Get Mystery Box with random crypto!

ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን//Heaven Gift Church//

የቴሌግራም ቻናል አርማ http_gcgm — ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን//Heaven Gift Church//
የቴሌግራም ቻናል አርማ http_gcgm — ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን//Heaven Gift Church//
የሰርጥ አድራሻ: @http_gcgm
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.34K
የሰርጥ መግለጫ

👉መልካሙ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
👉ማቴ 14፥30
👉ሚኒስትሪያችንን በተለያዩ ስጦታዎች
ስለምታግዙን እናመሰግናለን።
ለማንኛውም ጥያቄ እና እገዛ👇
ለፀሎት አገልግሎት ከስር ያለውን ስልክ ይጠቀሙ።
https://www.facebook.com/gcgm.gctv?mibextid=sCpJLy
👉YouTube-https://youtube.com/@melkamqine?si=vBbrpgENQkfcJ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-12-16 11:50:55
“በክርስቶስ “ተፈጸመ!
መፅሐፉ በነጻ የሚከፍፈል ነው ፥ ወስዳችሁ
ተባረኩበት

ኢየሱስ ያድናል!
889 viewsEjob1 Ejob, 08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 05:55:14 ሰላም ለእናንተ የGoodness of Christ Gospel Ministry ወዳጆች በሙሉ ዛሬ የትምህርት ርእሳችን ስለ ሥላሴ ይሆናል።

               ሥላሴን መረዳት
የሥላሴ አስተምህሮ የክርስትና እምነት መሠረት ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ማንነት ለማወቅ፣ እርሱ ከእኛ ጋር በምን መልኩ ህብረት እንደሚያደርግና እኛም ከእርሱ ጋር እንዴት ህብረት ማድረግ እንዳለብን ለመረዳት እጅግ አስፈላጊ አስተምህሮ ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ ከበድ ያሉ ጥያቄዎች ያሉበትም ትምህርት ነው። እግዚአብሔር እንዴት በአንድ ጊዜ አንድና ሦስት ይሆናል? ትምህርተ ሥላሴ እርስ በእርሱ ይቃረናል? ኢየሱስ አምላክ ከሆነ ወደ እግዚአብሔር እንደፀለየ በወንጌላት ላይ ለምን ተገለፀ? ሥላሴን ( ወይም የትኛውንም ሌላ ነገር ቢሆን) ሙሉ በሙሉ መረዳት ባንችልም ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት ጥያቄዎች በመመለስ እግዚአብሔር ሦስትና አንድ ነው ማለት ምን እንደሆነ ጠንካራ ጭብጥ ይኖረናል።

እግዚአብሔር ሥሉስ አምላክ ነው ማለት ምን ማለት ነው?

የሥላሴ አስተምህሮ ማለት እግዚአብሔር ሦስት የተለያዩ አካላት ማለትም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሆነ አንድ አምላክ ነው ማለት ነው። በሌላ አገላለፅ እግዚአብሔር በማንነት፣ በመለኮትና በህልውና አንድ ሲሆን በአካል ግን ሦስት ነው ማለት ነው፡፡ ይህ አተረጓጐም ሦስት ጠቃሚ እውነቶችን ያዘለ ነው፦ (1) አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሦስት የተለያዩ አካላት ናቸው፥ (2) እያንዳንዱ የሥላሴ አካል ሙሉ አምላክ ነው፥ (3) እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው።
አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሦስት አካላት ናቸው
መፅሐፍ ቅዱስ አብ አምላክ እንደሆነ (ፊልጵስዩስ 1፡2)፣ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ (ቲቶ 2፡13) ፣ መንፈስ ቅዱስ አምላክ እንደሆነ (ሐዋርያት ሥራ 5፡3-4) ይናገራል። እነዚህ ክፍሎች የሚያሳዩት አንድ እግዚአብሔርን የምንረዳበት ሦስት የተለያዩ መንገዶች ወይም ስለ አንድ እግዚአብሔር ሦስት የተለያዩ ገጽታዎች ነውን?
መልሱ አይደለም መሆን አለበት ምክኒያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያመለክተው  አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሦስት አካላት እንደሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ በዮሐንስ 3:16 መሠረት አብ ወልድን ወደ ዓለም እንደላከው ስለተገለፀ ከወልድ ጋር አንድ አካል ሊሆን አይችልም። በተጨማሪም በዮሐንስ ወንጌል 16፡ 1ዐ መሠረት ወልድ ወደ አብ ከተመለሰ በኋላ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስን ወደ ዓለም ይልካሉ (የሐንስ 14:26፣ ሐዋርያት ስራ 2:33)፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና ወልድ ሌላ ሦስተኛ አካል ነው ማለት ነው።
በማርቆስ 1፡1ዐ-11 ላይ እንደተጠቀሰው ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ ከውሃው ሲወጣ እግዚአብሔር ከሰማይ በድምፅ ሲናገርና መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል ከሰማይ ሲወርድ እንመለከታለን፡፡ በዮሐንስ 1፡1 ላይ ኢየሱስ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነና በተመሳሳይ ጊዜም "ከእግዚአብሔር ጋር" እንደነበር በማመልከት ኢየሱስ ከአብ የተለየ አካል እንደሆነ ያሳያል (1:18ን በተጨማሪ ተመልከት)። በዮሐንስ 16፡13-15 ላይ በሥላሴ መሃል ጥብቅ የሆነ አንድነት እንደተጠበቀ ሆኖ መንፈስ ቅዱስ እንደአብና ወልድ የራሱ አካል እንዳለውም ተጠቅሷል። አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሦስት አካል ናቸው ማለት በሌላ አባባል አብ ወልድ አይደለም፤ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ አብ አይደለም  ማለት ነው። ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው፤ ነገር ግን አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፤ ነገር ግን አብ ወይም ወልድ አይደለም። ሦስት አካል ናቸው እንጂ አንድ እግዚአብሔርን የምናይባቸው ሦስት መንገዶች አይደሉም።
ሥላሴ ሦስት አካል መሆኑ እያንዳንዱ የራሱ የሆነ ሃልዎት ያለው እንደሆነ ያሳያል፡፡ ስለዚህም እርስ በርስ ግንኙነት የሚያደርጉትም በዚህ መሠረት ነው፦ አብ ራሱን "እኔ" (1ኛ መደብ) ብሎ ሲጠራ ወልድን ወይም መንፈስ ቅዱስን ደግሞ "አንተ" (2ኛ መደብ) ብሎ ይጠራል። በተመሳሳይም መንገድ ወልድ ራሱን "እኔ" ብሎ ሲጠራ አብን ወይም መንፈስ ቅዱስን "አንተ" ብሎ ይጠራል። 
