Get Mystery Box with random crypto!

Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teklu_tilahun — Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
የሰርጥ አድራሻ: @teklu_tilahun
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.25K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 74

2022-07-13 16:05:13
#አባቴ_እንሰሳ_ነው!

አባቴ በፍፁም እራቱን ሳይበላ ወደ መኝታ አይሄድም፡፡ የፈለገው ነገር ቢፈጠር፣ እራቱን ሳይበላ? አይደረግም! እኛ ግን ከቤት ምግብ ከሌለ ባዶ ሆዳችንን ወደ እንቅልፍ እንሸኛለን፡፡ ለሁላችንም የሚበቃ ምግብ ከቤት ከሌለ እናቴ በሆነ እቃ ውስጥ ከእኛ ደብቃ ለአባቴ ታስቀምጥለታለች፡፡ አባቴም እንደመጣ እጁን ይታጠብና እኛን አስቀምጦ ሆዳችን እየጮኸ፣ አይን አይኑን እያየነው ብቻውን ጥርግ አድርጎ ይበላዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ባህሪ ያላቸው እንሰሳት መኖራቸውን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሰው ግን የዚህ አይነት ባህሪ እንዳለው በአባቴ አረጋግጫለሁ፡፡ አንድ ቀን የረሀብ ጠኔ ይዞ ሲያንገላውደኝ አባቴ ደግሞ በዚያ ሰፊ መዳፉ እየጎሰጎሰ ይጎርስ ነበር፤ እጄን ወደ ማዕዱ ሰደድኩ፡፡ አባቴ የማይበላበትን እጁን አመጣና እጄን ከትሪው ጋር አጋጨው፡፡ ደግሞ ደጋግሞ መታኝ፡፡ ዱላው ከረሀቡ ጋር ተደማምሮ እንደ ሰመመን አድርጎኝ ዝም አልኩ፡፡ ማልቀስ አልቻልኩም፡፡ ከፊቱ ተቀምጬ ሲጎርስ ተመለከትኩት፡፡

አይኖቼ ከትሪው አንስቶ በአየር ላይ አንሳፎ ወደ አፉ የሚያስገባውን ምግብ ይከታተሉ ነበር፡፡ አፉን ሲከፍተው ግመል ይመስላል፤ ሲያመነዥክና አፉን ክፍት፣ ግጥም ሲያደርግ የሚወጣው ድምፅ አንዲት የባላገር ሴት በድንጋይ ወፍጮ እህል የምትከካ ይመስል ነበር፡፡ አላምጦ ሲውጥ ጥርሶቹ እርስ በእርሳቸው ሲፋጩ ይሰማሉ፡፡ ምላሱ አሁንም አሁንም ከአንዱ የጉሮሮ ጥግ ወደ ሌላኛው የጉሮሮ ጥግ ይመላለሳሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ከአፉ ተርፈው የሚወጡ ደቃቅ የምግብ ፍርፋሬዎች በከንፈሩ ዳርና ዳር ሲታዩ አሞት አስታውኮ አፉን መጥረግ ያቃተው በሽተኛ እንጂ ጠግቦ እንደዚህ የሆነ ጤነኛ ሰው አይመስልም፡፡

#ማራ መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ

*
ቤተሰብ ይሁኑ

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
3.0K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:40:56
#ለራስህ_ክብር_ስጥ!

ለራሳችን ክብር መስጠት እንዴት እንደምናዳብር በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፣ ባለሞያዎቹ ግን ይህ ነገር የሚጀምረው ገና በለጋ እድሜ ላይ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ልጆቻቸውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚወዷቸው የሚያሳዩ ወላጆች - ራሳቸውን በመሆናቸው ብቻ ልጆቻቸው ቀሪው ሕይወታቸው የሚደግፍ ጤናማ በራስ የመተማመን መሠረት ይገነባሉ።

ባህሪ በመባል የሚታወቀው የሞራልና የስነምግባር መዋቅር የሚወጣውም ከዚህ መሰረት ነው፡፡ ጤናማ የሆነ ራስን ማክበር ከራስ ወዳድነት ጋር መምታታት የለበትም። ራስ ወዳድ ሰው እራሱን የሚወደው ላዩን በሆኑ ምክንያቶች ሲሆን ራሱን የሚያከብር ሰው ግን የሚኮራው ብዙ ደክሞ ባዳበረው ባህሪይ ነው።

ራሳቸውን የሚያከብሩ ሰዎች፣ ራሳቸውን እና ሌሎች ሰዎችን ያደንቃሉ፤ እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ውሳኔ የሚያደርጉ ሲሆኑ፣ ሌሎች የሚነግሯቸውን የሚያደርጉት በነገሩ ሲስማሙ ብቻ ነው፡፡ ዓለምን በተጨባጭ የሚያዩ በመሆናቸው ራሳቸውን የበለጠ አዎንታዊ በሆነና በራስ መተማመን አቅጣጫ ለመቀየር ይገፋፋሉ፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ሰዎችንም እንደራሳቸው ይቀበላሉ፣ በቀላሉ በህይወታቸው ውስጥ ችግሮችን በመፍታት ላይ ማተኮር ይችላሉ፨

እሴቶቻቸው ምን እንደሆኑ ለይተው ያወቁና በእነዚህ እሴቶች መሰረት የሚኖሩ በመሆናቸው ከሰዎች ጋር ያሉ ግንኙነቶቻቸው በፍቅር እና በአክብሮት የተሞሉ ናቸው፡፡ በሌሎች ሰዎች ህይወት ላይ ገንቢ ለውጥ ለማምጣት ጥረት የሚያደርጉ በመሆናቸው፣ የራሳቸውን አስተያየት ሲሰጡም ሆነ የራሳቸው ፍላጎት ለሌሎች ሲናገሩ በእርጋታና በደግነት ነው።

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ

*
ቤተሰብ ይሁኑ https://www.facebook.com/booklandbook/

https://t.me/teklu_tilahun
3.2K views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 19:53:14
#ራስህን_እየገደልክ_ነው

በሰሜን አርክቲክት ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ። በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩን ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል። ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል። በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል።

ደሙ ይጣፍጠዋልና፤ ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል። በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል። ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም። አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፤ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም።

ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል። ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው ... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በሃይልም ህይወታችንን ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው።

#ተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ
3ተኛው ዕትም በገበያ ላይ
*

ቤተሰብ ይሁኑ https://www.facebook.com/booklandbook/

https://t.me/teklu_tilahun
3.5K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:53:22
#ጥቅም_አልባ_ሳጥን

ከመቶ አመታት በፊት በአሜሪካ ምድር የሆነ ታሪክ ነው። ዘላኖቹ ቀይ-ህንዳውያን ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር በተደጋጋሚ ውጊያ ውስጥ ይገቡ ነበር። በአንድ ወቅትም እነዚህ ቀይ ህንዳውያን ከአሜሪካ የጦር ሰፈር አንድ ካዝና ሙሉ ወርቅ ዘረፉ።

ካዝናው የተቆለፈ ነበርና እንዴት መክፈት እንዳለባቸው አላወቁም። በድንጋይ ቀጠቀጡት፣ በመጥረቢያ ለመስበር ሞከሩ፣ ከእሳት ውስጥ ጨመሩት... ሆኖም በምንም መንገድ ሊከፍቱት አልቻሉም። በመጨረሻም ምናልባት ይከፈት ይሆን በማለት ወደ ገደል ወረወሩት። ይህም ካዝናውን አልከፈተላቸውም።

ቀይ ህንዳውያኑ ካዝናው ሸክም ስለሆነባቸው እዛው ጥለውት ሄዱ፤ ኋላ ላይ አሜሪካውያን ወታደሮች ካዝናውን አገኙት። በጥቂት ደቂቃዎችም ካዝናው ላይ ያሉ የኮድ ቁጥሮችን በማሽከርከር ከፈቱት።

ሰዎችም እንደዚሁ ናቸው፤ በእያንዳንዳችን ውስጥ የታመቀ አቅም፤ የታመቀ ወርቅ አለ። ሆኖም ለመክፈት ጥበብን ይጠይቃል። ይህን ጥበብ እሳካላገኙም ድረስ ጥቅም አልባ ሳጥን ብቻ ይሆናሉ....

