Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ሕዝብ ከዚህ የከፋ ታሪካዊ ውርደት አላጋጠመውም፤ ለወደፊቱም ያጋጥመዋል ብለን አንገምትም። | Christian Tadele Tsegaye

የአማራ ሕዝብ ከዚህ የከፋ ታሪካዊ ውርደት አላጋጠመውም፤ ለወደፊቱም ያጋጥመዋል ብለን አንገምትም። ባለፉት 50 ዓመታት በአጠቃላይ እና ባለፉት 4 ዓመታት በተለይ የተፈፀሙት ጅምላ ጭፍጨፋዎች በሙሉ በመንግስት ቸልታና ፍላጎት ማጣት፤ ብሎም በየደረጃው ባሉ የመንግስት አመራሮች ተሳትፎ ጭምር የተፈፀሙ መሆናቸውን የሰብአዊ መብቶች ያወጧቸው ሪፖርቶች ሳይቀር ያረጋገጡት እውነታ ነው። ይኽ በመሆኑም የኅልውና ትግሉን አስከፊና ከባድ አድርጎታል። ሕዝባችንን ከጅምላ እልቂት የሚታደግ ሦስተኛ ወገን እንደሌለ በመገንዘብ አማራ የሆነ ሁሉ ከዚህ አስከፊ ውርደት ለመውጣት የሚጠበቅበትን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል። ክብሩን ለመቀዳጀት የማይታገል ሕዝብ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ በየቀኑ መዋረድና በኃፍረት መሸማቀቅ እጣፈንታው ይሆናል።