2023-01-13 06:21:54
አዲሱ ሰው እና የመንፈስ ፍሬ
ገላትያ 5 (Galatians)
22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
አዲሱ ሰው ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን የሚገኝ ህይወት ነው።
2 ቆሮንቶስ 5 (2 Corinthians)
17፤ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
ይህ አዲሱ ሰው ደግሞ
ዛፍ ሲያድግ ፍሬ እንደሚኖረው ሁሉ ፡አዲሱ ሰው ሲፈጠርም ፡በመንፈስ አዲስ ተደርጓል ፡ነፍሱ እየታደሰ ይሄዳል ፡ስጋው እየዳነ ይሄዳል በዳነው መንፈስ አማካኝነተ የሚቀለው የመንፈስ ፍሬ ይኖረዋል። ሁሉም ነገር ፍሬ እንዳለው አዲሱ ሰውም ፍሬ አለው እሱም እንዳልነው የመንፈስ ፍሬ ተብሎ ይጠራል።እንደሚከተለው እናየዋለን ፡
መነሻ ጥቅስ
ገላትያ 5 (Galatians)
22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
እነዚህ አሁን ከላይ የተጠቀሱት (በቋሚነት) ሰው በክርስቶስ ሆኖ አዲስ ሰው ከሆነ በኋላ የሚያገኘው ህይወት ነው ።
በመጽሃፍ ይህ ፍሬ የማይቆም እንደሆነ ሲናገር
መዝሙር 1 (Psalms)
3፤ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
እንዚህን ፍሬዎች ማግኘት የምንችለው እግዚአብሔር ወይም አዲሱ ሰው ላይ ብቻ ነው።በመጀመሪያ ሰው ተሳካልኝ ብሎ ስለስኬት ማሰብ ያለበት ፡በንብረት ፡በቁሳቁስ ሳይሆን ይህን ህይወት መለማመድ ሲጀምር ነው፡እኩይ የህነውን የጌታን አይነት ማንነት ፡በመንፈስ ፍሬ መልኩ ማግኘት እና መለማመድ ሲችል ነው።
እህቶች/ወንድሞች ሁሉ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት እንዲሆኑ እና ይህን ህይወት እንዲኖሩ የጌታ መሻት ነው። እያንዳንዱ የመንፈስ ፍሬዎች የራሳቸው ፍቺ እና አቅም በውስጣቸው ይዘዋል፡ልክ እያንዳንዱ መድሃኒት የራሱ የሆነ የማዳን አቅም እንዳለው፡ወይም ልክ እንደ ፍራፍሬ የራሱ የሆነ ጥቅም እንዳለው ሁሉ ፡የመንፈስ ፍሬዎችም የራሳቸው የሆነ አቅም ይዘዋል እያንዳንዱን እንመልከት።
22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
Galatians 5 (WEB) - ገላትያ
22: But the fruit of the Spirit is love, joy, peace, patience, kindness, goodness, faithfulness,
23: gentleness, and self-control. Against such things there is no law.
1.ፍቅር(love)
2.ደስታ(joy)
3.ሰላም(peace)
4.ትዕግስት(patience)
5.ቸርነት(kindness)
6.በጎነት(Goodness)
7.እምነት(faithfullness)
8.የውሃት(genetleness)
9.ራስን መግዛት(self-control)
እያንዳንዱን እንመልከት....
1ኛ. ፍቅር
እንግዲ ፍቅር ብለን ስንል የተለያዩ የፍቅር አይነቶች እንዳሉ ጥናቶች ያመለክታሉ
1.1. ፍቅር
#. storge---parental love which is protection(የቤተሰብ ፍቅር)
#.philia--brotherly love or friendly love(የወንድም/የጓደኛሞች ፍቅር)
#.Eros---which is Romantic love(የሴት እና የወንድ ፍቅር)
#. Agape---The love of God(የእግዚአብሔር ፍቅር)
በመጽሃፍ በገላ5፥22
ላይ የተገለጸው የፍቅር አይነት Agape or ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር አንድ አይነት (እኩይ)የሆነ ህይወት ነው::
ስለዚህ አዲስ ፍጥረት ሲሆን አንድ ሰው ይህን ፍቅር ነው።
የሚያፈራው ከላይ የተጠቀሱትን
የቤተሰብ ፍቅር፡የወንድም ፍቅር፡የሴት እና የወንድ ፍቅር የሚባሉትን በደንብ ለማጣጣም, Agape ወይም የእግዚአብሔር ፍቅር የሚባለውን እውነተኛ ፍቅር ማፍራት አለብን፡ይህን ለማፍራት ደግሞ በክርስቶስ መሆን አለብን::
ሃገር ሰላም እንድትሆን፡ትዳር ሰላም እንዲሆን፡ስራ ቦታ መከናወን የሚቻለው ፡እና ለሁሁሉም ነገር እውነተኛ የሆነውን የአዲሱ ሰው የመንፈስ ፍሬ ማፍራት አለብን።
ይህ ህይወት በክርስቶስ የሆነ ሁሉ ሊያፈራው የሚገባ ነው።
በክርስቶስ ላልሆናችሁ ወንድሞች/እህቶች አንድ ነገር መንገር እንፈልጋለን በክርስቶስ መሆን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም የምንለው ለዚህ ነው፡በክርስቶስ ለሆናችሁ፡በክርስቶስ፡እህት /ወንድሞች ሁላችሁም ይህ ህይወት መሰረታዊ እና አስፈላጊ ነው፡እንድታፈሩ የጌታ ጸጋ ይብዛላችሁ።
=============================
በቀጣይ ሳምንት
2ኛ. ሰላም (peace)
ከትምህቱ የተወሰደ
እውነተኛ እና የማይደፈርስ "ሰላም" ለፍተን የምናገኘው ሳይሆን በክርስቶስ በመሆን እና አዲስ ፍጥረት በመሆን የሚገኝ ነው።"
============================
በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን....
ብሩካን ናችሁ
Goodness Of Christ Gospel Minstry
እዮብ አበራ
718 viewsEjob @ JS, 03:21