Get Mystery Box with random crypto!

ኖኅ Book Delivery

የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የቴሌግራም ቻናል አርማ noahbookdelivery — ኖኅ Book Delivery
የሰርጥ አድራሻ: @noahbookdelivery
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.84K
የሰርጥ መግለጫ

The first and the only book delivery service in Ethiopia. Order books all over the world with fair price & fast delivery
Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-08 22:48:24
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" እስረኞቹ "
እንዳለጌታ ከበደ

ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ብዙዎች ተገስጸዋል፣ በገንዘብ ተቀጥተዋል፤ ከደረጃቸው ዝቅ ተደርገዋል፤ ተሰደዋል፤ ታስረዋል፤ለሞት ተላልፈው ተሰጥተዋል። ደግሞም በየዘመናቱ የታሰሩ ከያኒዎች እና ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆኑ የታሰሩ ሃሳቦችም አሉ። ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው <ተወሽቀው> የተቀመጡ። የታሰረው ወይም የሚታሰረው ግለሰብ ብቻ አይደለም፡፡ ግለሰቡ ሲያስበው የነበረው ሃሳብ ብቻም አይደለም፡፡ አሳሪውም ታሳሪ ነው፤ <ደግሞ መጡብኝ> ብሎ ራሱን አሳስሮ የተገኘ . . .በነጻነት የተገለጸውን ሃሳብ ምን መዘዝ ያስከትልብኝ ይሆን? ብሎ በመሳቀቅ ዘመኑን የፈጀ . . .

እና ይህ መጽሐፍ ስለእነዚህ እስረኛ ስለነበሩ ግለሰቦች፣ እስረኛ ስለሆኑ ሃሳቦች እና <አሳሪዎቻቸው> ይተርካል፣ እያሳቀም፣ እያሳቀቀም ፤ እያስለቀሰም ፣ እያጫወተም ፣ እያጨዋወተም. . . <ነበር>ን እና <ነው>ን
ያወጋል።

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
370 viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 22:53:58
157 viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 22:48:28
መጽሐፍ ጥቆማ
" ቢስሚከ ነሕያ "
ትርጉም፦ መሐመድ ሰዒድ

የጠበቅሽው  የጓጓሽለት ነገር ፍጻሜው እርቆሻል?አብሽሪ አላህ [ሱ ወ]አል-ወሐብ መሆኑን አትዘንጊ ድንገት ሳታስቢው ከማያልቀው ስጦታው ያዘንብልሻል አዎ አላህ (ሱ.ወ) በእጅጉ የሚሰጥ ችሮታው ሰፊ የሆነ ለጋስ ነው በጣም የምትወጂው ሰው በጣም ውድ የሆነ ስጦታን ሰጥቶሽ ከምትደሰቺው በላይ አል-ወሐቡ ስለሚወድሽ ብቻ በድንገት የሚሰጥሽ ስጦታ የተለየ ነው ምንም ነገር አያሳጣንም በበለጠው ሊታካልን ቢሆን እንጂ ምክንያቱም እሱ አል-ወሐብ ነው!ለኛ ያለውን ውዴታ እኛ ለሱ ካለን ውዴታ አስቀድሟል [{ ይወዳቸዋል፤ይወዱታል።{አል-ማኢደህ፡54}]

የሰው ልጅ ደካማ ፍጡር ነው። ፍላጎቶቹም የሚያልቁ አይደሉም። ምግብና መጠጥ ይፈልጋል። ስለሆነም አላህ (ሱ.ወ) በአር-ረዛቅ ስሙ ይገለጥለታል። ከአደጋ መጥጠበቅና እንክብካቤንም ይፈልጋል። አላህ (ሱ.ወ “አል ሐፊዝ” በሚለው ስሙ ይደርስለታል፡፡
መስተካከልና በጥሩ ሁኔታ መታነፅንም ይፈለጋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) “አር-ረሒም" በሚለው ስሙ ይከበዋል። ማወቅና መገንዘብም ይፈልጋል። አልፈታሕ፣ አልዐሊም; በሚለው ስሙ የፍላጎቱን ያሟላል። ኃይልና ጥንካሬ ይፈልጋል። አል_ዐዚዝ በሚለው ስሙ ያጠናክረዋል።

