Get Mystery Box with random crypto!

ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ http_gcgm — ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ http_gcgm — ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን
የሰርጥ አድራሻ: @http_gcgm
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.05K
የሰርጥ መግለጫ

👉መልካሙ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
👉ማቴ 14፥30
👉ሚኒስትሪያችንን በተለያዩ ስጦታዎች
ስለምታግዙን እናመሰግናለን።
ለማንኛውም ጥያቄ እና እገዛ👇
ለፀሎት አገልግሎት ከስር ያለውን ስልክ ይጠቀሙ።
📲 251966222852
👉 https://www.facebook.com/gcgm.gctv?mibextid=sCpJLy
👉YouTube-https://youtube.com/@melkamqine?si=vBbrpgENQkfcJZ_V

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-04 16:42:36 ኢየሱስን እንጠብቃለን…
የሐዋ ሥራ 1:11
354 viewsEjob @ JS, 13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 06:00:08 ሰላም ቅዱሳን
ዛሬ ከባለፈው የቀጠለውን ክፍል እናያለን
መጽሃፍቅዱስ በዘመን ከፍሎ ካልተጠና ፡እንደተደራሲ ማግኘት የሚገባንን ህይወት እና የተካፈልነውን ህይወት መኖር ያስቸግረናል ስለሆነም መነሻ አድርገን
2ጢሞ 2፥15 /1ቆሮ 15፥3-4...መጽሃፍ እንደሚል አንስተናል::

ሃዋርያው ጳውሎስ ፡የማያሰፍር ሰራተኛ ለመሆን መጽሃፍ በሚገባ ከፋፍሎ እንዲያጠና ለጢሞቲዮስ ሲያስረዳው እናያለን::
ከዚያም ባሻገር በዚሁ ክፍል ላይ ሙታን ትንሳኤ ሆኗል በሚል የስህተት ትምህርት ሄሚኖስ እና ፊልጦስ ለእምነት የሚሆንን እውቀት ሲያበላሹ እናያለን::

አንድ አገልጋይ "መተተኛይቱ በህይወት እንድትኖር አትፍቀድላት "የሚል አውድ ያልጠበቀ ጥቅስ በማንበቡ እየዞረ መተተኛ ሰዎችን ሲገል ነበር::
በዘመኑ ሄዶ እውነቱን ካልተረዳ ልክ ያልሆነ አድራጎት ነው።ሰዎች እንዲገደሉ የጌታ ፈቃድ አደለም ፡ለማን ተጻፈ ብለን ማሰብ ይጠበቅብናል።

ስለዚህ በክፍል 2 ጊዜታችን
1 ያለፉት ዘመናት የሚባል እንዳለ እና የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሉ (ከዘፍ-ሚል/ማቴ-ዩሐ) ድረስ የሚገኘው ክፍል ያለፉት ዘመናትን የሚጠቁም እና ለትምህርታችን የተጻፉ ናቸው ብለና ቀጥታ እኛን የሚመለከት እንዳለሆነ አንስተናል::

የአሁን ዘመን
ኤፌ 2፥13
የአሁን ዘመን የምንለው በቀጥታ ተደራሲ የሚሆነው ለአህዛብ (ለእኛ ነው ደግሞም ለትምህርታችን ነው)
የሚጀምረውም(ከሐዋ ስራ ም 15 እስከ ፊሊሞና መጽሃፍ )ይሆናል::
በተለምዶ አጠራሩ "የጸጋ ወንጌል"የሚባልበት ዘመን ነው።
እዚህ ዘመን ላይ ጸጋ እና ሰላም በግልጽ የተገለጠበት፡የበዛበት ዘመን ይባላል(ሮሜ 11፥25)
ወንጌል ላልተገረዙት የሚል እንቅስቃሴ የታየበት(ገላ 2፥7)
የጸጋ ወንጌል የሚል እንቅስቃሴ የተጀመረበት (20፥24)
በማየት ሳይሆን በእምነት የሚንቀሳቀስበት ዘመን ማለት ነው::

የአሁኑ ዘመን በአጠቃ ላይ (REVLATION OF MYSTERY) ሚስጥር የተገለጠበት ዘመን ማለት ነው።
ይህ ዘመን ላይ ሁሉ ተጠቅልሎ የሚሰራው ለመልካም ፡ይህ ዘመን የሚሰራው በክርስቶስ ላይ ባለን እምነት እንጂ የነህምያ መጽሃፍ ተጠቅሶ በሚተነበይ ትንቢት ወይንም፡ዘይት ምርት ስራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች የሚሰራልህ/ሽ ህይወት የለም ::