ብዙ ጊዜ "ኢየሱስ አምላክ ከሆነ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት መፀለይ የነበረበት ወደ ራሱ ነው'' የሚል ተቃውሞ ይስተዋላል። ነገር ግን ከላይ የተመለከትነው እውነት ለዚህ ተቃውሞ በቂ መልስ ነው። ኢየሱስና አብ አምላክ ቢሆኑም ሁለት የተለያዩ አካላት ደግሞ ናቸው። ስለዚህ ኢየሱስ ወደ አብ እንጂ ወደ ራሱ አልፀለየም። እንደውም በአብና በወልድ መሃል ያለው ቀጣይነት ያለው ንግግር (ማቴዎስ 3፡17፣ 17፡5፣ ዮሐንስ 5፡19፣ 11፡41-42፣ 17: ከ1ጀምሮ ) ሁለት የራሳቸው ሃልዎት ያላቸው አካላት ለመሆናቸው በቂ ማስረጃ ነው። 
አንዳንድ ጊዜ በአብና በወልድ ላይ ትኩረት እናደርግና መንፈስ ቅዱስን ግን እንዘነጋለን። አንዳንዴ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ሃልዎት እንዳለው አካል ሳይሆን እንደ "ሃይል" ተደርጐ ይወሰዳል። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ሃይል ሳይሆን የራሱ ሃልዎት ያለው አካል ነው (ዮሐንስ 14:26፣ 16፡7-15 እና ሐዋርያት ስራ 8:16 ን ተመልከት)። መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አካል መሆኑንና ዝም ብሎ ሃይል አለመሆኑን (ልክ የመሬት ስበት ሃይል እንደምንለው) የሚናገር በመሆኑ (ዕብራውያን 3፡7)፣ በምክኒያታዊነቱ (ሐዋርያት ስራ 15፡ 28) ፣ ማሰብና መረዳት በመቻሉ (1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10-11)፣ ፈቃድ ያለው በመሆኑ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡11)፣ ስሜት ያለው በመሆኑ (ኤፌሶን 4፡30) እና የግል ህብረትን የሚሰጠን በመሆኑ (2ኛ ቆሮንቶስ 13፡14) በእነዚህ ማየት ይቻላል። እነዚህ ባህሪያት ራሱን የቻለ ማንነት ያለው አካል መገለጫዎች ናቸው። ከእነዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በተጨማሪ ከላይ ያሉት ክፍሎችም መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የሚለይ ሌላ አካል መሆኑን በግልፅ ያሳዩናል። ስለዚህም እነዚህ ሦስት የሥላሴ አካላት እንጂ የአንድ እግዚአብሔር ሦስት የተለያዩ ገጽታዎች አይደሉም፡፡ 
በሥላሴ ዙሪያ ሰዎች የሚሳሳቱት ሌላው አደገኛ ስህተት ደግሞ አብ ወልድ ሆነ፤ ቀጥሎ ወልድ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ሆነ የሚል ነው፡፡ ከዚህ ዕይታ በተቃርኖ ግን ከላይ ያየናቸው ክፍሎች እግዚአብሔር ሦስት አካል መሆኑን ያሳዩናል። በሥላሴ ውስጥ ያለ የትኛውም አካል ያልነበረበት ጊዜ የለም። ሦስቱም አካላት ዘላለማዊ ናቸው።
ሥላሴ ሦስት አካል ቢሆንም አንዱ የሥላሴ አካል ግን ከሌላው ያንሳል ማለት አይደለም። በአንፃሩ በባህርይ ሁሉም አቻ ናቸው። በሃይል፣ በፍቅር፣ በምህረት፣ በፍርድ፣ በቅድስና፣ በዕውቀት እና በሌሎች ባህሪያት ሦስቱም እኩል ናቸው። 
እያንዳንዱ የሥላሴ አካል ምሉዕ አምላክ ነው
እግዚአብሔር ሦስት አካል ነው ካልን እያንዳንዱ አካል የሥላሴ ሲሶ (አንድ- ሦስተኛ) ነው ማለት ነው? ሥላሴ ማለት እግዚአብሔር በሦስት ይከፈላል ማለት ነው?
ትምህርተ ሥላሴ እግዚአብሔርን በሦስት ቦታ አይከፋፍልም፡፡ እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ግልፅ አስተምህሮ እያንዳንዱ የሥላሴ አካል ራሱ መቶ በመቶ አምላክ ነው።አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሦስቱም ምሉዕ አምላክ ናቸው ። ለምሳሌ በቆላስያስ 2፡9 ላይ ስለ ክርስቶስ ሲናገር "የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና፤" ይላል። እግዚአብሔርን "ኬክ" ሦስት ቦታ ሲቆረጥ እያንዳንዱ ቁራጭ አንዱን የሥላሴ አካል ይወክላል በሚለው ምሳሌ መመሰል የለብንም። ...ይቀጥላል

