Get Mystery Box with random crypto!

ኖኅ Book Delivery

የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የሰርጥ አድራሻ: @noahbookdelivery
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.84K
የሰርጥ መግለጫ

The first and the only book delivery service in Ethiopia. Order books all over the world with fair price & fast delivery
Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-29 19:05:00
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" መሠረታዊ የግዕዝ ቋንቋ መማሪያ "

መ/ር በትረማርያም አበባው

እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመን ግእዝ ቋንቋን ማወቅ መንፈሳዊ ግዴታ ነው። ምክንያቱም ቅዳሴው የሚከናወንበት፣ ማኅሌቱ የሚቆምበት፣ ዜማው የሚዜምበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚተረጎሙበት በዋናነት በግእዝ ቋንቋ ስለሆነ ነው። አንድ ሰው ቅዳሴ ሲቀደስ፣ ዜማ ሲዜም፣ ማኅሌት ሲቆም የሚባለውን ካላወቀው ሥርዓቱን በሚገባ ለማከናወን ይቸገራል። ስግዱ ሲባል ቋንቋውን ባለማወቁ ቆሞ ሊቀር ይችላል። ስለዚህ ይህ እንዳይሆንና በልምድ ሳይሆን በእውቀት የተመሠረተ ሥርዓተ አምልኮን ለመፈጸም እንዲረዳው ግእዝ ቋንቋን ማወቅ ይጠበቅበታል። በመሆኑም የግእዝ ቋንቋን በቀላሉ ለመረዳት ያስችል ዘንድ ይህንን መጽሐፍ አዘጋጅቻለሁ።
                                  -
              መ/ር በትረማርያም አበባው
               የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
371 viewsኖኀ መፅሐፍ, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 22:48:44
"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ

መጋቢት 18፣ 2015

በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ “የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ በ99 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ካሣዬ የለምቱ በ1916 በአዲስ አበባ ውስጥ የተወለዱ ሲሆን፤ በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል።
በ19 ዓመታቸው ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 ዓመታቸው ምንኩስናን ተቀብለዋል።

ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም የውብዳር ሲሆን፤ በወጣትነታቸው ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ መጠሪያቸው ወደ እማሆይ ፅጌማርያም ተቀይሯል።
ከ1984 ጀምሮ ኑሯቸውን በእየሩሳሌም አድርገዋል።

አባታቸው ገብሩ ደስታ የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን፤ በአፄ ሃይለስላሴ ዘመንም የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን ማገልገላቸውን የቤተሰባቸው ታሪክ ያስረዳል።

እማሆይ ፅጌ ማርያም እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ዕብራይስጥኛ፣ አማርኛ ና ግዕዝን አቀላጥፈው የሚናገሩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሙዚቃ ሥራዎቻቸው በማቅረብ የሚገኙትንም ገንዘብ ለድሆች መርጃ አውለዋል።

እማሆይ ፅጌማርያም ከሰሯቸው ከበርካታ የሚዚቃ ሥራዎች ውስጥ « Homeless Wonder » /ሆምለስ ወንደር/ ፣ «The Son of Seam» /ዘ ሰን ኦፍ ሲም/፣ «The Mad Man's Daughter» /ዘ ማድ ማንስ ዶተር/ እና «Mother's Love» /ማዘርስ ላቭ/ የሚል አርዕስት ያላቸው ሙዚቃዎች ከበርካታ ሥራዎቻቸው ውስጥ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ።

እማሆይ ፅጌማርያም በሙዚቃ መሳርያ ብቻ የተቀናበሩ ረቂቅ ሙዚቃ በመጫወት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት መሆናቸውም ይነገርላቸዋል።

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
800 viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 11:26:44
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" መገብተ ኦሪት "
በመምህር ምሥጢሩ ታየ