ሰው ቸርች ሄዶ፡ወይንም ከወድሞች ጋር ሲሆን የሚገለጥ የክርስቶስ የጸጋ ህይወት እንጂ በየቤተክርስቲያን እየዞርክ ትንቢትየምትቀበልበት ህይወት አደለም::

ወደረፍት የገባ ህይወት መድረክ ላይ በሚያገለግል አንድ ጸጋ በሚሰራበት ሰው አዲስ ህይወት አይሰጠውም ህይወቱ በእናንተ ይሰራል በገንዘብ የሚገዛ ፈውስ የለም ፍውውሱ በእናንተ ይሰራል የአሁኑ ዘመን ህይወት ጸጋው አብልጦኑ የሚሰራበት ነው
ትግል ሳይሆን ህይወት ሰጪው መንፈስ እንዲሰራ በማመን የሚገለጥ ህይወት እንጂ አቶ እከሌ የጸለዩበትን ዘይት በመጠታት የሚሰራ ህይወት አደለም::

የክብር ተስፋ ያለው እየሱስ በእናንተ ውስጥ ሆኖ የሚሰራበት ዘመን ነው፡ታዲያ ይህ ዘመን በዚህ መልኩ ከተረዳን እንዴት እንመላለስ?....ይቀጥላል
===============================
በቀጣይ ሳምንት
የወደፊት ዘመን(ኤፌ 2፥7)
===============================
ለተጨማሪ ጥያቄዎች-0966222852
Or Inbox us on Telegram (https://t.me/joinchat/AAAAAFMzwMKEzglqqR6tnw)
Powered by እዮብ አበራ
Goodness of Christ Gospel Ministry 
713 viewsEjob @ JS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 06:00:04
716 viewsEjob @ JS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 16:34:09 ወንጌል እንስራ እወዳቹሃለሁ::
ዮሐ 3:16
766 viewsEjob @ JS, 13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 06:00:25 ሰላም ቅዱሳን ዛሬ ከባለፈው የቀጠለውን ክፍል እናያለን መጽሃፍ ቅዱስን በዘመን ከፍለን ማጥናታችን ፡ነቀፋ የሌለበት ፡እና እውነተኛ የሆነው የቅዱስ እግዚአብሔርን ህይወት ለመኖር ፡በክርስቶስ የተሰራውን እውነት ተረደቶ ለመመላለስ ይጠቅማል ።
የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል
2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)
15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
2 Timothy 2 (WEB) - 2 ጢሞቴዎስ
15: Give diligence to present yourself approved by God, a workman who doesn't need to be ashamed, properly handling the Word of Truth.
(study)
የሚለውን ሃሳብ የያዘ ሲሆን
ትክክለኛ የሆነ ኑሮን ለመኖር ይጠቅማል።

መጽሃፍ ቅዱስ በሰጠናችሁ ቻርት መሰረት በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን ብለናል

1.ያለፉት ዘመናት( ኤፌ 2፥11)
2.የአሁኑ ዘመን (ኤፌ2፥13)
3.የወደፊቱ ዘመን (ኤፌ2፥7)

ኤፌ2፥7-14
ኤፌሶን 2 (Ephesians)
6-7፤ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።
8፤ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
10፤ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።
11፤ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤
12፤ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።
13፤ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።
Ephesians 2 (WEB) - ኤፌሶን
7: that in the ages to come he might show the exceeding riches of his grace in kindness toward us in Christ Jesus;
8: for by grace you have been saved through faith, and that not of yourselves; it is the gift of God,
9: not of works, that no one would boast.
10: For we are his workmanship, created in Christ Jesus for good works, which God prepared before that we would walk in them.
11: Therefore remember that once you, the Gentiles in the flesh, who are called "uncircumcision" by that which is called "circumcision," (in the flesh, made by hands);
12: that you were at that time separate from Christ, alienated from the commonwealth of Israel, and strangers from the covenants of the promise, having no hope and without God in the world.
13: But now in Christ Jesus you who once were far off are made near in the blood of Christ.

1.ያለፉት ዘመናት
(ኤፌ 2፥11)
11፤ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤
12፤ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።

በዚህ ዘመን የተጻፈው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል በቀጥታ ተደራሽነቱ፡ለአህዛብ አደለም ነገር ግን ለትምህርታችን ተጽፏል::
ያ ማለት መጽሃፍ ቅዱስን ከመጀመሪያው ጀምረን እስከ የሽግግር ጊዜ እስከምንለው የሐዋርያት ስራ ድረስ በቀጥታ አህዛብን የሚመለከት አደለም ፡ግን ለትምህርት ተጽፈዋል::

