2023-03-17 06:13:26
ሰላም ቅዱሳን እንደምን አላችሁ ይህ የምትመለከቱት Chart መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነት ማወቅ እፈልጋለሁ ለሚል እና እውነቱን አውቆ ለመኖር እንዴት መጽሃፍ ቅዱስን ላንብብ ብሎ ለሚል የሚጠቅም "chart" ነው።
መሰረታዊ የመጽሃፍ ቅዱስ አነባበብ
መጽሃፍ ቅዱስን እንዴት እናጥና?
በዘመን ከፍለን እናጥና
አንድ ሰው ለምሳሌ አንድ ቋንቋ ማወቅ ከፈለገ ፡ሊያውቀው የፈለገውን ቋንቋ መሰረታዊ ትምህርቶች ሊማር ግድ እደሆነበት::
መጽሃፍ ቅዱሳዊ እውነትን ለማወቅ እና ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ለመግባባት ከፈለገ ይህን "chart" በደንብ መረዳት አለበት::
እንግዲ እደምትመለከቱት መጽሃፍ ቅዱሳዊ መረጃን በመመርኮዝ ፡መጽሃፍ ቅዱስን በዘመን ከፍሎ ማጥናትን እናያለን
መነሻ ጥቅስ 2ጢሞ 2፥15
2 Timothy 2 (KJV) - 2 ጢሞቴዎስ
15:( Study) to shew thyself approved unto God, a workman that needeth not to be ashamed, rightly dividing the word of truth.
በንኡስ ሃሳብ( study) ወይንም( አጥና)ብሎ ሃዋርያው ጳውሎስ ይናገራል ።
ይህ የሚያሳየው መጽሃፍ ቅዱስ በዘመን ከፍሎ ማጥናት መሰረታዊ የሆነ ነገር እንደሆነ ይናገራ::
መጽሃፍ ቅዱስ በዘመን ከፍሎ ማጥናት ያሰፈለገው ምክኒያት እውነተኛ የሆነ እውነት ለመያዝ ነው::
በዚህ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የጊዜ መዛባት ይታያል
2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)
15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
16፤ ነገር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ፤ ኃጢአተኝነታቸውን ከፊት ይልቅ ይጨምራሉና፥ ቃላቸውም እንደ ጭንቁር ይባላል፤
17፤ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ናቸው፤
18፤ እነዚህም፡— ትንሣኤ ከአሁን በፊት ሆኖአል እያሉ፥ ስለ እውነት ስተው፥ የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ።
በዘመን ከፍሎ ባለማጥታት ምክኒያት እምነታቸው እስከሚገለበጥ ድረስ ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ "ትንሳኤ"በፊት ሆኗል በማለት የስህተት ትምህርት ሲያስተምሩ እንመለከታለን ፡ለዚህ ነው ሃዋርያው ጳውሎስ አጥና የሚለው::
ትንሳኤ ወደፊት የሚሆን ሲሆን እነሱ ግን ከዚህ በፊት ሆኗል ፡የሚል አስተምህሮት ያንጸባርቃሉ
የመጽሃፍ ቅዱስ ሶስት ዘመናት እንዳለ ይነግረናል
1.ያለፉት ዘመናት(ኤፌ 2፥11)
2. አሁን ዘመን(ኤፌ 2፥13)
3.ወደፊት ዘመን(ኤፌ 2፥7)
===============================
በቀጣይ ሳምንት
ያለፈው ዘመን ለማን ተጻፈ?ያሁኑ ዘመን ለማን ተጻፈ?የወደፊቱስ ማንን የሚያመለከት ነው?
===============================
ለተጨማሪ ጥያቄዎች-0966222852
Or Inbox us on Telegram (https://t.me/joinchat/AAAAAFMzwMKEzglqqR6tnw)
Powered by እዮብ አበራ
Goodness of Christ Gospel Ministry
320 viewsEjob @ JS, edited 03:13