በጨለማ ለነበረ ሕዝብ ብርሃንን ማሳየት እንደምን ያለ ደግነት ነው? ብርሃን ክርስቶስ እስኪወጣ መዓልት ወንጌል እስክትመጣ፥ ቅዱሳን ነቢያት የተቀበሉትን መከራ ዘርዝሮ ቆጥሮ መናገር አይቻልም። ልጅነት ሳይቀበሉ በመንፈስ ቅዱስ ሳይታደሱ የሚደረግ መንፈሳዊ አገልግሎት ልዩ ብርታት ይጥይቃል። ቅዱሳን ነቢያት በዚህ ዓለም መከራ ሲቀበሉ በወዲያኛው ዓለምም  ሲወርዱ ቢኖሩም በዚያ ዘመን የነበረው ሕዝብ የሚመጣውን መሢሕ ተስፋ ያደርግ ዘንድ አዘጋጁ። የሚወለድበትን ስፍራ ቤተ ልሔምን፣ የምትወልደውን ብላቴና ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍስ ያላት መሆኑን፣ በዕለተ ልደቱ እጅ መንሻ የሚያቀርቡ ነገሥታቱን በእስትንፋሳቸው ያሟሟቁ እንስሳቱን አስቀድመው ያሳወቁን ነቢያት ናቸው።

ክርስቶስ ሳይመጣ ስለ ክርስቶስ ሰበኩ፤ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ከሰይጣን ልጆች ከአይሁድ በቀር ሁላችንም የሐዋርያትን ይን ዐይን አድርገን ያየነው ያወቅነው በነቢያት ስብከት ነው። በአጠቃላይ ከሐዋርያት ቀድመው ክርስቶስን ለዚህ ዓለም የገለጡ አባቶቻችንን ዜና መምህር ምሥጢሩ እንዲህ አንባቢን ወደ ዘመነ ነቢያት በትዝታ እንዲመለስ በሚያደርግ ልዩ የብዕር አጣጣል ቀርጸው ያቀረቡልን ስለሆነ ባነበብሁት ጊዜ የተሰማኝ ደስታ እንደሚሰማችሁ እርግጠኛ በመሆን ጋብዣችኋለሁ።

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
383 viewsኖኀ መፅሐፍ, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 09:32:14 እስከዚያው አልኖርም

“It is not uncommon for people to spend their whole life waiting to start living. ” ― Eckhart Tolle

ታላቁ ገጣሚ ጸጋዬ ገ/መድህን “አብረን ዝም እንበል” በተሰኘው ግጥሙ ውስጥ
      “ተስፋ መቀነን ነው መቼም
     የሰው ልጅ አይችለው የለም” ይለናል።

አንድም ህይወታችን ያለተስፋና እና ምኞት ነቅታ መጓዝ እንደማትችል ሲጠቁመን። በሌላ በኩል ደግሞ የሰውን ልጅ ማለቂያ የሌለውን ምኞት ሲያስዳስሰን ይመስለኛል። ህይወታችንን ብንቃኘው ደስታ ይሰጡናል ብለን ስንጠብቃቸው የነበሩት ነገሮች በእጃችን ሲገቡ እንዳሰብነው ደስተኛ ሳያደርጉን ይቀሩና ደግሞ ከፍ ወዳለ ሌላ ምኞት ያሻግሩናል።

“ይህንን ባገኝ ደስተኛ እሆን ነበር” የሁላችንም መፈክር አይደለም? ወይም የለመድነው የኑሮ ሂደት። ከላይ የሰፈረው የኤካርት ቶሌ አባባል ይህንን አኗኗራችን በደንብ ይገልጸዋል ብዬ አስባለው ። ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፤ ይህንን ያህል ገንዘብ ሳገኝ፤ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለው እያለን ለኑሮዋችን ቀጠሮ ስንሰጥ፤ ያሰብነው እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰንን ነው።

የሰው ልጅ ምኞት ማለቂያ የለውም። በጠየቅን ቁጥር ፈጣሪ ያልነውን ቢሰጠን እንኳን እንደሰው እረክቶ ለመኖር ይከብደናል። ለዚህ ነው ደስታችንን ነገ ከምናገኛቸው ነገሮች ጋር መቋጠር ዛሬን በሰመመን እንድንኖር የሚያደርገን።  ያሰብኩት እስኪሳካ ደስተኛ መሆን አልችልም ማለት ነው “አስከዛው አልኖርም” ማለት ነው።
የነገው ህይወታችን ትልቅ ትርጉም አለው፤ ዋጋው ግን የዛሬን ያህል በፍጹም አይሆንም።

ምንጭ፦Ethiohumanity
ሚስጥረ አደራው

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
647 viewsኖኀ መፅሐፍ, 06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 18:33:53
መጽሐፍ ጥቆማ
" ግዮን ወንዝ "
በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

