Get Mystery Box with random crypto!

#አንተ_እኮ_ውድ_ነህ! ሰዎች ቢያገሉህ ወይም ቦታ ባይሰጡህ አትዘን። ብዙ ሰዎች ውድ ነገሮችን | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#አንተ_እኮ_ውድ_ነህ!

ሰዎች ቢያገሉህ ወይም ቦታ ባይሰጡህ አትዘን። ብዙ ሰዎች ውድ ነገሮችን ባለማወቅ ይንቃሉ፤ ርካሽ ነገሮች ላይም ይሻማሉ።
ሁሉም ነገር በጊዜ ሂደት ያልፋል። ሁሉም ሰው በተለያዬ ሁኔታ፣ ለተወሰነ ጊዜ በህይወትህ ይከሰታል። ስለዚህ በህይወት እውነታ ተደሰት። መንገድህን ቀጥል።

የተወለድከው ከድሃ ቤተሰብ ከሆነ 'እንኳን ደስ ያለህ!' ምክንያቱም ይሄ ቤተሰብህን በጉብዝናህ ሃብታም እንድታደርግ ፈጣሪ የሰጠህ እድል ነው። ቀጣይነት ያለው ሰው ሁን። ነገሮችን በጅምር አታቋርጥ። ለራስህም ይሁን ለቤተሰብህ ለውጥን የምትጽፍ ልዩ ትሆናለህ።

ዋጋ ሳትከፍል ያለመሰዋትነት የምታሳካው ምንም ነገር አይኖርም። መሰዋትነት፣ ችግሮችን መጋፈጥ የህይወት አካል ስለሆነ- እመንበት። ትክክለኛውን ነገር ለማግኘት ተገቢውን ዋጋ እስከ-ከፈልክ ጸጸት ህመም ሆኖ ሰላምህን አይነሳህም።

የሰዎች መሄድ መምጣት ሳይሆን፣ ያ'ንተ መስራት አለመስራት ጥያቄ ሊሆንብህ ግድ ነው።

ልብ በል… አንተ ርካሽ ነገር አይደለህም- አንተ ውድ ነህ!

ምን ያህል ውድና ድንቅ አእምሮ የያዝክ መሆንህን ደግሞ

#ድብቁ_አእምሮህ_ድብቁ_ኃይልህ መጽሐፍ ያሳይሀል፡፡

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?