Get Mystery Box with random crypto!

#ዓለም_እንደምታያት_ናት! ከተፈጥሮ በስተቀር ከአንተ በላይ የሆነ ምንም ኃይል አጋጥሞህ አያውቅም | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#ዓለም_እንደምታያት_ናት!

ከተፈጥሮ በስተቀር ከአንተ በላይ የሆነ ምንም ኃይል አጋጥሞህ አያውቅም፡፡

በከፍተኛ ጉልበት የሚነፍሰውን ነፋስ ያስጀመርከው አንተ አይደለህም፡፡ ተፈጥረህ ተገኘህ እንጂ ራስህንም የፈጠርከው አንተ አይደለህም፡፡ ከአንተ በላይ ያለ ኃይል ወይም የሆነ ነገር ባይኖር ኖሮ ምንም ነገር ሊከሰት አይችልም ነበር፡፡

አንተን የፈጠረህ ነገር ምን እንደሆነ ስለማታውቅ፥ ቀጥሎ የምትለው ነገር የሰራኝ ፈጣሪ መሆን አለበት ነው፡፡

ፈጣሪ የመጣው ከየት ነው?

አንተ ሰው ስለሆንክ፥ ፈጣሪ በሰው መልክ የተሰራ ትልቅ አካል እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ጎሽ ብትሆን ኖሮ ደግሞ፥ ፈጣሪ በጎሽ መልክ የተሰራ ትልቅ አካል እንደሆነ ታስብ ነበር፡፡ ስለ ፈጣሪ ያለህ አመለካከት በሙሉ የመጣው ስለ ማንነትህ ካለህ ውስን ተሞክሮና ውስን ምናብ ነው፡፡

በሰው መልክ ስለተሰራህ፥ ፈጣሪ የሰው መልክ የያዘ ትልቅ አካል እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ስለዚህ ፈጣሪ ወይም ኃይል ብለህ የምትጠራው የትኛውም ነገር አንተ ወይ የምታስበው አለዚያም የምታልመው በአእምሮህ ውስጥ ብቻ ያለ ነገር ነው፡፡ በእውነት መለማመድ የምትችለው ብቸኛው ነገር በውስጥህ ያለውን ነው፡፡ በውስጥህ ያለውን ደግሞ በጥልቀት አይተኸው አታውቅም፡፡

እስካሁን የምታውቃቸውን ነገሮች የተለማመድካቸው በአምስቱ የስሜት ህዋሳት የተወሰኑ ናቸው፡፡

አለምንም ይሁን ራስህን በተመለከተ እስካሁን የምታውቃቸው ነገሮች ሁሉ፥ የመጡት በማየት፥ በመስማት፥ በመንካት፥ በመቅመስና በማሽተት ብቻ ነው፡፡

እነዚህ ስሜት ህዋሳት ባይሰሩ፥ አለምንም ሆነ ራስህን አታውቅም ነበር፡፡

የስሜት ህዋሳት ሁሉንም ነገሮች የሚነግሩን ከሌላ ነገር ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ ለምሳሌ ብረት ብትነካና ቅዝቃዜ ቢሰማህ የሰውነትህ ሙቀት ከብረቱ ሙቀት መጠን የበለጠ ስለሆነ ነው፡፡ የሰውነትህን ሙቀት ከብረቱ ሙቀት እጅግ ያነሰ ብታደርገው ብረቱ ሞቃት እንደሆነ ይሰማሃል፡፡ ስለዚህ ይህ የምትተማመንበት ልምምድ ሳይሆን በአካላዊ እውነታ ውስጥ ለመኖር ብቻ በቂ የሆነ ልምምድ ነው፡፡

በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ግንዛቤዎች ምንም አይነት ተሞክሮ ቢኖርህ፥ ያ ተሞክሮ በዚህ ህልውና ውስጥ ለመኖር ብቻ በቂ የሆነ ልምድ ነው፡፡

#የሕይወት_ኬሚስትሪ መጽሐፍ #2ተኛው ዕትም በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?