«ለምን ትቀናለህ»

« ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው። ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው። ቅናት ግን በምታስተውል ነፍስ ውስ የሚበቅል መርዝ ነው። …ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ።ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም። ራእይህን፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች አሉ። ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል።… ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆነ አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን። ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር።

በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም።ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም። እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃ ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር።ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ። ያንተ ሕይወት ቁልፍ  የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው።ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ። መብለጥ ከፈለግህ አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን።» (ገጽ 39 እና 41)

«ድንገት የተበጠሰ ገመድ»

«በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው።የሕይወትህ ገመድ ሲበጠስ እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው በል።ገመድህ ሲበጠስ ሊተክልህ ነው። አብ የተከለውን ማንም አይነቅለውም» (ገጽ-59)

ወዳጄ ይህን መጽሐፍ  ብላ!

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
899 viewsኖኀ መፅሐፍ, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 17:09:58
መጽሐፍ ጥቆማ
" ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ "
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ምን አይነት ጻድቅ ሰው ነው? ከረዥም ጉዞ በኋላ ኢየሩሳሌም ተሳልሞ በመመለስ ላይ ሆኖ እንኳን መንፈሳዊነቱ አልቀዘቀዘም። ከመንፈሳዊ ጉዞ የሚመለሱ ሰዎች ምናልባትም ከጉዞው መጠናቀቅ በኋላ ለእራሳቸው እረፍት ይሰጣሉ። ሰውነታቸውን የሚያዝናና ከድካማቸው የሚያበረታ ነገር ለማድረግ አያመነቱም። አንድ አንድ ጊዜ ሰዎች ከመንፈሳዊ ጉዞ መልስ የሚያደርጉት መዝናናት ከገደብ አልፎ መስመሩን ጥሶ የጉዞውን በረከት እስከማሳጣት የሚደርስበት ጊዜ አለ።

ኢትዮጵያዊው  ጃንደረባ ግን ፍቅረ እግዚአብሔር የማይወጣለት መንፈሳዊ ነበር። የገንዘብ ሚኒስቴር እንደመሆኑ እንደ ባለስልጣን ብዙ ሊያያቸው የሚችሉ መዛግብት ቢኖሩትም ከስግደት መልስ መጽሐፍ ቅዱሳን እያነበበ የሚመለስ ባለ ሥልጣን ነበር።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለማንበብ ሥራ ስለሚበዛብኝ ጊዜ የለኝም የምትል ወንድሜ ሆይ እዚህ ላይ እራስህን ከጃንደረባው ጋር አነጻጽረው። ይቅርታ አድርግልኝ ምንም ሥራ ቢበዛብህ በንግስት ሕንዳኬ በገንዘብዋ ሁሉ ከሰለጠነው በጅሮንድ በላይ ስራ አይበዛብህም። ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ጅሮም እንዲህ ሲል እራሱን ይወቅሳል።

"እዚህ ላይ ታሪኩን ትቼ ወደ እራሴ መለስ ልበል። የንግሥቲቱን ቤተ መንግስት ትቶ ከምድር ዳርቻ ከኢትዮጵያ ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ ከተጓዘውና ለእግዚአብሔር ሕግና ለአምላካዊ እውቀት ካለው ፍቅር የተነሳ በሰረገላው ላይ ሆኖ እንኳን ቅዱሳት መጽሐፍትን ከሚያነበው ከዚህ ጃንደረባ የተሻልሁ ጻድቅም ጽኑም አይደለሁም።"

ገጽ 67-68

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
851 viewsኖኀ መፅሐፍ, 14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 16:23:30
መጽሐፍ ጥቆማ
"ብርሃን እናት"
7ኛ ዕትም
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