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍ

*
ቤተሰብ ይሁኑ

Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
3.8K views03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:41:48 #ኢትዮጵያ_ልዩ_ናት

#ሉባር እና ሰርድዮን የተሰኙ ሁለት መጽሀፍት በገበያ ላይ ማዋላችንን በመግለጽ ሀገራችንን ከዓለም ልዩ የሚያደርጋትን የገለጸ ይሸለማል በሚል ማወዳደራችን ይታወቃል፡፡ በውድድሩ አንደኛ የወጣችው ኢትዮጵያን ልዩ የሚያደርጋትን እንደዚህ ገልጻታለች፡፡

#ኢትዮጵያ_ልዩ_ናት

አዎ ኢትዮጲያ ልዪ ናት እንዴት ቢባል ስለኢትዮጲያ መግለፅ ቢከብድም፦አሁን የረር ብለን በምንጠራ ኤረርዐዳም ከገነት በተባረረ ጊዜ መላእክት ያስተማሩትን የሠማይና የምድር ሚስጥራት የህይወት መፅሀፍ (መፅሀፈ ራዚኤልን) በእግዚዐብሄር ፈቃድ በግዕዝ ቋንቋ ፅፎ በዚህ የረር(ኤረር) ተራራዎች ከመሬት በታች በሆነዉ ስዉሩ ስፍራ አኑሮታል ኢትዮጲያም ባለፉት ዘመናት ውስጥ ይህን መፅሀፍ ተጠቅማ ሀያል ሆና ነበር...

ጀርመናዉያንና ሌሎችም የዉጪ ሀገራት የግዕዝ ቋንቋን በየሀገራቸዉ በዲግሪና በማስተርስ ደረጃ የሚያስተምሩት ለጠቅላላ አዉቀት ዐይደለምኮ የቋንቋዎች ሁሉ መጀመሪያ የጥበብ መነሻ መሆኑን ስላወቁ ነዉ...

ጀምስ ብሩስ ፅድቅን ፍለጋኮ ዐይደለም በኢትዮጲያ ገዳማት ለዐመታት ግዕዝ ሲያጠናና ሲባዝን የኖረዉ ትልቁንና የስልጣኔ እንዲሁም የጥበባት ሁሉ ሚስጥራትመከማቻ የሆነዉን ኢትዮጲያ ዉስጥ ብቻ የሚገኘዉን መፅሀፈ ሄኖክን ፍለጋንጂ...

ዛሬ ላይ ምዕራባዉያኑ ከኛ በሠረቁት የጥበብ መፅሀፍት ተጠቅመው የሚሠዉር ልብስ ሰራን ሲሉ ይሰማሉ ይህ ግን ኢትዮጲያን ጠንቅቆ ለሚያዉቃት ብርቅ አይደለም ምክንያቱም የቀደሙት ዐባቶቻችን ዕፀ ልባዊትን ተጠቅመዉ በጦርነት ጊዜ ዐብያተ ክርስቲያናትን፣ ብርሀና መፃህፍታትን እንዲሁም እራሣቸዉን ይሠዉሩ ነበር ይህቺ ዕፀ ልባዊት ዐሁንም ኢትዮጲያ ዉስጥ ትገኛለች።

ገነትን ከሚያጠጡት ዐራቱ ዐፍላጋት መሀል ዐንዱ ጊዮን(ዐባይ) ኢትዮጲያ ዉስጥ ነዉ ሚገኘዉ መየ ህይወት(የህይወት ዉሀም) እዚሁ አከባቢ ሊገኝ እንደሚችል ይገመታል መነሻዉ ጣና ሀይቅም በገዳማቱና በዉስጡ ብዙ ሚስጥራትን ይዞ ዪገኛል...