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
179 viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 15:38:44
መጽሐፍ ጥቆማ
" የነቢያት ታሪክ "
ከነብዩሏህ አደም (ዐ.ሰ) እስከ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ዝግጅት፦ ሙሐመድ አሊ (ቡርሃን)

የነቢያት ታሪክን ለምሳሌነት የምናጠናው በብዙ ምክንያቶች ነው፡፡በዋናነት ግን ከሌሎች ታላላቅ ባለታሪኮች የሚለዩበት ትልቅነት አለ፡፡ከሰዎች አእምሮ በላይ የሆኑ የዓለም ምስጢሮችን ያዉቃሉ፡፡ ከአምላክ የሚገለጥላቸው ጠቃሚ የህይወት ምሳሌዎችና መርሆዎች አሏቸው፡፡ የመኖርን ፋይዳና ግብ በመግለጥ ከነቢያት የተሻለ መንገድ የሚመራን ጠቢብ ወይም አርአያ አናገኝም፡፡ ለዚህ ከፍ ያለ ምሳሌ ስንል የነቢያትን ድልና ታሪክ ማጥናት ይኖርብናል፡፡

በሁሉም ነቢያት ውስጥ ብዙ ድንቅ ተዓምራትና ምልክቶች አይተናል።በፍጥነት ተፅዕኖ በመፍጠርና ፅኑ ተከታዮችን በማፍራት ግንነብዩ መሐመድ (ሠ.ዐ.ወ) ስኬታማ ናቸው፡፡ መልክታቸው የገባቸው ተከታዮቻቸው
የሳቸውን ፈለግ ለመቀጠል ፅኑ እምነት መላበስችለዋል፡፡ይኸው በአስራ ሶስት
ዓመታት የትግል ቆይታቸው ብቻ እጅግ ከፍተኛ ስቃይና መከራን መቋቋም የሚችሉተከታዮች አፍርተዋል፡፡

ነቢያትና የጥበብ ሰዎችን በሁለት ፈጽሞ የማይገናኙ የጥበብ ምንጭ ተጠቃሚነታቸው እንለያቸዋለን፡፡የጥበብ ሰዎች ስለሁሉም የተፈጥሮ ሚስጥራት ለመናገር አእምሯችንታገለግላለ ይላሉ።ነቢያት በተቃራኒው አጠቃላይ የተፈጥሮ ፈጣሪያለ ሲሆን እኛም ሆንን ሌሎቹ ፍጥረታት ሁሉ የርሱ ድርሰቶችነን፡፡
ከመጽሐፉ የተወሰደ

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
587 viewsኖኀ መፅሐፍ, 12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 08:48:30
መጽሐፍ ጥቆማ
" ፍኖተ - ጀነት "
በኡስታዝ በድሩ ሁሴን

በዶክተር ኻሊድ አቡሻዲ ተዘጋጅቶ በኡስታዝ በድሩ ሁሴን ተረርጉሞ " ፍኖተ - ጀነት " በሚል ርዕስ ለንባብ በቃ ::
ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ከዚህ ቀደም እጅግ ተወዳጅ የሆኑት ..
ለውጥ
የምጥቀት ጎዳና ቅጽ አንድ
የምጥቀት ጎዳና ቅጽ ሁለት
የተሰኙ መጻሕፍትን ተርጉሞና አዘጋጅቶ ለንባብ አብቅቷል ::

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

  @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
733 viewsኖኀ መፅሐፍ, 05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:09:18
መጽሐፍ ጥቆማ
" ፍጻሜ አልባው ሕይወት "
ፀሀፊ፦ በሐሰን አዩብ ተጽፎ
ተርጓሚ፦ በሁሴን ከድር

