2023-04-29 18:26:23
ለመለወጥ የሚያስፈልግህ አዲስ ሃሳብ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ አመለካከት ፣አዲስ ማንነት ፣ እንደወትሮው ያልሆነ አዲስ አካሄድ ፣ ያልተለመደ የአኗኗር ዘይቤ ነው!
አዲስ አስተሳሰብ የመኖር ጉጉትን የሚጨምር ፣ ወደ ደስታ ፣ ወደ እርካታና ወደ መትረፍረፍ የሚያቀርብ ነው።
በአዲስ አስተሳሰብ እና አመለካከት አዲስ የተሻለ ሰው ይኮናል ፤ የስኬት ጉዞ ይፈጥናል ፤ ልዕልናው ይቀርባል ፤ ከፍታው ላይ ይደረሳል ።
አዎ! የማትወደውን ኑሮ የመኖር ግዴታ የለብህም። የመቀየር ሙሉ መብት አለህ!
የማያስደስትህ ስፍራ የመገኘት ግዴታ የለብህም። መቀየር ትችላለህ!
በማትፈልገው ሁኔታ ውስጥ እራስህን የማቆየት ግዴታ የለብህም።
ተነጥለህ መውጣት ትችላለህ!
ዘወትር በማይረባና በማይጠቅም ጉዳይ የመጨነቅ ግዴታ የለብህም።
ሁኔታውን የመቀየር ወይም የመተው ሙሉ መብትና አቅሙ አለህ!
በህይወት ከመኖር በላይ እራስን ለመቀየር ዋስትና የሚሆን ነገር የለም።
ሰው እራሱን ፣ ቤተሰቡን ፣ ሀገሩን ፣ አህጉሩን ፣ ዓለምን የመቀየር ትልቅ አቅም አለው ።
አዎ! አዲስ አስተሳሰብን አትፍራ ፣ ለውጥን አትሽሽ።
ያለህበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የመቀየር ፣ የማስተካከልና የማሳደግ አቅም እንዳለህ እምነት ይኑርህ ።
ከዛሬው ህይወትህ በተሻለ በአዲሱ የለውጥ አስተሳሰብ እና አመለካከት አመርቂ ውጤትን በእራስህ ላይ ትመለከታለህ።
ተጉዘህ የምትደርስበት ፣ ሮጠህ የምታገኘው ግሩም መዳረሻ ይኖርሃል ።
የምታድገው አዲስ አስተሳሰብ እና አመለካከት ሲኖርህ ነው ፤ የምትቀየረው የለውጥ አስተሳሰብ ሲኖርህ ነው ።
ወዳጄ! በአዲስ አስተሳሰብ ተማመን ፣ ወደ ህልምህ እንደሚያደርስህ እመን ፣ በእርሱም ተጓዝ!!!
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
428 viewsኖኀ መፅሐፍ, 15:26