በዛሬዉ ዘመን በዐዉሮጵላን በዐየር ላይ ሊኬድ ይችላል የቅኔዉ ሰዉ ተዋናይ ግን በጥበብ በደመና ተጭኖ ይጓጓዝ ነበር...

እመቤታችንን በቀራኒዮ በእናትነት ለዐለም ከመሠጠቷ በፊት እኛ ኢትዮጲያዉያን ግን የዐስራት ልጆቿ የመጀመሪያ ለጆቿ ነበርን።

እኛ አዚህ እንጊሊዘኛ ያወራ እንደምሁር ስንቆጥር ምዕራባዉያኑ ግን ግዕዝ በማስተርስ ደረጃ እየተማሩ ቅኔ ሊዘርፉብን ነዉ ምክንያቱም ኢትዮጲያ ብቻ ውስጥ የሚገኘው ግዕዝ የቋንቋ ሁሉ መጀመሪያ የጥበብ መነሻ ስለሆነ ነዉ።

እኛ እዚህ በሠጡን ካልኩሌሽን ስንባዝን እነሱ ግን ከኛ በሠረቁት የጥበብ መፅሀፍት እየተራቀቁ የስልጣኔ ጥግ ላይ ደርሠዋል...

ኢትዮጲያ የሰዉ ልጅ፣የሥልጣኔ የቋንቋ ፣የጥበብ...መጀመሪያ ናት ኢትዮጲያዉያንን ከሌሎች ጋር ለመመሣሠል እንጥራለን እንጂ ኢትዮጲያ ልዩናት...

እጹብ ጌታነህ
143 ላይክ ያገኘች

#ሉባር 3ተኛ ዕትም
#ሰርድዮን አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

*
ቤተሰብ ይሁኑ

Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
3.9K views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:41:46
3.3K views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 06:54:17
#የአእምሮህ_አስደናቂ_ኃይል

የሰው ልጅ አእምሮ የብዙ ዝንባሌዎች እና ብቃቶች ድብልቅ ነው፡፡ በውስጡም ተስፋና ቀቢፀ-ተስፋ፣ መውደድና መጥላት፣ አጥፊነትና አልሚነት፣ ጭካኔ እና ርህራሄ ወዘተ አሉት፡፡ አእምሮ እነዚህን እና ሌሎችንም ብቃቶችን የያዘ ውህድ ነው፡፡ በእርግጥ በእያንዳንዱ አእምሮ ውስጥ ጎልተው የሚወጡት ብቃቶች ከሰው ሰው፣ ከጊዜ ጊዜ እና ከቦታ ቦታ ይለያያሉ፡፡

የአእምሮን አስደናቂ ኃይል መጠቀምን ተማር!

በአንድ አእምሮ ውስጥ ከሚገኙ በርካታ ብቃቶች መካከል የትኛው ገኖ እንደሚመጣ የሚወስነው ያ ሰው የሚኖርበት አካባቢ፣ ስልጠና፣ ትምህርት እና በተለየ ሁኔታ ደግሞ የሰውዬው የራሱ ሃሳቦች ናቸው፡፡

በአእምሮ ውስጥ የተያዘ የትኛውም ሃሳብ ወይም የትኛውም በትኩረት አእምሮ ውስጥ የገባና ወደ ንቁው አእምሮ የተወሰደ ሃሳብ እሱን የሚመስሉትን ሌሎች ሃሳቦችን የመሳብ ተፈጥሮ አለው፡፡

