Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-12-24 08:32:25 የአብን ዳግም ልደት!
*
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጅግ ዘግይቶም ቢሆን የወሰነው ውሳኔ ንቅናቄያችንን የሚታደግና ወደ ትክክለኛው መስመር የመለሰ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በዚህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት አብን ወደ መስራች ጉባዔው ውሳኔዎች በመመለስ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ 1162/2011 የሚጠይቀውን ፎርማሊቲ ለማሟላት አዲስ ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠራ ይሆናል።

የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በተለይም በየደረጃው ላሉ ለውጥ ናፋቂ የንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ፓርቲውን ወደፊት በማስቀጠል ለአገርና ሕዝብ የሚያደርገውን ትግል በአዲስ ተስፋ እና በጽኑ ቁርጠኝነት እንዲነሳሱ የሚያስችል ነው።
4.1K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 16:11:35 የአገር መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረበት አንገር ጉትን 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኪረሙ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ላይ ንፁኃን ዜጎች የአማራ ማንነታቸው ተለይቶ ጭፍጨፋ እየተፈፀመባቸው መሆኑን መረጃዎች ደርሰውናል።

የፌዴራሉ መንግስት አመራሮችና የአገር መከላከያ ሰራዊት አዛዦች በአማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጅምላ ጭፍጨፋ እንዲያስቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ።
4.9K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 21:12:01 በርካታ ወገኖች ከሰሞኑ በተለቀቀው የአብን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ቪዲዮ ዙሪያ ጥያቄዎችን በልዩ ልዩ መልኩ አቅርባችሁልኛል። ለያንዳንዳችሁ በተናጠል ምላሽ ለመስጠት ጊዜን የሚወስድ ሆኖ ስላገኘሁት ጥቅል ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።

የቪዲዮው በሚዲያ መዋል ተገቢነት፦

ከጠቅላላ ጉባዔ ውጭ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ቀረፃ ሲሰራለት እስከማስታውሰው ድረስ ይሄ የመጀመሪያው ነው። መቀረጹ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ለሕዝብ ይፋ ይሁንና በሚዲያ ይተላለፍ የሚለው ጉዳይ ግን የማዕከላዊ ኮሚቴውን ፈቃድና ይሁንታን የሚጠይቅ ነው። ይህ ደግሞ እንዳልሆነ ፍፁም እርግጠኛ ነኝ። ይተላለፍ ቢባል እንኳን ሙሉው ወይንም የተቆረጠ ካለም ይኸው ይዘት በማዕከላዊ ኮሚቴ ቀርቦ መጽደቅ ይጠበቅበት ነበር። የሚተላለፍበትን ሚዲያም የመምረጥ ኃላፊነቱ እንዲሁ ለግለሰቦች ነፃ ውሳኔ የተተወ አልነበረም።

(ለአማራዊ ክብር ብለን እንጂ እንዲተላለፍ ይሁንታን ባልሰጠንበት፤ በስብሰባው ፈቃድ ተሰጥቶት ቀረፃ ያላከናወነ ሚዲያም ተገቢውን ቅጣት ማስቀጣት ይቻል ነበር። የድርጅትን የጋራ ንብረት ለግል ጥቅም ማዋል ኃላፊነትን በአግባቡ ያለመወጣት ነውር ነው። በመንግስታዊ ተቋም ቢሆን በሙስና ወንጀል ያስቀጣል። የአብን ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በሥራ ላይ ቢሆን ኖሮ በሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ላይ እርምጃ ይወስድ ነበር።)

ከሥልጣን ስለመልቀቅ ስለቀረበው ሞሽን፦ ሞሽኑን ያቀረቡት ሊቀመንበሩ ናቸው። የቀረበው ሞሽን እርሳቸውን ጨምሮ አብንን በሥራ አስፈፃሚነት የመሩ ግለሰቦች ከኃላፊነት እንዲወርዱ ነው። አንድ ሊቀመንበር ራሱን ከኃላፊነት ለማንሳት ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል። አዲስ ሊቀመንበር ሲመረጥ የራሱን ካቢኔ ያዋቅራል። ነባር አዲስ ሳይል ማዕከላዊ ኮሚቴው እስካፀደቀለት ድረስ እጩዎችን ማቅረብ መብቱ ነው። ይህን መብት መልቀቅ የሚፈልግ ተሰናባች ሊቀመንበር በሞሽን ሊገድብ አይገባም። ደንባችንም ማንኛውም አባል የመምረጥ መመረጥ መብት አለው የሚል ድንጋጌ አለው። ሊቀመንበሩ ከ2 ዙር በላይ አይመረጥም ከሚለው ውጭ ገደብ አላስቀመጠም። ስለሆነም የቀረበው ሞሽን ኢደንባዊ ነው ብዬ ሞግቻለሁ። ሆኖም በእለቱ የተሰበሰቡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሞሽኑን ሲደግፉት ብቻዬን ተቃውሜዋለሁ። በአብላጫ ድምጽ የፀደቀው ሞሽን ቀጣዩ ተግባር የነበረው አዲስ ሊቀመንበር መምረጥ ነበር። ይሁንና ሞሽኑን በጀርባ የተውኔት ልምምድ ይዘው የቀረቡ ግለሰቦች በሚመረጠው አዲስ ሊቀመንበር ማንነት ላይ መስማማት አልቻሉም ነበር። በዚህ ምክንያትም 31 ለ 1 በሆነ ፍፁም አብላጫ ድምጽ የፀደቀው ውሳኔ ተሽሮ እስከጉባዔ ድረስ የነበረው አመራር እንዲቀጥል በሁለት ዙር አስቂኝ ድራማ ተወሰነ። ዜናው በመንግስት ሚዲያዎች ጭምር ውሳኔውን ወስነን ከመቋጨታችን በፊት በሰበር ዜና ተዳረሰ። ሰበር ዜናውንና ድራማውን ባልወደውም በውሳኔው ግን ደስተኛ ነበርሁ።

ለምን ተደሰትሁ?

ባለፉት ዓመታት በጉልህ ሲነሱ ከነበሩ ቅሬታዎች አንዱ የድርጅቱ ላእላይ መዋቅሮች (ሥራ አስፈፃሚ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን) አካታችነት ይጎላቸዋል የሚለው ነው። አካታችነት ከአካባቢ፣ ከእምነት፣ ከፆታና አካል ጉዳተኝነትን ጨምሮ ልዩ ፍላጎቶችን ታሳቢ ያደረገ፤ በተጨባጭ የነበሩ ክፍተቶችን መሙላት የሚችል የአመራር ሪፎርም እንዲደረግ በእጅጉ እፈልግ ነበር። ይህ ደግሞ ሞሽኑ ተቀባይነት አግኝቶ ከነባሩ የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር ቢዋቀር ኖሮ ተግባራዊ አይሆንም ነበር።

ሞሽኑ በመውደቁ በዋነኝነት የተደሰትሁት ግን አሁን ያለው ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ሥራ አስፈፃሚና የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን በየደረጃው ያለው የአብን መዋቅር እና የመዋቅሩ ወኪል የሆነው የጠቅላላ ጉባያተኛ ፍላጎት የማያሟላ፣ ድርጅቱ በቀጣይ አገራችንና ሕዝባችን ከሚፈልጉት ትግል አኳያ አዳዲስ ፊቶችንና አቅሞችን የሚፈልግ በመሆኑ፤ ከምንም በላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ከእከከኝ ልከክልህ ጠበባ ሰርክል በመውጣት በውድድር በጉባኤው በቀጥታ እንዲመረጡ እፈልግ ስለነበረ ነው። ማዕከላዊ ኮሚቴውም መዋቅራዊ ውክልና ኖሮት እንዳዲስ እንዲመረጥ፤ በአዲስ ከሚመረጠው ማዕከላዊ ኮሚቴ በመዋቅሩ የታመነባቸው ብቃቱ ያላቸው የሥራ አስፈፃሚዎች እንዲመረጡ በብርቱ እፈልጋለሁ። ይህን ደግሞ የድራማው ደራሲዎች አይፈልጉትም። ምክንያቱም ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለመምጣት መዋቅራዊ ውክልና ያስፈልጋቸዋል። መዋቅሩ እንደማይወክላቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ። ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ለመሆን የጉባያተኛውን አብላጫ ድምጽ ማግኘት ግድ ይላቸዋል። ይህ ደግሞ በመርፌ ቀዳዳ መሽሎክ ሆኖባቸው ጉባኤ እስከመበተንና ጉባያተኛን «መንጋ» ብለው እስከመዝለፍ አድርሷቸዋል። የጠቅላላ ጉባኤ መጥራት በኤርታሌ ላይ በባዶ እግር የመራመድ ያህል ያስጨነቃቸውም ይኸው ነው። ይህ ፍርሃታቸው ጉባያተኛን እስከማሳሰርና በዲስፕሊን ክስ ሽፋን እስከማገድ አወላክፏቸዋል። የምንታገለው የጭቆና ሥርዓት እንኳን ያልደፈራቸውን ነውሮች ሁሉ ፈጽመዋል። መዋቅራችን ግን በፍፁም ጽናት፣ አስተውሎትና ታጋሽነት የጉባዔውን እለት ዛሬም በመጠባበቅ ላይ ነው።