"እግዚአብሔር የሰው ልጅን ያዳነበት መንገድ በዕለተ ዐርብ በመሰቀሉና መከራን በመቀበሉ ብቻ የሚመስለውና ከነገረ መስቀሉ ውጪ ያለው ጉዳይ የሚጠቅም የማይመስለው ሰው ካለ ነገረ ድኅነትን ጨርሶ አልተረዳም።እንደዚያ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ተፀንሶ ተወልዶ ሠላሳ ዓመታትን መቆየት ሳያስፈልገው ልክ የመጀመሪያውን አዳም እንደፈጠረው የሠላሳ ዓመት የሆነ ሥጋንና ነፍስን ለራሱ ፈጥሮ መለኮቱን አዋሕዶ ሰው መሆን ይችል ነበር።ይህንን ቢያደርግም ሦስት ዓመታት በምድር ላይ አስተምሮ በጊዜው ተሰቅሎ የማዳን ሥራውን መፈጸም ይችል ነበር።እርሱ ግን ማዳኑን የጀመረው በማሕፀን ከመፀነስ ነበር።አረጋዊው ስምዖን‘ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋል’እንዳለ ማዳኑንም የጀመረው ሕፃን ሆኖ በመታቀፉ ነው።ሉቃ.፪፥፴

የጌታ የማዳን ሥራ ወሳኙ ታሪክ ከመስቀሉ ጋር በችንካር የታሰረበት ብቻ ሳይሆን በድንግል ማርያም እቅፍ በፍቅር የታሰረበት ቅፅበትም ነው።ክርስቶስ ሊያስታውሰው የማይፈልገው የልጅነት ሕይወት ያለው አይደለምና ስለ
ክርስቶስ የሚሰብኩም ሁሉ ይህንን ድንቅ የሕፃንነት ጊዜውንና ያደገበትን ሁኔታ ቸል ሊሉ አይገባም።ክርስቶስን ‘በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ ሆኖ’ በሰዎች ልቡና እንዲሣል በመጀመሪያ በድንግል ማርያም እቅፍ እንደተወለደ ሆኖ መሣል ይገባዋል።ልብህ ውስጥ ሳይወለድ የሚሰቀል ክርስቶስ ካለ ለወለደችው እናቱና ለድንቅ ልደቱ ዋጋ ልትሠጥ አትችልም።መስቀል መሸከሙ ዘልቆ የሚሰማህ በልጅነቱ ያቀፈችውን ድንግል ማየት ስትችል ነው።ሐሞትና ከርቤ መጠጣቱ የሚያስለቅስህ ድንግልናዊ ወተትን ካጠባችው እናቱ ጋር አብረህ ስትሆን ነው።"

FreeDelivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

Join us @noahbookdelivery
596 viewsኖኀ መፅሐፍ, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 15:18:56
መጽሐፍ ጥቆማ
" ሕማማት "
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
21ኛ ዕትም

"ጲላጦስ ‹‹እውነት›› የሚለውን ቃል ሲሰማ ‹‹እውነት ምንድር ነው?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ምላሹን ግን ሳይሰማ ወደ ውጪ ወጥቶ ለአይሁድ ‹‹እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም›› አላቸው፡፡ ...
    
ጲላጦስ የጌታችንን መልስ ሳይጠብቅ የወጣው የጠየቀው ጥያቄ ጊዜ የሚያስፈልገው እንደሆነ አውቆ ከአይሁድ እጅ ባስጥለው ይሻላል ብሎ ነው ይላል፡፡

ጲላጦስ ሆይ! ጥያቄ ጠይቆ መልሱን ሳይሰሙ መውጣት እንዴት ያለ ነገር ነው? ነጻ ላትለቅቀው ነገር ጥቂት ታግሠህ ብትሰማው ኖሮ ምን አለ? ለነገሩ ቆመህ ብትሰማው ኖሮ ‹እውነት ምንድር ነው?› ለሚለው ጥያቄህ ‹እውነትም ሕይወትም መንገድም እኔ ነኝ› ብሎ በመለሰልህ ነበር! (ዮሐ. ፲፥፮) ምስኪኑ ጲላጦስ ለእውነት ‹እውነት ምንድር ነው› ብሎ ጠየቀው፡፡ ምላሹንም ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጣ"

ገጽ 182

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
657 viewsኖኀ መፅሐፍ, 12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 17:28:11
መጽሐፍ ጥቆማ
" ዐስራ ሥድስት "
ደመወዝ ጎሽሜ
፬ኛ እትም