አእምሮ ልክ እንደ ለም መሬት ነው፡፡ የተዘራበትን ነገር አባዝቶና አሳድጎ በአይነት ይሰጣል፡፡ ስለዚህ አእምሮ የትኛውንም አይነት አጥፊ ሃሳብ እንዲይዝ መፍቀድ አደገኛ ነው፡፡ እንደነዚህ አይነት ሃሳቦች ቶሎም ይሁን ዘግይተው አካላዊ መገለጫን ተላብሰው መውጣታቸው አይቀርምና፡፡

#ወርቃማ_ህጎች መጽሐፍ

*
ቤተሰብ ይሁኑ

Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
3.8K views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:55:27
#የፍልስፍና_ሀሁ
እና
#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ

#እውነት_ምንድን_ነው? የሚለው ጥያቄ የምንጊዜም እንቆቅልሽ ጥያቄ ሆኖ ኖሯል፡፡ ከግሪክ እስከ ሮም፣ ከህንድ እስከ ጃፓን፣ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ድረስ በተለያዩ ዘመናት የኖሩ አያሌ ፈላስፎች ይህን ጥያቄ ለመመለስ እድሜያቸውን ሰውተዋል፡፡

ከሰዎች ተለይተው በየዋሻውና በየምኩራቡ እውቀትን ክፉኛ ቢሹም፣ እስካሁን ሁሉንም የሚያስማማ መልስ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይሁንና የሁሉም መልስ ደግሞ ስህተት ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ሁሉም የየራሱ እውነት አለውና፡፡ ፍለጋው አሁንም ቀጥሏል፡፡ ሁለቱም መጽሐፍት #የፍልስፍና_ሀሁ እና #ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ ደግሞ አብረውን እውነትን ይፈልጋሉ፡፡

ፍጥረትና ህይወት ከየት ተገኘ?

የምንኖረው ለምንድን ነው?

የህይወት የመጨረሻው አላማ ምንድን ነው?

ለምን ወደዚህ ምድር መጣን?

ወዴትስ እንሄዳለን?

እነዚህና ሌሎች አያሌ ጥያቄዎች የእውነትን እውነተኛ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ዴስካሬት በፕላቶ መልስ ቢስቅም፣ ሩሶ በስፒኖዛ ፍልስፍና ቢበሳጭም፣ ፓይታጎራውያን በኢፒስኩሮሶች ቢያፌዙም፣ ሁሉም ግን በአንድ ነገር ብቻ ፈጽሞ ይስማማሉ፡፡

#የመጨረሻው_የጥበብ_ፍለጋ ፍልስፍና መሆኑን፡፡

#የፍልስፍና_ሀሁ እና #ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍት ስለ ፍልስፍና አስደናቂና አዝናኝ ጉዞ ይተርካሉ፡፡

ከአቴንስ እስከ ኤፌሶን፣ ከለንደን እስከ ፓሪስ፣ ከንጉስ እስከ ባሪያ በተለያየ ዘመን የኖሩ አለምን የቀየሩ ፈላስፎችን በር ያንኳኳሉ፡፡ መሰረታዊ ፍልስፍናን ማወቅ አለብኝ ለሚልና የኢትዮጵያንና የአለምን ፍልስፍናን ለተጠማ አንባቢ እነዚህ መጽሐፍት ትልቅ ገጸ በረከቶች ናቸው፡፡

#በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች_እጅ_ያገኙታል፡፡

https://t.me/teklu_tilahun
4.0K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:07:24
እንዴት አደራችሁ

እናስተውል...!
ለ90 ሚሊየን ሠው አንድ ፀሐይ ነው እንጂ የምትወጣው ለሁሉም የተለያየ ፀሐይ አይወጣም፡፡ ፀሐይ ስራዋ መውጣት ነው መሞቅ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ አንዳንዶች ፀሐይን በአግባቡ ሞቀዋት ስታይ ለኔ ጨልሞ እንዴት ለነሱ ፀሐይ ሆነ አትበል። እነሱ የተሳካላቸው ከፀሐይዋ አወጣጥ ሳይሆን ከቆሙበት ቦታ መሆኑን ልብ በል፡፡