ስለመጽሐፉ ሙሐመድ አሊ ( ቡርሃን ) ይህን አስተያየት ሐሳብ ሰጥቷል።

" ... በአጭሩ እንዲህ እናስብ ፤ በየትኛውም የሃይማኖት ወይም የፍልስፍና  ( በተለይ የሜታ ፊዚክስ ) እሳቤ ውስጥ ከሞት ወዲያ ስላለ ዓለም መጠየቅ  ፣ ማሰብ ፣ መንገርና መተረክ ማዕከላዊ ጭብጥ ነው። የኃይማኖት መሰረት ማዕዘን ነው።ሰዎች በምድር ያላቸውን ቆይታ ሲጨርሱ በተለምዶ ሞት በምንለው የመኖር ፍጻሜ ይለዩናል።

በሳይንስ ቅኝት ዳራ ከሞት በሞት በኃላ ምንም የሚታሰብ ዓለም የለም። ሳይንስ የሚኖረው ሙከራ ( Experiment ) እስካለ ነው። በመጪው ዓለም ስለሚነገረን ትርክት ደግሞ ለቤተ ሙከራ የሚሆን ቁስ አያገኝም። ስለዚህ ሳይንስ ስለሰው ልጅ የህይወት እውነታ የሚያጠናው መተንፈስና መኖር እስከቻለ ድረስ ብቻ ነው።... "

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238
 

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
74 viewsኖኀ መፅሐፍ, 15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 06:43:22
መጽሐፍ ጥቆማ
" ማሙሽ "
2ኛ ዕትም
ማይክል አዝመራው

በድንጋጤ ጉሮሮው አለመጣበቁን ለማረጋገጥ "ኧኧኧ" በሚል ድምፅ ወሬውን እየጀመረ "ኧኧኧ ያው አስተማማኝ ውበት ያላት ሴት ናት።"
"እንደዚህ የደከመ አገላለፅ ሰምቼ አላውቅም።ምንድን ነው
አስተማማኝ?በደንብ ግለፃት እንጂ!"

"ሰውነቷን ብታዬው ነበር የምለው የሚገባህ።" አይኖቹን ጨፍኖ የመጀመሪያ ቀን ያያትን ማሕሌት ለማስታወስ ሞከረ። "ጡቶቿ ትላልቅ ቢሆኑም ከታች መሰረታቸውን ሰፋ አድርገው ስለሆነ የጣሉት የመውደቅ ስጋት የለባቸውም።የጠይም ቆንጆ ነች..ማዲያት ይወጣባታል ብለህ አትፈራም።መቀመጫዋ ሲያዩት ደስ ይላል..በዛው ልክ ደግሞ ለግሯም እንዳልከበደው ያስታውቃል።ከንፈሯ ከጥርሷ..አይኗ ከቅንድቧ..ፀጉሯ ከራስ ቅሏ..ሁሉ ነገሯ ተመጣጥኖ ነው የተቀመጠው።የፍንዳታ ውበት አይደለም ያላት።ከመስከረም እስከ መስከረም ድረስ የማትረግፍ አበባ ነች።ይቺ አርባ ሲሆናት ከወጣት ሴቶች ጋር ቺት የምታደርግባት አይነት አይደለችም። ሶስት ወልደህባት ብትፈታት ራሱ ካንተ የባሰ ወጣት እንደምታገባብህ ታውቃለህ።ያረጃል አልያም ደግሞ ይባክናል ብለው የማይሰጉለት አስተማማኝ ውበት ነው ያላት።"

ተናግሮ ሲጨርስ ጠበቃው በግርምት እየሳቀ "ዋው! እንደዚህ ደስ የሚል የውበት አገላለፅ ሰምቼ አላውቅም። ታዬኝ ጌታቸው በየቀኑ ሲያገላብጣት!" አለ ተነስቶ ወደ መቀመጫው እየሔደ።
"ስነስርዓት ይኑርህ ጨምላ..!" ቃሉን አንጠልጥሎ ተወው።
"የሚያገላብጣት እያለ እኔ ላይ ነው የምትናደደው?'
"ቢሆንም…"

