Get Mystery Box with random crypto!

#Psychodynamics 3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ለፈተና በቂ ዝግጅት ስላላደረጉ ለመሸ | ኖኅ Book Delivery

#Psychodynamics

3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ለፈተና በቂ ዝግጅት ስላላደረጉ ለመሸወድ ፈለጉ። በዚህም ምክንያት አንድ መላ ዘየዱ። ራሳቸውን ግሪስ ቀቡና ራሳቸውን በሚገባ በማቆሸሽ ከሌክቸረሩ ፊት በመቅረብ እንዲህ ሲሉ ምክንያታቸውን አቀረቡ፦

ኢንስትራክተር በጣም እናዝናለን፤ ፈተናውን ለመፈተን የማያስችል እንከን ገጥሞናል። ምክንያታቸውን አስከተሉ፦

አንድ ሰርግ ላይ ታድመን ነበር፤ እናም ከፕሮግራሙ በኋላ በመመለስ ላይ እያለን በመንገዳችን ላይ መኪናችን ብልሽት ገጠማት። የመኪናችንን ብልሽት ለመጠገን እንደምትመለከተን በአስቀያሚ ሁኔታ ቆሽሸናል።

#ሌክቸረሩም ከምክንያተቸው በመነሳት ተረዳቸውና ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለፈተና ዝግጅት 3ት ቀን ሰጣቸውና አሰናበታቸው።

ከ3ት ቀን በኋላ ለተዘጋጀላቸው ፈተና በበቂ ሁኔታ አጥንተውና ተዘጋጅተው መጡ።

ሌክቸረሩ አንድ ውሳኔ ወሰነና እንዲህ አደረገ ...

ሶስቱም ተራርቀው የተለያየ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ተማሪዎቹም በጣም ተራርቀው ተቀመጡ፤ የፈተና ወረቀትም ተሰጣቸው። ጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፦

ጥያቄ ቁጥር 1 - ማን ነበር ያገባው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 2 - የት ነበር የሠርግ ፕሮግራሙ የተካሄደው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 3 - መኪናዋ የተበላሸችበት ትክክለኛ ቦታ የት ነው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 4 - የተበላሸችው መኪና ሞዴሏ ምን አይነት ነው ? (25% ማርክ)

ከጥያቄዎቹ መጨረሻም #ማስጠንቀቂያው እንዲህ ይላል - መልሳችሁ የግድ ተመሳሳይ መሆን አለበት !!!
___
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery