Get Mystery Box with random crypto!

የአልበርት አነስታይን ድንቅ ንግግሮች ~~~~ 1.“ምንም የተለየ ተሰጥኦ የለኝም። በልዩ ጥልቀት | ኖኅ Book Delivery

የአልበርት አነስታይን ድንቅ ንግግሮች
~~~~
1.“ምንም የተለየ ተሰጥኦ የለኝም። በልዩ ጥልቀት የሚንጠኝ ጉጉት ከመያዜ በስተቀር።”

2.“ከሌላው በተለየ ብልህ ኾኜ አይደለም። ግን ውስብስብ ችግሮች ሲገጥሙኝ ብዙ እቆይባቸዋለሁ።”

3.“ምናብ ሁሉም ነገር ነው። ሕይወት ይዛቸው የምትምጣቸው ማራኪ ኹነቶች ቅድመ ምልከታ ማለት ነው። ምናብ ከእውቀትም የበለጠ ኃይል አለው።”

4.‹‹ ስህተት ሠርቶ የማያውቅ ሠው ምንም ነገር ሞክሮ አያውቅም ማለት ነው፡፡ ››

5.‹‹ ሁሉም ሠው ብሩህ ጭንቅላት አለው፡፡ ነገር ግን አሣን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሣ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ››

6.“እብደት ምንድን ነው ብትሉኝ አንድን ነገር ደጋግመው እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው እላችኋለሁ።”

7.ስለወደፊቱ አላስብም። ተጣድፎ መምጣቱ መች ይቀራል!”

8.“በመጀመርያ የጨዋታውን ህግጋት መማር አለብህ። ከዚያ ድግሞ ከማንም በተሻለ መጫወትን ልመድ።”

9.‹‹ ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡ ››

10.‹‹ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር፡፡ ››

(Menur Yassin እንዳጋራው)

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery