2022-11-11 06:14:27
እውነተኛው አምላክ እና አዲሱ ሰው
አዲሱ ሰው እና የማይታወቅ አምላክ ተብሎ የተጠራው አምላክ
ሰላም ለእናንተ....
Acts 17 (WEB) -
23: For as I passed along, and observed the objects of your worship, I found also an altar with this inscription: 'TO AN UNKNOWN GOD.' What therefore you worship in ignorance, this I announce to you.
አማርኛ - የማይታወቅ አምላክ
English-Uknown God
Ancient Greek-Agnostos Theos
ይህን ልብ በማለት
1.ክርስትና
ክርስቲያን ተብለው የሚጠሩ አማኞች፡የእምነት መጠሪያቸው ሲሆን ፍቺውም "ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ " እንደሆነ የሚያምኑ ሰዎች መጠሪያ ሆኖ ያገለግላል:: አዲሱ ሰው ከነዚህ አማኞች ጎራ ነው:: ለምን አዲሱ ሰው ብዙ የእምነት አይነቶች በአሁኑ ዘመን እያሉ "ክርስትና" ላይ አተኮረ ካላችሁ.....
በመጀመሪያ የክርስትና ሃሳብ አጀማመር እና አቋም እንመልከት እና ሌሎቩንም በዘመናት መካከል የሚገኙትን የእምነት አይነቶች ተመልክተን ከዚያ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እንሞክራለን::
ክርስትና የተባለው አሳብ መሰረት ያደረጉት ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን ላይ ሲሆን:: በህብረትም ሆነ በግል ሆነው ለአምላካቸው እውቅና ለመስጠት እና እራሳቸውን ሆነ ሌሎችን ለማነጽ፡ለመምከር ፡ለመገሰጽ፡ለማስተማር መጽሃፍ ቅዱስ ከአምላክ የተላከ በተመረጡ ሰዎች ተጽፈዋል በማለት ይጠቀሙበታል።
ይህ እምነት በዋናነት ጎልቶ የወጣው ጴንጤናዊው ጲላጦስ ገዢ በነበረበት ዘመን ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ከተሰቀለ በኋላ ነው።
በዋናነትም
እግዚአብሔር አብ "አባት"፡
እግዚ አብሔር ወልድ "ልጅ"
እግዚአብሔር መንፈስ "መንፈስ ቅዱስ"
ብለው ያምናሉ እና ሞት፡ትንሳኤ፡የኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ላይ ጽኑ አቋም ያላቸው አማኞች የሚጠሩበት ነው።
የዚህ እምነት አራማጆች "ባለአምሳ ቀን" በተባለበት ቀን ክርስቶስ ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ፡ተሰብስበው በህብረት በመሆን
ቤተ-ክርስቲያን (ኤክሊዢያ)፥ መስርተዋል:: በአብዛኛው በዚህ ህብረት ውስጥ የነበሩት " አይሁዳዊ" ሲሆኑ ቤተ-ክርስቲያን የመሰረቱት እየሩሳሌም ውስጥ ነበር:: ከተመሰረተም በኋላ ብዙ አህዛቦች ክርስቲያን የመሆን እድል አግኝተዋል።
በዋናነትም "ወንጌል" ወይም "የምስራች ቃል" ለመናገር እና ለማብሰር እንደተጠሩ ያምናሉ።
12 መሪ ሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ከተመረጡት ጨምሮ በዋናነት ወንጌልን አተኩሮ ይሰራ የነበረ ቀድሞ አሳዳጅ የነበረ ከዚያም የወንጌል ወዶ ዘማች የሆነው ሓውርያ ሊሆን የተጠራው ጳውሎስ ለዚህ ተምሳሌት ተደርገው ይወሰዳሉ::
በ64 A.D"ንጉስ ኔሮ" ገዢ በነበረበት ሰአት ከባድ ስደት የተፈጠረባቸው እንደሆነ ይነገራል፡በተጨማሪም በ 313 A.D ትልቅ ስደት ተፈጥሮባቸዋል።
ይሕ ሁሉ ከሆነባቸው በኋላ
በድጋሚ የተነሳው የወንጌል አብዮት እንዴት ነበር ሳምንት ይጠብቁን
===============================
በቀጣይ ሳምንት
በድጋሚ የተነሳው የወንጌል አብዮት እንዴት ነበር
===============================
ለተጨማሪ ጥያቄዎች-0966222852
Or Inbox us on Telegram (https://t.me/joinchat/AAAAAFMzwMKEzglqqR6tnw)
P. እዮብ አበራ
Goodness of Christ Gospel Ministry
655 viewsEjob1 Ejob, edited 03:14