2023-04-09 12:17:31
በአንድ ወቅት የከተማዋ ገዢ የሆነው ንጉስ ለሕዝቡ
" የሁላችሁም ጠላት የሆነ ሰው ሞቷል ስለዚህ ለትምህርት እንዲሆናችሁ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ተቀምጦላችኃል ሁላችሁም መጥታችሁ እንድትመለከቱ " የሚል አዋጅ አስነገረ
የሁላችንም ጠላት ሊሆን የቻለው ሰው ማነው ? በሚል ብዙ የከተማው ህዝብ በሬሳው ሳጥን ውስጥ ያለውን ለማየት በመጏጏትና በመገረም ስሜት ወደ ቦታው ሄደ ብዙዎች ባዩት ነገር በመገረም አንዳንዶች ደግሞ ግራ የመጋባት ስሜት ይስተዋልባቸዋል
ህዝቡ በሳጥን ውስጥ ያየው ምን ይመስላችኃል?
በሬሳ ሳጥን ውስጥ የተቀመጠው ሰይጣን አሸባሪ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ ወይም ክፋ ሰው ሳይሆን የራስን መልክ መመልከቻ መስታወት ነበር :: ሁሉም ሰው ጎንበስ ብሎ ጠላቱን ሲፈልግ የሚያገኘው የራሱን ፊት ነበር:: ንጉስ ይህን ያደረገበት ምክንያት ሁሉም ሰው የራሱ ጠላት ራሱ መሆኑን ለማስተማር ስለሆነ ነው::
አንድ ግጥም አለ ገጣሚው ሰለሞን ሞገስ ይባላል እንዲም ይላል
ጠላቴን ስፈልግ ከጎረቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ ከሩቅ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው !!!
ብዙዎቻችን ጠላት በዛብኝ እንጂ ጠላት አብዛሁ አንልም ሰው አይመቸኝም እንጂ አልመቸውም ማለት ይከብደናል የራስን ስህተት ማወቅ ትልቅ መሆኑን አንረዳም
ራሳችንን ስለማንወድ ሌላውን መውደድ ራሳችንን ስለማንቀበል ሌላውን መቀበል ይከብደናል እነዚህ ሁሉ ተግባሮች እራስን መግዛት ታላቁ ግዛት መሆኑን ማሳያ ነው
መደምደሚያ ቻይናዊው ጥበበኛ " ሌሎችን የሚቆጣጠር ጠንካራ ሲሆን ራሱን የሚቆጣጠር ግን ኃያል ነው.... ሌሎችን አውቃለው የሚል ብልጥ ሲሆን ራሱን የሚያውቅ ግን ብልህ ነው" ይለናል
ራሳችንን በመግዛት በራሳችን ላይ እንንገስ
።።።።።።።።ውብ አሁን።።።።።።።
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
634 viewsኖኀ መፅሐፍ, 09:17