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

@Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
512 viewsኖኀ መፅሐፍ, edited  03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 22:45:50
መጽሐፍ ጥቆማ
" ለዓለማት እዝነት የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ "
ታሪካዊ ክስተቶች የቀረቡብት ፤ ሁኔታዎች በሰፊው የተተነተኑበት

ዝግጅት፦ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ አሰ-ሶልላቢ
ትርጉም፦አህመድ ሁሴን (አቡ-ቢላል)

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከኢስላምና የዓለማት እዝነት ከሆኑት ነቢይ(ሰ.ዐ.ወ)ጋር ልዩ ትሥሥር አላት፡፡ይህንን መልካም የሆነ ግንኙነትም ላለፉት በርካታ ምዕተ ዓመታት ሙቀቱ ሳይበርድ ጠብቃ ማቆየት ተሳክቶላታል፡፡ይህ በወንድም አህመድ ሁሴን(አቡ ቢላል)የተተረጎመ መጽሐፍ የነቢዩን(ሰ.ዐ.ወ)ታሪክ ከመተንተኑ ባሻገር ስለዚህ ጥልቅ ትስስሮሽ በርካታ ጉዳዮችን ያወሳል።ተርጓሚው ማለፊያ ሥነ-ጽሑፋዊ ቅርስ አበርክቶልናልና ምስጋና ይገባዋል፡፡
ረ/ፕሮፌሰር አደም ካሚል

ይህ ውብ ድርሳን..ምድርን ከረገጡ ፍጡራን ሁሉ የበላይና ምሉዕ ስብዕና ስለነበራቸው ታላቅ ሰው ከውልደት እስከ ህልፈት ይተርካል፡፡ከረዥም እልህ አስጨራሽ ጉዞ በኋላ..የገነቡትን ኢስላማዊ ስልጣኔ፣የዓለምን የታሪክ ሂደት በመቀየር ላይ የተጫወቱትን ሚና፣ ለሰው ልጆች ሁሉ መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ ሕይወት ያበረከቱትን ወደር የለሽ አስተዋጽኦ በተመስጦ ያስቃኛል፡፡በ2ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የዳዕዋ ጉዞ ላይ ጉልህ አሻራውን እያሳረፈ ያለውን ወንድሜን ይህን ታላቅ ስጦታ ስላበረከተልን ላመሰግነው እወዳለሁ፡፡ወንድሜ አቡ ቢላል መልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ)በብዕርህ ስታወድስ..ብዕርህን በመልዕክተኛው(ሰ.ዐ.ወ)እንዳወደስክ ተረዳ!ድንቅ ሥራ! ሁሉም ቤት ውስጥ
ሊገኝ የሚገባው ውብ የኢስላም ቅርስ!!
(ኡስታዝ ያሲን ኑሩ)

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
234 viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 22:31:49
መጽሐፍ ጥቆማ
" ጎቤው "
ትርጉም፦ ጌታነህ አንተነህ
ገጽ፦ 557

" እንጀራ ይወጣልኛል ብሎ ወደሌላ መንደር መሰደድ በባስቲድ ታላቅ ነውር ነው፡፡ እስካሁን እንዲህ በማድረግ መንደሩን ያዋረዱት የሜዴሪክ ልጅና የቴስታር ቤተሰብ ናቸው፡፡ የሜዴሪክ ልጅም ቢሆን፣ ትምህርት ስለነበረውና ማርሴይ ውስጥ የጉምሩክ ሰራተኛ ሆኖ ስለተቀጠረ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት፣ ሰው ኣልተቀየመውም፡፡ የጉምሩክ ሰራተኛ የደንብ ልብስ ስለሚለብስ፣ ማንንም ሰው - ኣቡኑን ሳይቀር - የመፈተሽ መብት ያለው ስለሆነ፣ ስራው የተከበረ ነው፡፡ ይህም ብቻ ኣይደለም፡፡ እሱ ድርቅ፣ ውርጭ፣ በረዶ ፈርቶ እንቅልፍ ኣያጣም፡፡ ኣለመኛ ነው፡፡ ሲያረጅም ምንም ስራ ሳይሰራ ተኝቶ መጦር ይችላል፡፡ እዚህ ባስቲድ ተቀምጦ እንዲህ ያለ ሙያ ለማግኘት እማይቻል ነው፡፡