ምን ፍለጋ ቪዲዮው ተለቀቀ?

በመንግስት ሚዲያዎች በሰበር ዜና የተለቀቀውን አስታወሳችሁት? አዎ፥ መልቀቅ ፈልገን አላስለቅቅ አሉን የተባለውን አስቂኝ ተውኔት በምልሰት ለመተወን ነው።

የድርጅት ውስጠ ፓርቲ ጉዳዮች ያላነሳኋቸው በተለይ ከኦዲት ጋር የተገናኙ በአስረጂ ሰነዶች የተደገፉ ወሳኝ ነጥቦች አሉ። ጠቅላላ ጉባዔውን እንደጌታ ምጽኣት የናፈቅሁትም ይኸንኑ ለድርጅት የመጨረሻ የሥልጣን አካል በማቅረብ ተገቢው ውሳኔ እንዲያርፍበት ከልብ በመሻት ነው።

በዚሁ አጋጣሚ መላው የአብን አባላት፣ መዋቅራችንና ደጋፊዎቻችን እስካሁን ላደረጋችሁት በወርቅ ቀለም የሚከተብ የተጋድሎ ታሪክ እጅጉን አመሰግናችኋለሁ። የእናንተ ትውልድ አካል በመሆኔም ኩራቴ የትየለሌ ነው። ተጋድሏችሁ ለፍሬ እንዲበቃም በጽኑ እመኛለሁ!
1.5K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 18:03:17 ኢትዮጵያ የድንቅ ምድር፥ መሪዎች ስለመንደር ዘምሩ ብለው ሲያስገድዷቸው፤ እምቦቃቅላዎች እምቢኝ የምንዘምረው ስለሀገር ነው ይላሉ። የነገ ተስፋችን ስለመንደር ከቆሙ «ታላላቆች» ይልቅ ስለሀገር ከቆሙ እምቦቃቅላዎች መዳፎች ላይ ነው።
2.6K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 15:38:24 የብልጽግና ባለሥልጣናት በወለጋ በአማራ ላይ የሚፈጽሙትንና የሚያስፈጽሙትን የዘር ፍጅት በ«ጽንፈኛ ፋኖ» ተረክ መሸፋፈን አይቻላቸውም። ይዘገይ ካልሆነ በስተቀር ከወንጀል ተጠያቂነትም አያመልጡም።

