Get Mystery Box with random crypto!

ለውብ ቀን!         መምህሯ ዩሱፍ ከተባለው ተማሪ ወላጅ አባት ጋር በልጁ ጉዳይ ለመምከር | ኖኅ Book Delivery

ለውብ ቀን! 
      
መምህሯ ዩሱፍ ከተባለው ተማሪ ወላጅ አባት ጋር በልጁ ጉዳይ ለመምከር ቀጠሮ ያዘች። አባት በቀጠሮው ሰዓት በትምህርት ቤቱ ተገኘ። መምህርቷም «ልጅህ በትምህርት ክፍለ ጊዜ ተማሪዎችን ያውካል። ትምህርቱን በንቃት አይከታተልም። የትኩረት መሰለብና የመቅበጥበጥ ህመም የሚስተዋልበት ስለሆነ Ritalin የተባለውን መድሃኒት የግድ መውሰድ እንዳለበት ማወቅ አለብህ» አለችው።

መምህርቷ ዩሱፍ የመምህራን ክፍል እየገባ ክኒኑን ከወሰደ በኋላ በተጨማሪም ለርሷ ቡና በማምጣት ትምህርቱን እንዲከታተል አስተያየት አቀረበች። ዩሱፍም ያቀረበችውን አስተያየት ተቀብሎ ለአንድ ወር ያህል የተባለውን ፈጸመ። መምህርቷ የዩሱፍን ወላጅ አባት
ዳግም በመጥራት «ዩሱፍ በትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚያሳየው እንቅስቃሴ ሰከን ብሏል። አስደናቂ የባህሪ ለውጥ አምጥቷል» በማለት አደነቀችው። ወላጅ አባትም የመምህርቷን አድናቆት በመስማቱ ተደሰተ። ወደ ልጁ ዘወር ብሎ በፈገግታ «ከቀድሞ በተሻለ ሁኔታ ላይ እንዳለህ ከመምህርህ መስማት እጅጉን ያስደስታል።ያሳለፍከውን የለውጥ ሂደትና የስኬትህን ሚስጥር እስኪ አጫውተኝ» አለው።

ልጁም « አባቴ ጉዳዩ እጅግ በጣም ቀላል ነው። ሁሌም ወደ መምህራኖቹ ክፍል አመራለሁ። ቡናውንም ለመምህርቷ አቀርባለሁ። ግና
እንድወስድ የታዘዝኩትን መድሂኒት መምህርቷ ከምትጠጣው ቡና ውስጥ እጨምረዋለሁ። ለዚህ ነው መምህሯ ይበልጥ የተረጋጋችና በተገቢው ሁኔታ ማስተማር የጀመረችው»
ብሎት አረፈ።

የመልዕክቱ መቅኔ :- አንዳንዴ እኛ ራሳችን ለውጥ የምንሻ ሆነን እያለ ሌሎች
እንዲለወጡ ወቀሳ ማቅረብ ፋይዳ የለውም - የሚል ነው።

             ውብ ቀን!

"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery