Get Mystery Box with random crypto!

ኖኅ Book Delivery

የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የሰርጥ አድራሻ: @noahbookdelivery
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.84K
የሰርጥ መግለጫ

The first and the only book delivery service in Ethiopia. Order books all over the world with fair price & fast delivery
Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-18 23:06:19
Book Suggestion
" Rich Dad Poor Dad "
Robert T. Kiyosaki

Rich Dad Poor Dad is Robert's story of growing up with two dads—his real father & the father of his best friend,his rich dad & the ways in which both men shaped his thoughts about money and investing.The book explodes the myth that you need to earn a high income to be rich & explains the d/t b/n working for money & having your money work for you.

In many ways,the messages of Rich Dad Poor Dad,messages that were challenged and criticized 25 ago,are more meaningful,relevant & important today than ever.

Rich Dad Poor Dad..
Explodes the myth that you need to earn a high income to become rich
Challenges the belief that your house is an asset
Shows parents why they can't rely on the school system to teach their kids about money
Defines once and for all an asset and a liability
Teaches you what to teach your kids about money for their future financial success

FreeDelivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
485 viewsኖኀ መፅሐፍ, 20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 08:39:19
መጽሐፍ ጥቆማ
‹‹ ሕግጋተ ሥልጣን ››

በአንጋፋው የራዲዮ ጋዜጠኛ ጌታሁን ንጋቱ የተተረጎመ።

ጋዜጠኛ ጌታሁን የተረጎመው የአሜሪካዊው ደራሲ ሮበርት ግሪኔ 48 laws of power የተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡
መጽሐፉ 48 ሕግጋትን የያዘ ሲሆን፣ ከታሪክ- ሕግጋቱን በመተግበር የተሳካላቸውን እና ባለመተግበር ደግሞ የወደቁትን ያጣቅሳል፡፡
‹‹ መሪነት ጉልበት መጠቀም ብቻ አይደለም ፣ ጥበብ እንጂ፤ ›› የሚለው መርህ የመጽሐፉ ቁልፍ መልዕክት ሲሆን፣ ይህንኑ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው እያብራራ ያመላክታል።



ህግ 28 በደፋርነት ወደ እርምጃ ግባ

በድርጊቱ ሂደት እርግጠኛ ካልሆንክ አትሞክረው፡፡ የአንተ ጥርጣሬና ማመንታት የድርጊቱን አፈጻጸም ያውከዋልና፡፡ ፍርሀት አደገኛ ነው፡፡ በደፍርነት መግባት ይበልጥ የተሻለ ነው፡፡


ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
442 viewsኖኀ መፅሐፍ, 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 08:04:28
መጽሐፍ ጥቆማ
" ስለ ትናንሽ አለላዎች "
ዮናስ አ.

አኹን ግጭታችን የርዕዮት አለም አይደለም። አደባባይ ተሰብስበን ዲስኩር የምንደሰኩርበት ያ ዘመን ላይመለስ አክትሞለታል። ያን ዘመን የሚናፍቁ እጸድቅ ባይ አላዋቂ ትናንተኞች በየሜዳው በባዶ ሜዳ ሲንፈራገጡ ሲያይ ይገርመዋል። እንኮይ ሆይ፣ አይጩኹብኝ ጅብ ከሄደ ቆይቶል ቢላቸው ይወዳል።



ጥሎብን የአድባር የአውጋር፤ ዛሬአችንን ከትናንት አሰናስለን ከምንዋጅ በአፄ ማንቲዎስ ዘመን የተፈጠረች ቀጭን አሉባልታ ጀሮቻችንን እና ብልታችንን ትገዛዋለች። ሀገራችን ከብዙ የታሪክ ድብዳብና ከኁልቆ መሳፍርት አሉባልታ የተገነባች የሶስት ሺ ዓመት ኩይሳ ናትና። ነገር ግን አኹን ግጭታችን አጽንሰ ሐሳብ፣ ከዲበ አካላዊ እንቆቅልሾችና ከእውነት ምንነት ጋር አደለም።



ዲበ አካልም፣ ጽንሰ ሐሳብም ውጫዊ ናቸው። ወጫዊ ችግሮቻችንን በቀላሉ የምንቀርፍበት የቀመር ዘመን ላይ ነን። በጨረቃ የማይገረም ትውልድ ነው ያለው። የአራት ዓመት ህጻናት በቡድሀ ቦርጭ ይቀልዳሉ። ፍልስፍና አልፈነው የመጣነው የጋርዮሽ ዘመን ስነ-ዕውቀት ነው። አሁን የሚያስቡልን የኤለክትሪክ አንጎሎች ከወዳደቁ ነገሮች ሠርተን ጨርሰን ሁሉን ነገር በስሌት እናከናውናለን። ፍቅርና ናፍቆትን ጭምር።

ዛሬ ዛሬ እውነት የግል ናት።

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
461 viewsኖኀ መፅሐፍ, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 04:17:33
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፦ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም ፣ በጤና ፣ በፍቅር ፣ በደስታ ፣ በሀሴት ፣ በመተሳሰብ ፣ በብልጽግና እንዲሁም በአንድነት እንኳን አደረሳችሁ!


Free Delivery
መፅሐፎችን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
810 viewsኖኀ መፅሐፍ, 01:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 21:13:48
መጽሐፍ ጥቆማ
"ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት"
መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ዶ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

ይህ መጽሐፍ የነገረ ማርያም (Mariology)ድንቅ ምሁራዊ ጥናት ከመሆኑ ባሻገር ውዳሴ ማርያም ትርጓሜን ከቤተ ክርስቲያን ቀደምት አበው ሥነ ጽሑፍ(Patristic Litrature)ጋር ያጣመረ አባ ጊዮርጊስን ከቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ቅዱስ ያሬድን ከዮስጦስ ሰማዕት፣ አባ ህርያቆስን ከቅዱስ ጄሮም ጋር ለምስክር የጠራ ቴዎሎጂ ከአብነት ትምህርት ጋር ሲጣመር እንዴት ያለ ውበት እንዳለውና ለክህደት የሚዳርጋቸው በአግባቡ ያልተማሩና ያላነበቡትን ሰዎች ብቻ እንደሆነ በተግባር ያስመሰከረ፣ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን ያስከበረ እጅግ እጅግ ውብ ሥራ ነበረ።

በዛሬው መጠሪያቸው የመጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ዶ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ  ‘ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት’ መጽሐፍ ያለ ምንም ማጋነን ይሄ ትውልድ ተሳልሞ ሊያነበው የሚገባ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ ጸሐፊውን ለPHD ያበቃ እኛን ደግሞ ለጥልቅ ንባብ ያነቃ ታሪካዊ መጽሐፍ ነው። ምንም እንኳን በጸሐፊያን ዘንድ የተሻሉ ሥራዎችን አይቶ እንዳላየ የመሆን በሽታ(Silent conspiracy) የጸናበት ዘመን ቢሆንም በመጽሐፉ የተጠቀማችሁ ጸሐፍት ሁሉ ስለዚህ መጽሐፍ ውለታ ዝም ልትሉ አይገባም።

ወዳጄ ይህ መጽሐፍ ትናንት ባይኖር የዛሬዎቹ እነ ‘የብርሃን እናት’ ጨርሶ ባልኖሩም ነበረ።በእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ቤት ሊኖር የሚገባና በማንበብህ የምትኮራበት ውድ መጽሐፍ መሆኑን ስታነቡት ታምኑኛላችሁ። መጽሐፉ አሁን ገበያ ላይ ነው።‘ይህን መጽሐፍ ብላ’ ብዬ ስናገር እንደ ሕዝቅኤል ‘በላሁት ጣፈጠኝ’ እንደምትሉ በመተማመን ነው።

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

Join us @noahbookdelivery
313 viewsኖኀ መፅሐፍ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 06:09:58
የውጪ መፅሃፎችን በነፃ ማውረድ የምትችሉባቸው ገፆች!
1. www.pdfdrive.com
2. https://zlibrary.to
3. booksee.org
4. bookyards.com
5. doabooks.org
6. bookboon.com
7. bookzz.org
8. golibgen.io
9. libgen.io

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
48 viewsኖኀ book delivery, 03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 05:56:58 እውነተኛ ሠላም

ንጉሱ በትክክል ሠላምን ሊወክል የሚችል ስዕል መሳል ለቻለ አርቲስት(የስዕል ሙያተኛ) ወሳኝ የሆነ ሽልማት ለመስጠት ተዘጋጅቶ አሳወጀ፡፡ ብዙ የስዕል ሙያተኞችም ሙከራ አደረጉ፡፡ ነግር ግን ንጉሱ የቀረቡትን ስዕሎች ሲመለከት ሁለት ስዕሎችን ብቻ ወደደ፡፡ ንጉሱ ቀልቡ ካረፈባቸው ሁለት ስዕሎች አንዱን መምረጥ የተዘጋጀውን ሽልማት መስጠት ነበረበት፡፡

አንደኛው ስዕል ፀጥ ያለ ባሕርን የሚወክል ስዕል ነው፡፡ አሳሳሉም ባሕሩ በዙሪያው ያሉትን የተራራ ማማዎች እንደ መስታውት አንጸባርቆ ለተመልካች ቅርብ ያደርጋል፡፡ አናቱ ላይም በነጭ ደመና ተሸፍኖ ሰማዩ አርብቦበታል፡፡

ይህን ስዕል የተመለከተ ማናቸውም ሰው እውነተኛ የሠላም ምልክት አድርጎ ሊወስደው የሚችል የአሳሳልጥበብ ያረፈበት ነው፡፡
ሌላኛው ስዕል እንዲሁ የተራራ ስዕል ሲሆን በተራራው ላይ የሚታየው የተራቆተና ያገጠጠ አለት በላዩ ላይም ቁጣ የሚነበብብት ሰማይ የዝባብ እንባውን ሊያንጠባጥ በብልጭታ ጥፊ እየተመታ ይታያል፡፡ በተራራው ጎንም የሚያጓራ ፏፏቴ ይታይበታል፡፡ ስዕሉን ላየ ጨርሶ የሠላም ስሜት የማይፈጥር ስዕል ነበር፡፡ ነገር ግን ንጉሱ ተጠግተው በአንክሮ ሲመለከቱት በፏፏቴው መውረጃ ጀርባ በተሰነጠቀው አለት ላይ ትንሽየ ቁጥቋጦ በቁጥቋጦው ላይ ደግሞ ወፏ ጎጆዋን ቀልሳ ተመለከቱ፡፡ በዛ በተናወጠው የፏፏቴ ድምጽ መሃል ወፏ በፍጹም ሠላም ተቀምጣለች፡፡
የትኛው ስዕል የአሸናፊነት ሽልማቱን የሚወስድ ይመስላችኋል? ንጉሱ የመረጡት ስዕል ሁለተኛው ስዕል ነበር፡፡

ለምን እንደመረጡት ንጉሱ ሲያብራሩ “ሠላም ማለት ምንም አይነት ድምጽ በማይሰማበት፣ ሁከትና ጫጫታ በሌለበት ስፍራ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ሠላም ማለት ያለነው በግር ግር መሃል ቢሆንም ፀጥ ያለ ልብ ሲኖረን ሠላም አለን ማለት ነው፡፡ እሱ ነው እውነተኛና ፍፁም ሠለም፡፡” አሉ፡፡ መጽሐፉም የሠላም መጓደልን ሲያጠይቅ አፋቸው ዝም ብሏል በልባቸው ግን ብርቱ ሰልፍ አለባቸው እንዳለው፡፡ ውስጣችን ሠላም ሲያጣ በሆነ ባልሆነው መበሳጨት እንጀምራለን፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተቃራኒው ያለው እውነት ነው፡፡

Source: Wisdom pearls “The Real Meaning of Peace”
                       ምስጋናው ግሸን


"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
68 viewsኖኀ መፅሐፍ, 02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 21:08:11
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" አንኪይራ "
መጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ ሞሲሳ

አንኪይራ (Anykra)  ቃለ ጽርእ ነው። አንኮራ (Ancora)  ቃለ ላቲን ነው። ስዋስዉዋዊ ፍችው መልሕቅ ማለት ነው። ተምሳሌታዊ ውክልናውም የክርስቶስና በእርሱ ላይ ያለን ጽኑ እምነትና ተስፋ ነው።

አንኪይራ በዘይቤያዊ (Metaphorical)  ፍች ደግሞ የመረጋጋትና የደኅንነት፣ የጽሞናና የሰላም፣  የእምነትና የጥንካሬ፣ የስርና መሬት የመያዝ ትእምርት ነው።

በዚህ መሠረትነት  እኛ ትእምርተ መስቀልን በአንገታችን እንደምናስረው፤  በግንባራችንና በእጃችን እንደምንነቀሰው፤በአልባሳት እንደምንጠልፈው፤ በመካነ መቃብር ላይ እንደምናቆመው ሁሉ፥ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትም ትእምርተ አንኪይራን ወይም ትእምርተ መልሕቅን  በዚሁ መልክ ያከብሩታል።

