Get Mystery Box with random crypto!

መጽሐፍ ጥቆማ ' ሚተራሊዮን ' በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ ጩኸት  ከውጪ ብቻ አይደለም፡፡ ጩኸት | ኖኅ Book Delivery

መጽሐፍ ጥቆማ
" ሚተራሊዮን "
በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ

ጩኸት  ከውጪ ብቻ አይደለም፡፡ ጩኸት ከውስጣችንም አለ፡፡ አንዳንዴ ምንም እንኳን አካባቢያችን ፀጥ ረጭ ሲልም ውስጣችን በጩኸት የተሞላ ከሆነ ሰላምና ጸጥታ አይሰማንም፡፡ እንዲያውም ዝም ባልን ቁጥር አካባቢው ጭር ባለቁጥር የውስጣችን ጩኸት ጎልቶ ይሰማናል፡፡ የውስጥ ጩኸታችንን ላለማዳመጥ የውጪ ጩኸት እንሻለን፡፡ እናም የሚጮህ ሙዚቃ፣ ጫጫታ፣ሁካታ የበዛበት ስፍራ መገኘት እንፈልጋለን፡፡ እኔ ዘመኔን በጩኸትና በሁካታ ነው የኖርኩት ጭር ሲል አልወድም የሚሉት ትውልድ አባል ነኝ፡፡ ሁሉ ነገር እንዲጮህ እንሻለን፡፡ ሚዲያው፣ ቴሌቪዥኑ፣ ሬዲዮው፣ ታምቡሩ ሌላው ቀርቶ ስብከቱ ሁሉ ጩኸት ሆኗል፡፡ በአካባቢያችን የሚጮኸ ብናጣ እንኳን የሚጮህ ታኮ ያለው ጫማ እናደርጋለን፡፡ ቋ….ቋ….ኳ….ኳ…. መጥቻለሁ፣ ደርሻለሁ፣ ሄጃለሁ፣ ወጥቻለሁ ይላል ጫማችን እኛን ተክቶ እየጮኸ!

ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘዙ።
Order the book all over the world with fair price and fast delivery

Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

   @Noahbook7 0939115238

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery