Get Mystery Box with random crypto!

#ምርጥ_10_አባባሎች #አንድ 'እናንተ የእጣ ፈንታችሁ ጌታ ናችሁ። የራሳችሁን አካባቢ የመቀየ | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#ምርጥ_10_አባባሎች

#አንድ "እናንተ የእጣ ፈንታችሁ ጌታ ናችሁ። የራሳችሁን አካባቢ የመቀየር፣ የመምራት እና የመቆጣጠር አቅም አላችሁ።"

#ሁለት "ሀሳብህን በአንድ የተወሰነ ግብ ላይ አኑር፤ ያኔ ዓለም አንተን ለማሳለፍ ምን ያህል በፍጥነት ገለል ብሎ እንደሚቆም ትመለከታለህ።"

#ሶስት "ቆራጥነትን ለማዳበር መንገዱ ካለህበት መጀመር ነው።"

#አራት "ጥንካሬ እና እድገት የሚመጣው ቀጣይነት ባለው ጥረት እና ትግል ብቻ ነው። "

#አምስት "የስኬቶቻችሁ ከፍታ ብቸኛው ገደብ የህልሞቻችሁ ትልቅነት እና ለእነሱ ጠንክሮ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ነው።"

#ስድስት "አስታውሱ! በህይወት ከፍ ያለ ነገር ለማለም እና የተትረፈረፈ ህይወትን ለመጠየቅ፤ መከራን እና ድህነትን ከመቀበል የበለጠ ጥረት አያስፈልግም።"

#ሰባት "አብዛኞቹ ሰዎች ሽንፈት የሚያጋጥማቸው ፤ አዳዲስ እቅዶችን ለማቀድ ጽናት ስለማይኖራቸው ነው።"

#ስምንት "ራስህን ካላሸነፍክ በራስህ ትሸነፋለህ።"

#ዘጠኝ "የሁሉም ስኬት መነሻ ነጥብ ግልጽ የሆነ የህይወት ዓላማ መኖር ነው።"

#አስር "ራእዮቻችሁን እና ህልሞቻችሁን የነፍሳችሁ ልጆች፣ የመጨረሻ የስኬቶቻችሁ ንድፍ እንደሆኑ አድርጋችሁ ተንከባከቡ። "

#አስበህ_ሀብታም_ሁን መጽሐፍ #8ተኛው ዕትም በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?