ቅዱሰ ኤጲፋንዮስ አዘጋጅቶት ለነበረው መጽሐፉ፥በመጀመሪያዎቹ የክስትና ዘመናት የክርስትናና የክርስቲያኖች፥ የክርስቶሳዊነታቸው መለያ አርማ የሆነውን ትእምርተ መልሕቅን (አንኪይራን)፥ለመጽሐፉ ርእስ አድርጎ መጽሐፉን "መጽሐፈ መልሕቅ" ብሎ እንደሰየመ ሁሉ፤ መጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ ሞሲሳም መጽሐፋን "አንኪይራ" - መልሕቅ ብሎ ሰይሟል።

የመጽሐፉ ርእስ መጽሐፍ ራሱ ነው። ዘይቤ ለሚገባው ደግሞ መጽሐፉ ርእሱ ነው። ርእስ እና ይዘት ተሰናስለዋል። በርእስና በይዘት መካከል መረጋገጥ የለም።ሰባኪነቱን በቦታው ተጠቅሞበታል ባይ ነኝ።

በመጽሐፉ ውስጥ ቤተሰብ፣ቤተ ክርስቲያንና ሀገር  በከፍተኛ ማዕበል ከወዲህ ወዲያ የሚላጉ መርከቦች ናቸው።እነዚህ መርከቦች መሬት ይዘው  ከማዕበል መላጋት እንዲተርፉ መልሕቅ- አንኪይራ  ሲጣልላቸው  ታያላችሁ።

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
451 viewsኖኀ መፅሐፍ, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:09:46
ዓለማየሁ ገላጋይ ሚያዝያ 5 /1960 ዓ.ም በ አራት ኪሎ አካባቢ ተወለደ። በዳግማዊ ምኒልክ ፩ኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል። በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስኩል ኦፍ ጆርናሊዝም ተምሮ ተመርቋል።
ዓለማየሁ ገላጋይ "ኔሽን" ፣ " አዲስ አድማስ " ፣ "ፍትሕ" ፣ "አዲስ ታይምስ" ፣ እና "ፋክት"ን ጨምሮ በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ በሚያቀርባቸው መጣጥፎች ይታወቃል።

ሥራዎች
- ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት፣ ቅበላ፣ የብርሃን ፈለጎች፣ ኢህአዴግን እከሳለሁ፣ኩርቢት፣ ወሪሳ፣ አጥቢያ፣የፍልስፍና አፅናፍ ፣በፍቅር ስም ፣ መለያየት ሞት ነው ፣በእውነት ስም(ታለ) ፣ውልብታ፣በእምነት ሥም (ሐሰተኛው) የተሰኙ ልቦለድ ና ኢልቦለድ መፃሕፍት ለአንባቢያን አበርክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም "መልክዓ–ስብሐት " በተሰኘው መጽሐፍ 27 ጸሐፊያን፣ያን ደራሲያን፣ገጣሚያንና ሰዓሊያን አሳትፎ በማሰናዳት ለአንባብያን አድርሷል።
ዓለማየሁ ገላጋይ በሃያሲነትም ስም ያተረፈ የብዕር ሰው ነው። ገና ለሕትመት
ያልበቁ በርካታ ሥራዎችም አሉት።
ምንጭ፦Wikipedia
ዛሬ የተወለደበትን መልካም ልደት ልንለው ወደድን።

Join us @noahbookdelivery
842 viewsኖኀ መፅሐፍ, 09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 09:14:01
Book Suggestion
"Siege and Storm"
Leigh Bardugo 

Hunted across the True Sea, haunted by the lives she took on the Fold, Alina must try to make a life with Mal in an unfamiliar land, all while keeping her identity as the Sun Summoner a secret. But she can't outrun her past or her destiny for long.

The Darkling has emerged from the Shadow Fold with a terrifying new power and a dangerous plan that will test the very boundaries of the natural world. With the help of a notorious privateer, Alina returns to the country she abandoned, determined to fight the forces gathering against Ravka.

But as her power grows, Alina slips deeper into the Darkling's game of forbidden magic, and farther away from Mal. Somehow, she will have to choose between her country, her power, and the love she always thought would guide her - or risk losing everything to the oncoming storm.

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
109 viewsኖኀ መፅሐፍ, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