ኢየሱስ ያድናል!
https://t.me/http_GCGM
1.1K viewsEjob1 Ejob, edited  02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 05:54:28
1.1K viewsEjob1 Ejob, 02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 22:42:33
“በክርስቶስ “ተፈጸመ!
መፅሐፉ በነጻ የሚከፍፈል ነው ፥ ወስዳችሁ
ተባረኩበት

ኢየሱስ ያድናል!
554 viewsEjob @ JS, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 22:42:09
“በክርስቶስ “ተፈጸመ!
መፅሐፉ በነጻ የሚከፍፈል ነው ፥ ወስዳችሁ
ተባረኩበት

ኢየሱስ ያድናል!
570 viewsEjob @ JS, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 14:51:14
“በክርስቶስ “ተፈጸመ!
መፅሐፉ በነጻ የሚከፍፈል ነው ፥ ወስዳችሁ
ተባረኩበት

ኢየሱስ ያድናል!
1.3K viewsEjob1 Ejob, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 17:09:02 እጸልያለሁ



784 viewsEjob @ JS, 14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 06:46:15 ሰላም ለእናንተ የGoodness Of Chrsit Gospel Ministry ወዳጆች ዛሬ የምንማረው
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ይሆናል
ብሉይ ኪዳን በ 5 ሲከፈል እነርሱም፦
1)የሕግ መጽሐፍ
2)የታሪክ መጽሐፍ
3)የግጥም መጽሐፍ
4)ዋና ነብያት
5)ጥቂት ነብያት
ይባላሉ።
አዲስ ኪዳን በ 4 ሲከፈል እነርሱም፦
1)ወንጌላት
2)የቤተክርስቲያን ታሪክ
3)የመለእክት(የደብዳቤ)
4)የትንቢት
የሚባሉ ሲሆን በእያንዳንዱ የመጽሐፍ ክፍሎች ደግሞ የራሳቸው ክፍሎች ይኖራሉ
የሕግ መጽሐፍ
ዘፍጥረት
ዘጸአት
ዘሌዋውያን
ዘኋልቁ
ዘዳግም ይይዛል።
የታሪክ መጽሐፍ
መጽሐፈ ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1ኛ እና 2ኛ ሳሙኤል
1ኛ እና 2ኛ ነገሥት
እዝራ
ነህምያ
አስቴር መጽሐፍን ያካትታል።
የግጥም መጽሐፍ
መጽሐፈ ኢዮብ
ዳዊት
ምሳሌ
መክብብ
መኋልየ መኋልየ መጽሐፍን ያካትታል።
ዋና/ትላልቅ ነብያት
ከትንቢተ ኢሳያስ እስከ ትንቢተ ዳንኤል ያካተተ ነው።
ትንሽ/ጥቂት ነብያት
ትንቢተ ሆሴ ጀምሮ እስከ ትንቢተ ሚልኪያስ የያዘ ነው።
አዲስ ኪዳን ላይ
ወንጌላት የሚባሉት
ከማቴዎስ ወንጌል እስከ ዩሐንስ ወንጌል ይይዛል።
የቤተክርስቲያን ታሪክ
ሐዋርያት ሥራ የያዘ ነው
ደብዳቤዎች(መልእክቶች)
ከሮሜ መጽሐፍ እስከ ይሁዳ መልእት የተያያዘ ነው።
የትንቢት መጽሐፍት
የዩሐንስ ራእይን የሚይዝ ይሆናል።
ወገኖች ይህን እየተገነዘባችሁ መጽሐፍትን ብታነቡ ትልቅ መረዳት እና ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ህብረት የጨመረ ይሆናል።
66ቱ መጽሐፍ ቅዱስ መካከል 39ኙ ብሉይ ኪዳን ሲሆን 27ቱ ደግሞ አዲስ ኪዳን ነው።በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ምሪት በ40 የተለያዩ ሰዎች እና የሕይወት ልምምድ ባላቸው ሰዎች የተጻፈ ነው።
እዚህ ላይ በተጨማሪ እንድትገነዘቡት የምፈልገው major and minore prohet ወይም ዋና ነብያት እና ጥቂት/ትንሽ ነብያት ተብለው የተጠቀሱት አገልጋዪች ከጻፉት የትንምት መልእት የወረቀት ብዛት እና ለጥናትእንዲመች  እንጂ የጸጋ ትልቅ እና ትንሽ የለው ሰለዚህ በዚህ ዘመንም ቢሆን major and minore የተባለ የሚጠራ አገልጋይ የለም ።
በቀረውስ፦አምላኬ እንደባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልካችሁን ይሙላባችሁ።

https://t.me/http_GCGM
331 viewsEjob1 Ejob, edited  03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 06:46:10
335 viewsEjob1 Ejob, 03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 20:12:40
“በክርስቶስ “ተፈጸመ!
መፅሐፉ በነጻ የሚከፍፈል ነው ፥ ወስዳችሁ
ተባረኩበት
1.2K viewsEjob @ JS, 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