Get Mystery Box with random crypto!

ቡርሐን አዲስ እና ቴዎድሮስ ተ/ አረጋይ ቴዎድሮስ፦..ከሁላችንም ነፍስ ደስታን ተነጥቀናል።ቀና ብ | ኖኅ Book Delivery

ቡርሐን አዲስ እና ቴዎድሮስ ተ/ አረጋይ

ቴዎድሮስ፦..ከሁላችንም ነፍስ ደስታን ተነጥቀናል።ቀና ብለን አንሄድም።ምሬት መለያችን ሆኗል።ጥሩ ገቢ ያለው ነጋዴ "ስራ እንዴት"ነው?ስትለው"ምንም አይልም" ነው የሚልህ።አፋችን በረከት የለም።ምስጋና የለም።"ምንም አይልም"ምሬት ነው።ማጉተምተም ነው።እነዚህ ስሜቶች ውስደው የት ያደርሱናል? ምንድ ነው ራሳችንን የምንመክረው?

ቡርሐን፦አንባቢዎቻችን አማኝ ስለሆኑ ከየመጽሐፎቻቸው አንዳንድ ምሳሌ መጥቀስ ብንችል መልካም ነው።ከአዲስ ኪዳን በጣም የምወደው ቆንጆ ጥቅስ አለ።"አዕዋፋት ነገ ምን እንበላለን? ብለው አያስቡም።አበቦችን እዩዋቸው።ምን እንለብሳለን ብለው አያስቡም።ግን በህበረ ቀለማት አሸብርቀው፣ተውበው ታዩዋቸዋላችሁ"ይላል።ነብዩ ሙሐመድ ከተናገሩት ሌላ ጥቅስ ጋር ደግሞ ላያይዝልህ።"ሐብታም ማለት ባለው ነገር የሚብቃቃ ነው።የሰው ልጅ አንደ ሸለቆ ወርቅ ቢሰጠው ሁለተኛው ይጨመርልኝ ይላል።ሐብታም ማለት ባለው የሚብቃቃ ነው"የሚል ሐሳብ ነው።

የተባሉት ሁሌም አይሰሩም ነበር።በረው መስራት እንዳለባቸው ያውቃሉ።ይበራሉ።ዓላማህን እስከፈለከው ድረስ የሚያስፈልግህን አታጣም ነው ጭብጡ።እፅዋትም ውበታችውን በመስጠታቸው ነው የሚራቡት።አበቦች ዘራቸውን መቀጠል የሚችሉት በውበታቸው ነው።መብቃቃት ማለት ያለህንና የሚጎልህን ማሰብ ነው።አንድ ነገር ኢንዲኖረኝ ስፈልግ ለምንድን ነው እንዲኖረኝ የምፈለገው?በዋንኛነት ራሳችንን አጥተነዋል።ራስን መሆን።የራስን አለም መፍጠር፣በራስ ወሰን ልክ ማሰብ።በራስ መደሰትና ደስታ የልብ እንጂ የጭንቅላት አለመሆኑን ማመን ያስፈልጋል።የመኖርን ዋጋ ለማወቅ የምንኖርበት ምክንያት ማወቅ።ይህን ነው ዛሬ ድረስ የማስበው።
ቴዎድሮስ፦ነገስ?

ቡርሐን፦ነገ ላይ ስደርስ ነው መመለስ የምችለው።
ፍልስምና 4

Join us @noahbookdelivery