አለም ላይ ያላችሁ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን እንኳን ለ1443ኛው ኢደል አደሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የአድነት በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞትን ኖኀ Book Delivery ይገልፃል።
Edi Mubarak

Join us @noahbookdelivery
3.1K viewsኖኀ መፅሐፍ, 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 08:19:18
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
"21 ችግሮች 21 ምክሮች"
ትርጉም፦ ተሥፋጽዮን ጋሻነህ

#አትደናገጡ!

አሸባሪዎች የአእምሮ ቁጥጥር ባለሞያዎች ናቸው፡፡ የሚገድሉት ትንሽ ሰዎችን ነው፡፡ ነገር ግን ቢሊዮኖችን የማሸበርና እንደ አሜሪካና አውሮፓ ህብረት ያሉ ትላልቅ የፖለቲካ መዋቅሮችን ያነቃንቃሉ፡፡ ከመስከረም 2001 ጀምሮ ባሉት አመታት ሽብርተኞች በአውሮፓ ህብረት 50 ሰዎችን፣ በአሜሪካ 10 ሰዎችንና በሌሎች ሃገራት በአጠቃላይ (በዋናነት በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታን፣ በፓኪስታን፣ በናይጄሪያና በሶሪያ) በአማካይ በአመት 5000 ሰዎችን ገድለዋል፡፡በተቃራኒው የትራፊክ አደጋ በተመሳሳይ አመታት በአውሮፓ ህብረት 80,000 ሰዎችን፣በአሜሪካ 40,000 ሰዎችን በቻይና 270,000 ሰዎችን በአጠቃላይ ደግሞ 1.25 ሚሊዮን ሰዎችን በአመት በአማካይ ገድሏል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የስኳር በሽታ 3.5 ሚሊዮን፣የአየር ብክለት ደግሞ 7 ሚሊዮን ሰዎችን በአመት በአማካይ ይገደላሉ፡፡ስለዚህ ከስኳር በሽታ የበለጠ ሽብርተኝነትን የምንፈራው ለምንድን ነው? ፓርቲዎች ለመንግስትነት ሲወዳደሩ በአየር ብክለት ምክንያት ሳይሆን በሽብር ጥቃት ሰበብነት ለምን ይሸነፋሉ?የቃሉ ጥሬ ትርጉም እንደሚያመለክተው ሽብርተኝነት ተግባራዊ ጉዳትን ከማድረስ በዘለለ ፍርሃትን በብዛት በማሰራጨት የፖለቲካን ሁኔታ የመለወጥ ወታደራዊ ስትራቴጂ ነው፡፡
ስለዚህ ሽብርተኝነት አያሸብርምና አትሸበሩ!!

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
4.7K viewsኖኀ መፅሐፍ, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 22:54:47
Book suggestion
"WHERE WINNERS LIVE"
Linda Galindo&Dave Porter

Praise for Where Winners Live
"Galindo and Porter's direct, no-nonsense approach brings to life the practical success strategies we have heard or seen before but often fail to execute.Using examples of accountable leaders at varying levels in their organizations, Where Winners Live motivates and instructs readers on how to maximize their full potential by being accountable.This is a good read for both experienced leaders and young professionals looking to grow in their careers."
Alfonzo D.Alexander

"Linda Galindo and Dave Porter clearly explain that the secret weapon for success in business and in life is personal accountability.Where Winners Live is a must-read for leaders and managers who are responsible for results in today's uncertain economy.If you are willing to open your
mind to 100 percent personal accountability and start living Where Winners Live,this book is for you."
W.David Rook

@Noahbook7 0939115238

Join us @noahbookdelivery
3.3K viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 12:33:01
መጽሐፍ ጥቆማ
"ካህኑ መልከ ጼዴቅ"
ንጉሠ ሰላም ወጽድቅ

ከታሪኩ ሠረቀ ፀሐይ ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያን ቤተክህነቱን ቤተመንግሥቱን የተቆጣጠረውን
የሐሰት ንግርት በሚገባ የሚያብራራ ድንቅ መጽሐፍ ነው። እኔ በበኩሌ ለዘመናት ስፈልገው የነበረውን እውነታ በማስረጃ አስደግፎ ስለጻፈልኝ ለነፍሴ እፎይታን አግኝቻለሁና ከአጉል የቤተ አይሁዳውያን የሐሰት ንግርት እንድትላለቀቁና ኢትዮጵያውያን ማነን የሚለውን ምሥጢር
እንድታውቁ እመክራለሁ። መጽሐፉ በርካታ ምሥጢሮችን የያዘና ብዙ በሰዎች ዘንድ እንቆቅልሽ የሆኑ ነገሮችን ከነማስረጃው ያብራራል። ከእነዚህም መካከል
1.ካህኑ መልከጼዴቅ ማን ነው?
2.ክህነተ-ሥርዓተ-መንግሥት እና ሃይማኖታዊ ሥርዓተ-መንግሥት ንግሥናን በተመለከት በሚገባ ተብራርቶአል።

3.ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ4ኛው መቶ ክፍለዘመን ነው የሚል የሐሰት ንግርት እንዳለና ነገር ግን ይህ ንግርት ሐሰት መሆኑንና የኢትዮጵያ ክርስትናና ሃይማኖት የሚጀምረው ከአዳም እንደሆነ በማስረጃ አስደግፎ ጽፎልናል።
4.የሮምና የአረብ ክርስትና በኢትዮጵያ ታሪክ ሃይማኖት ባሕል ላይ ተጽዕኖ
ስለመፍጠሩና እንዴት እንደፈጠረም አብራርቶልናል።
5.ኦሪት እና ብሉይ ኪዳን መሠረታዊ ልዩነት እንዳላቸውም ከእነማስረጃው
አዘጋጁ አስቀምጦልናል።
አንብቡት ሀሳብ አስተያየት ስጡበት።

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
4.0K viewsኖኀ መፅሐፍ, 09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 08:16:55
መጽሐፍ ጥቆማ
" አለማወቅ "
በዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ

"እኔ ሰው ነኝ ያልኩህ ለዚህ ነው። ሰው ነኝ ማለት ደግሞ ትርጉም አለው። ሰው ነኝ ስልህ ፍላጎት አለኝ እያልኩህ ነው፣ ሰው ነኝ ስልህ ስሜት አለኝ እያልኩህ ነው፣ ሰው ነኝ ስልህ የአካል ህመም የሚያመኝን ያህል ሃዘን ይሰማኛል እያልኩህ ነው፣ ሰው ነኝ ስልህ ሳለቅስ እንደ እንስሳ እንባዬን ዓይኔን ለማራስ ብቻ አልጠቀምበትም እያልኩህ ነው፣ ሰው ነኝ ስልህ እምባ ሆነው ከዐይኔ
የሚወድቁት ትንንሽ የሃዘን ቋጠሮዎች ናቸው እያልኩህ ነው ! ገባህ ! "
አለማውቅ

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
3.5K viewsኖኀ መፅሐፍ, 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 23:31:47
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
"ይመስላል ዘላለም"
በሌሊሳ ግርማ

30 የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ የተለያዩ፣የሚመሳሰሉም ይኖራሉ ብቻ ሁሉም እጅግ ምጡቅና ድንቅ ልብወለዶች።የወለዳቸው ልብ ደግሞ ከልብነቱ በላይ በአሰላሳይነቱ
የምናውቀው ነው።በሐሳብ እና ፍልስፍናዎቹ የታጨቁ ፈጠራዎቹ።ግን ደግሞ ውበታቸው አጃኢብ የሚያስብሉ ከልቡ የመነጩ፣የተጨመቁ፣የተቀረሩ ረቂቅ ትረካዎች።የቱን መርጬ የቱን እተዋለሁ የሚያስብሉ ናቸው።“የሩሲያ ፎቶግራፎች” እጅግ በጣም የወደድኩት ነው።እናማ እስኪ ከሱ ላይ ልቀንጭብላችሁ፦

"ሦስቱም ፎቶግራፎች እርስ በራሳቸው ዝምድና እንዳላቸው ያስታውቃሉ።የተሰሩበት ዘመንና ጥሬ እቃ ያመሳስላቸዋል።አሁን በተጨባጭ በተለያየ ስፍራና የሕይወት ጎዳና ላይ ካሉት ወንድማማቾችና እህት ጋር ፎቶግራፎቹ ያላቸው ዝምድና ግን ግልጽ አይደለም።አሁን ግልጹ ነገር ሁሉም ማናቸውንም አለመምሰላቸው ብቻ ነው።“ይሄ እኔ ነኝ” እል ነበር፤ ድሮ ልጅ እያለሁኝ።ወይም ደግሞ፣ ሌሎች “ይሄ ቶቲ ነው”ይሉ ነበር።በምስሉና በአምሳያው መሀል ያንን ያህል ልዩነት አልነበረም።በፎቶግራፍ ሳይሆን በአካል ያለች ከእሷ በወቅቶች ልዩነት የተወለደች እህቷን በስጋና በደም የምትንቀሳቀስ ፎቶግራፍ መስላት “እሷ እኔ ናት” ያለችም ሕፃን መኖሯን ሰምቻለሁኝ።“ይሄ ማነው?” ብለው የሚጠይቁ ሰዎች የሚመጡት በሂደት ነው። ከብዙ ዓመታት በኋላ በሀገረ ሩሲያ የሚሰሩ ምስሎችና የሩሲያው ኃያል መንግሥት እንደ አሻንጉሊቷና እንደ ልጆቿ ተበታትነውና ተሰባብረው ጠፉ።
ጥቆማ፦Roman Tewolde

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
3.7K viewsኖኀ መፅሐፍ, 20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 22:07:03 የቴዲ አፍሮ አዲሱ ስራው ነው ተጋበዙልን።


Watch "TEDDY AFRO - ናዕት (እያመመው ቁጥር ፪) - [New! Official Single 2022] - With Lyrics" on YouTube


4.1K viewsኖኀ መፅሐፍ, edited  19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 21:20:49
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" ከሣቴ ምሥጢር "
ከመልአከ ፀሐይ አባ ኃይለ መለኮት ይኄይስ

ለቆሙለት ዓላማ እንደ መኖር አስደሳች ነገር የለም።ብዙ ሰው የሚማረው ከልኩ በማያልፈው ኑሮ አንዳች ነገር ሹመት ወይም ሀብት ለመጨመር ሊሆን ይችላል"ይህ ግን አላፊ ጠፊ የዛፍ ላይ እንቅልፍ መሆኑን ከተረዳሁት ቆየሁ።እውነተኛው መንፈሳዊ ሕይወት ግን እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ምሥጢር እያራቀቁ በመንፈስ ቅዱስ ሠረገላ እየመጠቁ መኖር ነው"ይህ ሀብተ ክህነት የተሰጣቸው አባ ኃይለ መለኮት ግን ሁል ጊዜም መማር አውቆ ለማገልገል ያላወቁትን ለማሳወቅ በመሆኑ የሚደንቅ አላማ ነው።እነሆ አሁንም የምሥጢር ባለቤት ፈቅዶላቸው ከአገልግሎታቸው አልፎ ለካህናት ማስተማሪያ ለምእመናን መማሪያ ይሆን ዘንድ ከሣቴ ምሥጢር በሚል ርእስ እነሆ በረከት ማለታቸው ለትውልድም የሚተርፍ የአስተዋዮች አላማ በመሆኑ መጽሐፉ በብዙ መንገድ አስተማሪ ነው!
ብፁዕ አባ ኤርምያስ የሰሜን ወሉ እና የኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ሊቃውንት የተዳፈኑ እሳት ማለት ናቸው።ይህ የተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ ሲሞሟቅ ቆይቶ ድንገት እንደ ደመራ ችቦ ቦግ ይላል በዚህ ጊዜ ድንጋጤ ይፈጠራል።ሊቃውንትም ይህንን የተዳፈነ እሳት ይመስላሉ።ለሃያ ለሠላላ ዓመት ያኽል አንገታቸውን ደፍተው ሲማሩ ይኖራሉ።ውስጣቸው በምሥጢር እሳትነት ሲፈላ ኑሮ በመጨረሻ እሳት ሆነው እንደ ደመራ ችቦ ቦግ ይላሉ።ዜና ሊቅነታቸው ከር እስከ ዳር ይደርሳል።አባ ኃይለ መለኮት ይኄይስም ከእኒህ እሳታውያን ሊቃውንት አንዱ ናቸው፡፡ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንት እንደሚመስክሩላቸው ከልጅነት እስከ ሽበት ሲማሩ ኑራዋል ከአብነት ትምህርት ቤት የተለዩበት ቅጽበት የለም።
ማዕበል ፈጠነ


@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
3.7K viewsኖኀ መፅሐፍ, edited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