(ባለፉት ዓመታት ወለጋ በፌዴራል መንግስት ኮማንድ ፖስት ስር ያለ መሆኑን ሁሉም በቁምነገር እንዲመዘግበው ማስታዎስ እፈልጋለሁ።)
1.8K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 17:42:49 የአማራ ሕዝብ ከዚህ የከፋ ታሪካዊ ውርደት አላጋጠመውም፤ ለወደፊቱም ያጋጥመዋል ብለን አንገምትም። ባለፉት 50 ዓመታት በአጠቃላይ እና ባለፉት 4 ዓመታት በተለይ የተፈፀሙት ጅምላ ጭፍጨፋዎች በሙሉ በመንግስት ቸልታና ፍላጎት ማጣት፤ ብሎም በየደረጃው ባሉ የመንግስት አመራሮች ተሳትፎ ጭምር የተፈፀሙ መሆናቸውን የሰብአዊ መብቶች ያወጧቸው ሪፖርቶች ሳይቀር ያረጋገጡት እውነታ ነው። ይኽ በመሆኑም የኅልውና ትግሉን አስከፊና ከባድ አድርጎታል። ሕዝባችንን ከጅምላ እልቂት የሚታደግ ሦስተኛ ወገን እንደሌለ በመገንዘብ አማራ የሆነ ሁሉ ከዚህ አስከፊ ውርደት ለመውጣት የሚጠበቅበትን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል። ክብሩን ለመቀዳጀት የማይታገል ሕዝብ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ በየቀኑ መዋረድና በኃፍረት መሸማቀቅ እጣፈንታው ይሆናል።
1.4K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 16:20:56 በወለጋ በአማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ፍጅት አስመልክቶ ለሚመለከታቸው ሁሉ መረጃ ብናደርስም አንዳችም የተግባር እርምጃ ባለመወሰዱ፤ በተለይም የአገር መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የሚመለከታቸው የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት እና የፖለቲካ አመራሮች በቸልታ በማየታቸው ጭምር በሕዝባችን ላይ እስከዛሬ ከተፈፀሙት ጭፍጨፋዎች ሁሉ አስከፊው ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት ይገኛል።

የፌዴራሉ መንግስት ኮማንድ ፖስት አዋቅሮ በሚመራው የወለጋ አካባቢ በአማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለው ፍጅት እንዲቆም መላው ሕዝባችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራትና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጥሪ አቀርባለሁ።
2.6K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 07:10:02 ቅን እንሁን!
****
ቅንነት ብዙ መጥፎ ነገሮችን ወደ በጎ የመቀየር አቅም አለው። ቅንነት ጦርነትን ወደ ሰላም፤ መውደቅን ወደ መነሳት፤ ማጣትን ወደ ማግኘት፤ ሽንፈትን ወደ ድል፣…የመቀየር ሙሉ አቅም አለው። ሌላው ቀርቶ ቅንነት ጠላትን ወደ ወዳጅ የመቀየር ልዩ አቅም አለው። ቅንነት የማንወዳቸው ቢሆን እንኳ በቂ ጊዜ ሰጥቶ ከማዳመጥ ይጀምራል።

ቅንነት ራሳችንን በሌሎች ቦታ በማስቀመጥ ስለነገሮች መረዳትን ይጠይቃል። ቅንነት ከግል እውነትና እምነት ይልቅ ለጋራ እምነትና የጋራ እውነት ይወግናል። ቅንነት ብዙ ዓይነትነትን ተፈጥሯዊ ፀጋ እንጂ ስጋትን ያዘለ የመለያየት እጣ እንዳልሆነ መተማመኛ ይሰጠናል። የሀሳብ መለያየት ወደ ጥላቻና አለመግባባት የሚያመራው ቅንነት ሲጓደል ብቻ ነው።

ቅንነት የአንድነት እርሾን ይጥላል። ቅንነት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል። ቅንነት የሻከረውን ያለሰልሳል፤ የደረቀውን ያለመልማል፤ የራቀውንም ያቀርባል። ከምንም በላይ ቅንነት የልብ ውስጣዊ ደስታንና ኅሊናዊ እርካታን ያጎናጽፋል። ሳንሰለች ቅን እንሁን!
1.8K viewsedited  04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 15:39:15
እነአርበኛ ዘመነ ካሴን በተመለከተ የሽምግልና ቡድኑ የደረሰበት ውሳኔ፤
3.5K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 16:34:04 የፌዴራል መንግስት በቁጥጥር ስር አውሏቸው የነበሩ ጋዜጠኞችን ከእስር መልቀቁ መልካም ነገር ነው። በቀጣይም በልዩ ልዩ ፖለቲካዊ ምክንያቶች በክልሎችና በአዲስ አበባ በእስር ላይ የሚገኙ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ከእስር እንደሚለቀቁ ተስፋ አደርጋለሁ።

ከእስር ለተለቀቃችሁና ለቤተሰቦቻችሁ በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ!
3.8K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