Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-13 08:58:40 Emailing Executive Summary - Ethiopia Annual Human Rights Situation Report (June 2022 – June 2023).pdf
6.2K views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 08:58:17 English Version of THE ANNUAL HUMAN RIGHTS SITUATION REPORT of the Ethiopian Human Rights Commission (Executive Summary)
6.2K views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 08:36:25 [በኢትዮጵያ ያለው] የሕግ የበላይነት እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ የላላ [ነው]።

~ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ፒኤችዲ)
****
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በያመቱ የሚያወጣውን የተጠቃለለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ሐምሌ 05/2015 ዓ/ም ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ሪፖርታቸውን በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዲያቀርቡ በሕግ ከተደነገገላቸው የዴሞክራሲ ተቋማት አንዱ ቢሆንም እሰከከዛሬ ድረስ ዓመታዊ ሪፖርቱን እንዲያቀርብ በምክርቤቱ ሁኔታዎች አልተመቻቹለትም። (ሌሎች በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዓመታዊ ሪፖርታቸውን ማቅረብ ያለባቸው አካላት እንባ ጠባቂ፣ ጠቅላይ ፍርድቤት፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ዋና ኦዲተር ይገኙበታል። ከዋና ኦዲተር በስተቀር አንዳቸውም ሪፖርታቸውን እያቀርቡ አይደለም። ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ብናቀርብም እስካሁን አዎንታዊ ምላሽ አላገኝንም።)

ገዥው ፓርቲ መንግስታዊ ሥልጣኑንና ሕግጋትን ለሥልጣኑ ማደላደያነት በመጠቀም መብት ጠያቂዎችንና ተቺዎችን ከሕግ ውጭ የማሰር፣ የመግደል፣ የመሰወር እና ሌሎችንም ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን እየፈፀመ ስለመሆኑ በምክርቤት ልዩ ልዩ አብነቶችን በማቅረብና በማስረጃ በማስደገፍ ጭምር ስንሞግት ነበር። በእንደራሴነት የምናቀርባቸውን ኃቀኛ አስተያየቶች በመቀበል አሰራሩን እና አመራሩን ከማስተካከል ይልቅ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎች በሰላማዊ ሰልፍ ለመደበቅ ሲታትር የባጀው ገዥው የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሚያወጣቸውን ሪፖርቶችም «የጽንፈኞች ክስ ነው በሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኩል የወጣው» የሚል አቋም ስለመውሰዱ የቀደሙ የውስጥ ለውስጥ ውይይቶች አረጋግጠዋል።

ይሁንና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ፒኤችዲ) ኮሚኑ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ባስተላለፉት ቁልፍ መልእክት ውስጥ፤

1/ በሕግ የተደነገገውን አሠራር በቂ ባልሆነ ምክንያት ወደ ጎን በመተው ከሕግ ውጪ የሚፈጸሙ አሠራሮች፣ ድርጊቶች ወይም ሂደቶች፣

2/ በሕግ የተደነገገውን በማስፈጸም ሂደት ተገቢውን የተሳትፎ፣ የምክክር እና የጥሞና ጊዜ ሳይወስዱ ለማስፈጸም መሞከር፣

3/ ተቋማት በሕግ ከተሰጣቸው ሥልጣን ወሰን ውጪ/በመተላለፍ አልያም ከወሰኑ በታች/ሥልጣን እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት እንዲሁም

4/ የተጠያቂነት አለመኖር (impunity)

የሕግ የበላይነት ላለመኖሩ እርስ በእርሳቸው ተመጋጋቢ የሆኑ ምክንያቶች እና አመላካቾች መሆናቸውን አጽንዖት ሰጥተዋል።

በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል በሰው ልጆች ላይ ሁሉ የሚፈፀም ወንጀል በመሆኑ ሁላችንም ገዥው የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥና ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን ሁላችንም ልንተጋ ይገባል።
6.7K views05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-12 20:42:26 Emailing የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት (ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም.).pdf
8.4K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-12 20:41:13 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የ2015 ዓ/ም ዓመታዊ ሪፖርት።
7.6K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:38:43
13.4K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:38:31 9.  በአገራችን የተጀመሩ ልዩ ልዩ ኘሮጀክቶች ፍትኃዊነት፣ እኩል ተጠቃሚነትና ሁሉን-አቀፍ ተደራሽነትን ባረጋገጠ መልኩ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተገቢውን ቁጥጥር እንዲያደርግ እና ትኩረት  እንዲሰጥ ቋሚ ኮሚቴው ያሳስባል፡፡ የተከበረው ምክርቤት እና በስሩ ያቋቋማቸው ቋሚ ኮሚቴዎችም ተገቢውን የቁጥጥር ሥራ እንዲሰሩ ቋሚ ኮሚቴው ይጠይቃል፡፡

10.   አንዳንድ ኘሮጀክቶች ያለቅድመ አዋጭነት ጥናት እና የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ወደ ሥራ በመግባታቸው የኢኮኖሚ አዋጭነት እና  የአፈፃፀም መጓተት ችግሮች እየፈጠሩ ስለመሆናቸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ ስለሆነም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የመንግሥት ኘሮጀክቶችን አቅዶ እንዲንቀሳቀስ ቋሚ ኮሚቴያችን ያሳስባል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በስሩ ባቋቋማቸው ቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ኘሮጀክቶች በስትራቴጂክ እቅድ ተይዘው እና በበቂ ጥናት ተደግፈው ወደ ሥራ መግባታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡

ማጠቃለያ

በ2014 ዓ.ም የተከበረው ምክር ቤት የ2013/14 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርትን ባዳመጠበት ወቅት ቋሚ ኮሚቴያችን ባቀረበው የማጠቃለያ አስተያየት መሠረት በፌዴራል ዋና ኦዲተር በሚቀርቡ ተከታታይ ሪፖርቶች በአንድ የምርጫ ዘመን ለ3 ጊዜ አስተያየት መስጠት ያልተቻለባቸው መስሪያ ቤቶችን እና የጎላ ችግር ያለባቸው ሆነው በመገኘታቸው ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት የተሰጠባቸውን መስሪያ ቤቶች በኃላፊነት የመሩ የሥራ ኃላፊዎች ለመንግሥት የሥራ ኃላፊነት የማያበቃ ገዳቢ ሆኖ እንዲያዝ የሚል ሐሣብ አቅርበን የተከበረው ምክር ቤትም በሙሉ ድምጽ የተቀበለው እና ያፀደቀው በመሆኑ፣ ይህንኑ የምክር ቤቱ ውሣኔ የሕግ መሠረት ለማስያዝ፣ በምክር ቤቱ እና በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ለሚፀድቁ ሹመቶች የመመዘኛ መስፈርት ደንብ ውስጥ እንዲካተት ቋሚ ኮሚቴያችን እያሳሰበ፣ የመንግሥት እና የሕዝብ ኃብቶችን በማስመለስ አጥፊዎችም በሕግ እንዲጠየቁ ይደረግ ዘንድ በአጽንፆት እንጠይቃለን፡፡
12.4K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:38:06 በዓመታዊ የዋና ኦዲተር ሪፖርት ላይ የቀረበ የማጠቃለያ አስተያየት፤
*
አመሰግናለሁ የተከበሩ ምክትል አፈ-ጉባዔ፣

የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላት፣

ምክር ቤታችን በ2014 በጀት ዓመት ያፀደቀው በጀት የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ባከናወነው ኦዲት ባቀረበው ሪፖርት በርካታ የሂሣብ አያያዝ ግድፈቶች እና የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶች መኖራቸውን እንዲሁም አፈፃፀማቸው ከሕግ እና ከተዘረጋው አሰራር ውጪ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ በመሆኑም የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርቱን በመገምገም በምክር ቤቱ እና በፌዴራል ዋና ኦዲተር ትኩረት ሊያገኙ የሚገቡ አንኳር ምክረ-ሃሣቦችን እና የማጠቃለያ አስተያየቶችን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የመንግሥት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለት እና ለታቀደለት ተግባር በትክክል ሥራ ላይ እንዲውል ለመቆጣጠር እና ለመከታተል ይረዳው ዘንድ የሰው ኃይል አደረጃጀት፣ የመረጃ አያያዝ፣ ተግባራትን በዕቅድ መፈፀም እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ዋና ዋና ጥንካሬዎቹ መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡

በሌላ በኩል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለክልሎች የሚተላለፈውን የድጎማ በጀት ኦዲት ሪፖርት አስመልከቶ ለምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት ላይ የበላይ አመራሩን በቂ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን እንዲሁም የሕግ እና ፖሊሲ ድጋፍ የሚሹ አሰራሮችን ለይቶ አለማቅረቡን እንዲሁም የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራሉ መንግሥት አጠቃላይ ገቢ እና ወጪ ኦዲት ሪፖርት በተመለከተ ባቀረበልን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት የተብራራ ነገር አለማቅረቡን ቋሚ ኮሚቴው በድክመት አይቶታል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኦዲት ግኝትን ለማሻሻል የክትትል ኦዲትን ማሳደግ፣ የአገሪቱን የ1ዐ ዓመት መሪ ዕቅድ ለማስፈፀም እንዲቻል የልማት ኘሮጀክቶችን የዕቅድ ክትትልና የአፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ውጤት ማስገኘት፣ የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲትና የክዋኔ ኦዲት ሥራዎች በዓለምአቀፍ ደረጃ ጥራታቸውን የጠበቁ በማድረግ የሪፖርቱን ተዓማኒነት በማሳደግ ተቀባይነቱን ማረጋገጥ፣ የመስሪያ ቤቱን የውስጥ አሰራር ውጤታማነቱንና ቅልጥፍናን የሚያረጋግጡ ሪፎርሞች ለመተግበር ከኦዲት ኮሚሽን ጋር በቅርበት መስራትን ቁልፍ ተግባሩ አድርጎ ሊወስድ ይገባል፡፡

የተከበረው ምክር ቤትም በስሩ ባደራጃቸው የቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ለኦዲት ሪፖርቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርት ሊገመግምና ውጤት እንዲመጣ ጥረት ሊያደርግ ይገባዋል፡፡

የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ግምገማን መነሻ በማድረግ በቋሚ ኮሚቴው በኩል የቀረቡ ምክረ-ሐሣቦች፤

1.  የገንዘብ ማስመለስ ምጣኔ 0.65% ብቻ መሆኑ አስፈፃሚው አካል ለኦዲት ግኝት ትኩረት ያለመስጠቱን እንዲሁም በመቆጣጠር ተጠያቂነትን የማስፈን ኃላፊነት የተጣለበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በስሩ የተቋቋሙ ቋሚ ኮሚቴዎች የኦዲት ግኝት ሪፖርቶችን የቁጥጥር መሣሪያ አድርገው ከመጠቀም እና በአጠቃላይ አስፈፃሚውን አካል ከመቆጣጠር አኳያ ውሱንነቶች ያሉባቸው መሆኑን አመላካች ነው፡፡ የመቆጣጠር እና ከፊል የመቆጣጠር የሕግ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ማለትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ገንዘብ ሚኒስቴርና የፍትሕ ሚኒስቴር በአግባቡ በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት መወጣት ካልቻሉ የመንግሥትና የሕዝብ ኃብትና ንብረት ከመንግሥት ሕግ አሰራርና መመሪያ ውጪ ጥቅም ላይ መዋሉ የብሔራዊ ደኀንነት ስጋት ሆኖ መምጣቱ የማይቀር ነው፡፡ ስለሆነም በተለይም የተከበረው ምክር ቤት ተጠያቂነትን ሊያሰፍን ይገባል፡፡

2.  ነቀፌታ የሌለበት አስተያየት የተሰጣቸው ተቋማት ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት እያደገ መምጣቱ በመልካም ጎኑ የሚታይ ሆኖ አስተያየት መስጠት ያልተቻለባቸውና የጎላ ችግር ያለባቸው ሆነው በመገኘታቸው ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት የተሰጣቸው ተቋማት 25 የሚደርሱ መሆናቸው በተለይም እነዚህ ተቋማት ከሚያንቀሳቅሱት ፋይናንስ፣ የሰው ኃይል እንዲሁም ለአገር እና ሕዝብ ካሏቸው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዎች አንፃር ሲታይ በኦዲት ግኝቱ የተሰጣቸው አስተያየት አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም የተከበረው ምክር ቤት እና በስሩ ያቋቋማቸው የቋሚ ኮሚቴዎች የጉዳዩን አሳሳቢነት በማጤን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የማስተካከያ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡

3.  እጅግ ከፍተኛ የሆነ ተሰብሳቢ ገንዘብ መኖሩ እና ከዓመት ዓመት የሚስተዋለው የመሰብሰብ ምጣኔም ለዜሮ የቀረበ መሆኑ፣ ዜጎች በተቋማት እና በፋይናንስ ሕጎች፣ መመሪያዎችና አሰራሮች ላይ ያላቸውን አመኔታ ከመሠረቱ ተጠየቅ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ ስለሆነም የተከበረው ምክር ቤት ብርቱ አቋም ወስዶ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ሕግጋትንና መመሪያዎችን በማክበር የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ በአጽንፆት እንዲያሳስብ እንዲሁም የመንግሥትና ሕዝብ ኃብትና ንብረት እንዲመለስ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ፣ ተጠያቂነትንም እንዲያሰፍን በአንክሮ እንጠይቃለን፡፡

4.  በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ተመን ሳይወጣላቸው ከሕግ ውጪ የሚሰበሰቡ ገንዘቦች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ፣ ይኸውም ለሙስና እና ብልሹ አሰራር እንዲሁም ለቁጥጥርና ኦዲት ሥራ አመቺ ባለመሆኑ፣ የተከበረው ምክር ቤት አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግበት ውሳኔ ሊያሳርፍ ይገባል፡፡ የሚኒስቴሮች ምክር ቤትም ከዚህ አንፃር የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በቁልፍ ተግባር ይዞ ማስተካከያ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡

5.  የመንግሥት ተቋማት ከሕግና መመሪያ ውጪ ግዥዎችን እየፈፀሙ በመሆኑ፣ ይኸውም ለከፍተኛ የኃብት ብክነትና ብልሹ አሰራር አጋላጭ በመሆኑ፣ የተከበረው ምክር ቤት ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን አቋም ሊወስድ ይገባል፡፡

6.   የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በየተቋሞቻቸው ያሉ ንብረቶችን በሕግ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋላቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነታቸውን በወጉ መወጣት እንዳለባቸው ቋሚ ኮሚቴው ያሳስባል፡፡

7.  የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ከዓመት ዓመት ያለው የበጀት አጠቃቀም የኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው ጥቅም ላይ ያልዋለ በጀት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን እንዲሁም ከተደለደለው በጀት በላይ ያለፈቃድ አዛውረው በመጠቀም በኩል ያለው ችግርም ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡ ስለሆነም የተከበረው ምክር ቤት በበጀት ማጽደቅ ወቅት የኦዲት ሪፖርቱን መነሻ ያደረገ የበጀት ግምገማ እንዲያደርግ እና ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደርግ ቋሚ ኮሚቴው ምክረ-ሐሳቡን ያቀርባል፡፡

8.  በበርካታ የመንግሥት ተቋማት እጅግ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መጠን ወጪ ተደርጎ ደጋፊ ሰነድ ባለመቅረቡ ኦዲት ማድረግ እንዳልተቻለ የዋና ኦዲተር ሪፖርት ያሳያል፡፡ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለኦዲት ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ለምርመራ ማቅረብ የሕግ ግዴታ እንዳለባቸው በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት እና በፌዴራል ዋና ኦዲተር ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ከዚህ አንፃር የሚስተዋሉ የሕግ ጥሰቶችን እንዲሁም ለብልሹ አሰራር እና ለምዝበራ አጋላጭ ሁኔታዎችን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ የገንዘብ ሚኒስቴርና የፍትሕ ሚኒስቴር ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ተጠያቂነትን ሊያረጋግጡ ይገባል፡፡
9.8K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 08:49:01
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአሐዱ ቲቪ ጋር የነበረንን ቆይታ ነገ በእለተ ትንሳዔ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
3.3K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 07:46:11
5.0K views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