ከዓሥራ ሥድሥት መጽሐፍ ላይ የተወሰደ!
ከ1980ዎቹ አጋማሽ በኋላ የሚኖረው ዓለም አቀፋዊው የህዝቦች ጠቅላይ አስተሳሰብ፥ በመሰረታዊ የማንነት ጥያቄዎች የተቀነበበ ይሆናል። ህዝቦች “እኛ ማነን?” ይላሉ፤ ባህላቸውን ይጠጋሉ፤ ዘራቸውን ይፈልጋሉ፤ ለባህላቸው መጠበቅና ልዩ ስለመሆኑም መሞገት ይጀምራሉ።ይህን የሚያደርጉበት መንገድም በራሱ የተለየ እንደሆነ ሳሙኤል ይገልጻል። የጥያቄዎቻቸውን መልሶች የሚፈልጉት በልማዳዊው መንገድ ነው/they want to answer in the traditional way/።

ሰዎች ማንነታቸውን፥ ከአያቶቻቸው፣ ከእሴቶቻቸው፣ ከሃይማኖታቸው፣ ከልማዶቻቸውና ከባህላዊ ተቋሞቻቸው አንጻር መግለጽ ይጀምራሉ። ሰፋ ተደርጎ ሲታይ፥ ሕዝቦች ከራሳቸው ስልጣኔ አንጻር መታወቅን ይመርጣሉ። በመሆኑም ልዩ ልዩ ስልጣኔዎች በመኖራቸው ይላል ሳሙኤል፥ ግጭት የመኖሩ ነገር ጥርጣሬ ውስጥ አይገባም። አንደኛው በሌላኛው የባህል ተጽእኖ ስር ላለመውደቅ ይታገላል። በዚህ ማህበረ-ባህላዊ እውነታ ምክንያትነት፥ የክፍለ ሃገራትና የአካባቢ ፖለቲካ በብሄርና በጎሳ ጥያቄዎች የሚመራ ሲሆን፥ አጠቃላዩ የዓለም ፖለቲካ ግን በስልጣኔዎች ግጭት የሚጦዝ ይሆናል። የፖለቲካው አውድ በስልጣኔዎች ፉክክር ይመካል። (ገጽ 294)
እያለ ይቀጥላል!!! መልካም ንባብ።

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238
 

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
678 viewsኖኀ መፅሐፍ, 14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 17:27:38
መጽሐፍ ጥቆማ
" ሶስተኛው ኪዳን "
5ኛ ዕትም
ደመወዝ ጎሽሜ

ዕውቀት የነፍስ ምግብ ነው! ይህ መፅሐፍ ትኩረቱ በመንፈሳዊ የዓለም ትርጓሜ ብቻ ሣይሆን በሌሎች የአለም ምልከታዎች የመፅሃፉን አንባብያን አዲስ የዕውቀት መሠረት አንዲያገኝ የሚረዱ በርካታ የጥበብ እና የዕውቀት ርዕሶችን የሚዳስሱ አንኳር ነጥቦችን ይዟል።

በ፫ኛው ኪዳን የአለም ወቅታዊ ጉዳዮች(የአለም ኃያላን ምልክቶቻቸው ፣ እንደ ንስር ፤ የኃይል አሰላለፋቸው) ከመተንተናቸው በተጨማሪም የየዘመኑ ፍልስፍናዎች ፤ ኃይማኖታዊ እና ስነ ምግባራዊ ጉዳዮች በስተጀርባ የሚገኙት ፅንሰ ሐሳቦች በጥልቀት ቀርበዋል።

በዚህ የአቀራረብ መንገድ ሦሥተኛው ኪዳን መንፈሳዊውን እና ቁሳዊውን ፤ የማይታየውን እና የሚዳሰሰውን ዓለም በአንባቢው ዓይነ-አዕምሮ እንዲገለጽ ያደረገበት ድንቅ የክፍለ ዘመኑ መፅሐፍ ነው።

በሰው ዘር ላይ ሁሉ የሥጋ እና የነፍስ ባሕሪያት አሉ። ከነዚህም ባሕሪያት ሥጋችንን ረሃብ ሲሰማን ምግብ እንደምናቀርብለት ሁሉ የነፍሳችንንም ረሃብ ዕውቀት ስናቀርብለት ይታገሳል።

ይህን መፅሐፍ በማንበብ ለነፍሳችን ዕውቀት ብቻ ሳይሆን ለመንፈሳችን መዳንን እናገኝበታለን። የነፍስ ምግቧም ዕውቀት ነው እንዲሉ አባቶቻችን!

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
615 viewsኖኀ መፅሐፍ, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