እነዚያ የቴስታር ቤተሰብ ግን የተሻለ መሬት ኣገኘን ብለው እሌላ መንደር ሄደው መጫር በመጀመራቸው ፣ እትብታቸው የተቀበረበትን መንደር ስም ኣጥፍተዋል፡፡ ክብሩንም ኣጉድፈዋል፡፡ የመንደሩ ሰው ሁላ በነሱ ባድማ በኩል ሲያልፍ ጢቅ! ሳይልበት ኣያልፍም፡፡ ደሞ’ስ እውጭ ኣገር ሄዶ ሃብት፣ ንብረት ማፍራት ምን ዋጋ ኣለው? ከዘመድ ከወዳጅ ጋር ካልተቃመሱት! ደሞ ጎረቤትህ ያንተን ሃብት እያየ በቅናት እርር ሲል ካላየኸው፣ ምን ፋይዳ ኣለው? "
ከመጽሐፉ የተወሰደ
ገፅ 50

TOWER IN THE SKY "  የተሰኘውን የሕይወት ተፈራ " ማማ በሰማይ " በሚል ርዕስ ውብ አርገው የተረጎሙት ጌታነህ አንተነህ 2009 ላይ " ጎቤው " የተሰኘ መጽሐፍ ተርጉመው አሳትመዋል።ሁለት መጽሐፍ በአንድ ነው የያዘ ነው።

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238
 

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
274 viewsኖኀ መፅሐፍ, 19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 20:25:16
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" አሮድዮን "
በሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ

አርድዮን ማለት አሮድን በሚባል ድምፀ መልካም ወፍ በኩል መልአኩ ለቅዱስ ያራፍ ተገልጦ ዜማውን ስለአስተማረው ምሥጢር ስለገለጠለት / ስለዚህ በወፉ በእርድዮን ምክንያት ያሬድ ተብሏል። ይኸውም ድምፁን እንደነሣ ስሙንም ነሥቷል። ማር ይስሐት እንዲህ እንዳለ

አሮድዮን የተባለ ወፍ ሰው ከሚኖርበት ቦታ ተለይቶ በረሃ ሄዶ ሲኖር እንደ ጠቢባን ፈጽሞ ደስ ይለዋል፤ኹለት  ያለው  የዚያ ወፍ ነገር ታወቀ፣ ተነገረ የዜማውን ስልት የሰማ ሁሉ ወደ በረሃ በሚሄድበት ጊዜ እንዲቆም ዜማው ደስ ከማሰኘቱ የተነሣ (አርሱመጅ) የዕፅ ፍሬ ዓይነት ነው) መልቀሙን እስኪተው ድረስ ሰውም መንገዱን እስኪዘነጋ ድረሰ ምግቡን ይተዋል ይሞታል-።

በማለት የአሮድዮን ዜማ ከዚህ ዓለም አኗኗር ለይቶ በተመስጦ ወደ እግዚአብሔር የሚያወጣ ነፍስን የሚማርክ ሥጋዊ መብል መጠጥን የሚያስረሳ ምድራዊ ኑሮን የሚያዘነጋ እንደሆነ ይናገራል። በዚሁ መሠረት የቅዱስ ያሬድም ዜማ እንደዚሁ ነው።
ማር ይስሐቅ ፳፰÷፫

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238
 

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
216 viewsኖኀ መፅሐፍ, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