Get Mystery Box with random crypto!

#አቦ_አትጨናነቅ!! ሰዎችም ሆነ የቲቪ ማስታወቂያዎች የመልካም ሕይወት ቁልፉ አሪፍ ስራ ማግኘ | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#አቦ_አትጨናነቅ!!

ሰዎችም ሆነ የቲቪ ማስታወቂያዎች የመልካም ሕይወት ቁልፉ አሪፍ ስራ ማግኘት፣ ወይም ዘናጭ መኪና ወይም ቆንጆ ሴት ጓደኛ ያለህ መሆን እንደሆነ እንድታምን ይፈልጋሉ፡፡

አለም ያለማቋረጥ የሚነግርህ ነገር፣ የተሻለ የሕይወት መንገድ የሚባለው ብዙ መግዛት፣ ብዙ ማግኘት፣ ብዙ መስራት፣ ብዙ መሆን እንደሆነ ነው፡፡

ስለዚህ ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ስለሁሉም ነገር ግድ እንዲኖርህ በሚነገሩ መልዕክቶች ስለምትጨናነቅ ያለማቋረጥ አዲስ ቲቪ ስለመግዛት፤ የእረፍት ጊዜህን ከስራ ባልደረቦችህ በተሻለ ስለማሳለፍና አዲስ ጌጥ ስለመግዛት የምታስብ ትሆናለህ፡፡

ለምን? የእኔ ግምት ብዙ ነገሮችን ለማግኘት መጨነቅ ለስራ ጥሩ ስለሆነ ነው፡፡ የጥሩ ስራ መኖር ስህተት ባይሆንም ችግሩ ስለ ብዙ ነገሮች መጨነቅ ግን ለአእምሮ ጤንነት መጥፎ መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በማይገባ አይነት የማይረቡና የውሸት ከሆኑ ነገሮች ጋር የተጣበቅክ እንድትሆንና ሕይወትህን ሙሉ የማይጨበጥ ደስታና እርካታ ስታሳድድ እንድትኖር ያደርግሃል፡፡

የመልካም ሕይወት ቁልፍ ስለ ብዙ ነገሮች መጨነቅ ሳይሆን፣ ስለ ትንሽ ለዚያውም እውነት፣ አስቸኳይና አስፈላጊ ስለሆነው ብቻ መጨነቅ ነው፡፡

#በጥበብ_መኖር መጽሐፍ
#The_subtle_art_of_not_giving_a...

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?