አዲሷ ፀሐይ አዲስ ዕድል፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ስኬት፣ አዲስ ራዕይ ይዛ በማለዳው ህይወትህን ልታሞቀው ስትወጣ አንተ ዛሬም በትላንት መጥፎ ታሪክህ በእንባ ጥላ ተጠልለህ ከተደበቅካት፤ ሳታሞቅህና አዲስ ዜናዋንም ሳታበስርህ ትገባለች፡፡ ታዲያ ህይወት ምናጠፋች? ተፈጥሮ ሁሌም ለሁሉም እኩል ናት፡፡ ለሁሉም አንድ ፀሐይ ነው የምትወጣው። እስኪ ዛሬ በፍቅር ከመኝታህ ተነስ። የዛሬዋን ፀሐይ በተስፋ ሙቃት፣ አትደበቃት፣ ከውድቀትህ እንቅልፍም እራስህን ቀስቅስ፡፡

ሰናይ ቀን ሄቨን ሲሳይ
@my_life_page

*
ቤተሰብ ይሁኑ

Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
4.4K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:57:12
#ሁለቱ_የችግር_ቀን_ስህተቶች!

ሁላችንም ቢሆን እንደማንኛውም ሰው በጣም አስቸጋሪ በሆነና እጅግ በሚሞግተን ሁኔታ ውስጥ እናልፋለን፡፡ ምናልባት በእድሜያችሁ ገና ወጣት ከሆናችሁና ይህች አለም ለሁላችንም ጊዜዋን እየጠበቀች የምታቀብለንን የሕይወት ውጣውረድ ብዙም ካልቀመሳችሁ፣ በሰው ጥላ ስር ከመኖር ወጣ ብላችሁ የራሳችሁን ውሳኔ እየወሰናችሁ የራሳችሁን ኑሮ መምራት ስትጀምሩ ትደርሱበታላችሁ፡፡

በአሁን ጊዜ ከባድ በሆነ ሁኔታው ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁ፣ እነዚህን ሁለት የችግር ቀን ስህተቶች ከመስራት ራሳችሁን እንድትጠብቁ ልምከራችሁ፡፡

የመጀመሪያው ስህተት አሁን ያለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ በእኛ ላይ ብቻ እንደደረሰ ወይም የእኛ ሁኔታ ከሌለው ለየት ያለና የከፋ እንደሆነ ማሰብ ነው፡፡

አንድን ነገር አንዘንጋ፣ አሁን እኛ በምናልፍበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ከዚህ በፊት አልፈውበታ፣ በማለፍ ላይ ናቸው፣ ወደፊትም ያልፋሉ፡፡ አንዳንዶች ከዚህ ችግር ባነሰ ችግር ደክመው ሲወድቁ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከዚህ ችግር እጅግ በገዘፈ ሁኔታ ውስጥ አልፈው እንኳን በብርታት አሸንፈው ይሄዳሉ፡፡

ሁለተኛው ስህተት አሁን ያለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ በቶሎ የማይበርድ፣ የማያቆምና ረጅም ጊዜ የሚቆይ እንደሆነ የማሰብ ስህተት ነው፡፡

በአንድ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስናልፍ ጊዜው ረጅም እንደሆነ ይሰማናል፡፡ ይህ የተፈጥሮ ሕግና የሰው ባህሪ ነው፡፡ ስለሆነም የምታልፉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ረጅምና የማያልቅ እንደሆነ ከማሰብ መለስ በሉና፣ “ይህም ሁኔታ ያልፋል” የሚልን ተስፋ በመያዝ ወደፊት ተራመዱ፡፡

የችግሩን ክብደትና የጊዜውን ርዝመት በማሰላሰል መጨናነቁን ቀነስ አድርጉትና “አልፈዋለሁ!”፣ “አሳልፈዋለሁ!” ማለትን ልመዱ፡፡

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
4.8K views03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