አህዛብ ስንል አህዛብ እኛን ማለት ነው ፡ወንጌለልልን በሐዋርያው ጳውሎስ ያገኘነው ማለት ነው።

በነዚህ ዘመናት ለእስራኤል ኪዳን የተገባላት,ቅነሳ የተደረገበት እንደአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን መልእክት ከተደራሽነት አንጻር አይሁድን እንጂ ፡አህዛብን አይመለከትም ሆኖም ግን ለትምህርታችን ተጽፏል ይህም ማለት

ለምሳሌ
ሁለት ጓደኛሞች ቢኖሩ እና አንደኛው ትልቅ ስህተት አድርጎ ቢሂን እና አብረው እያሉ አባትየው መትልጥቶ ያጠፋውን ልጅ ቢቆጣ ፡ወይንም ቢቀጣው ።
ጥፋቱን ያጠፋው ልጅ ቀጥታ ተደራሲ ሲሆን
ሁለተኛው ልጅ ደግሞ ከእሱ የሚማር ይሆናል;:

በመጽሃፍም እንዲህ ነው የሆነ ስለዚህ
በዘመናት መካከል ያለ የተዛባ እውቀት በዚህ መልኩ መስተካከል አለበት::

በብሉይ ኪዳን ቃል እየመዘዙ መተንበይ፡ይሁን ሌላም ሌላም በድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው።

ትክክለኛውን ህይወት መኖር የሚጀምረው ትክክለኛውን እውቀት በመያዝ ነው።

በክርስቶስ ሆኜ አዲስ ፍጥረት ነኝ ለሚል ይሄ በደንብ ሊረዳው ይገባል።

ታዲያ ያለፉት ዘመናት ብለን የምንለው እኛን በቀጥታ የማይመለከተን ከሆነ፡በቀጥታ እኛን ተደራሲ የሚያደርገው ክፍል የትኛው ነው?
===============================
በቀጣይ ሳምንት
ያሁኑ ዘመን ለማን ተጻፈ?የወደፊቱስ ማንን የሚያመለከት ነው?
===============================
ለተጨማሪ ጥያቄዎች-0966222852
Or Inbox us on Telegram (https://t.me/joinchat/AAAAAFMzwMKEzglqqR6tnw)
Powered by እዮብ አበራ
Goodness of Christ Gospel Ministry 
772 viewsEjob @ JS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 06:00:06
767 viewsEjob @ JS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 18:26:41
መልካም ዜና በሐገር ውስጥም ይሁን ከሐገር ውጪ ላላችሁ በሙሉ
ከሚኒስትሪያችን ጋር ማገልገል ይሁን ፥በተለያዩ ነገሮች ማገዝ የምትሹ በtelegram እና በwhatsApp ስልካችን +251966222852
Goodness Of Christ Gospel Ministry ብላችሁ ማናገር ትችላላችሁ።

ኢየሱስ በክብር ይመጣል!
748 viewsEjob1 Ejob, edited  15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 16:42:35
ወደልባችሁ መዝሙር ሲመጣ የትም ሁኑ ዘምሩት ምክኒያቱ በውስጣችሁ ያደረው መንፈስ ቅዱስ እሱን ዝማሬ መስማት ፈልጎ ነው፥ዘምሩት የዝማሬ ኋይል ታላቅ ነው።
በዝማሬ ከጥንት ጀምሮ ብዙ ዱል ሆኗል

ዝማሬ ጉልበት ነው(ዘጸ 15:2)
ዝማሬ ጠላትን መምቻ ነው(2ዜና 20:22)
ዝማሬ ማክበሪያ ነው(መዝ 33:3)
ዝማሬ ብዙዎች ጌታን ያምኑበታል(መዝ 40:3)
ዝማሬ ደስታ መግለጫ ነው(መዝ 71:23)
ዝማሬ ከወኋኒም መውጫ ነው(ሐዋ..)
ዝማሬ መንፈሳዊ አደራረግ ነው(ኤፌ 5:19)
ዝማሬ ለእግዚአብሔር ነው(ቆላ 3:16)
ትላትናም፥ዛሬም፥ወደፊትም ዝማሬን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ለሚዘምሩ ጸጋ ይብዛላቸው።
እናንተም መንፈስ ቅዱስ እንደሚመራችሁ ዘምሩ፥ ድንገት ወደልባችሁ ከመጣ ዝማሬ ዘምሩ ያለመከልከል።እግዚአብሔር ሲከብር አጋንንት ሲጮህ ነፍሳትም(ሰው)ሲፈወስ እና ሲድን ታያላችሁ።


ኢየሱስ በክብር ይመጣል!
953 viewsEjob1 Ejob, edited  13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 08:01:24 የኢየሱስን የማዳን ወንጌል ያለፍርሃት ተናገሩ
479 viewsEjob @ JS, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 14:16:05



ይህ ሲዳምኛ መዝሙር ግን…
730 viewsEjob @ JS, edited  11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