Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ የGoodness of Christ Gospel Ministry ወዳጆች ዛሬም ከሳምንት | ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን 🌍

ሰላም ለእናንተ
የGoodness of Christ Gospel Ministry ወዳጆች ዛሬም ከሳምንት የጀመርነውን ትምህርት እንቀጥላለን…
የመንፈስ ፍሬ እና አዲሱ ሰው
2. የመንፈስ ፍሬ (ደስታ)
ገላትያ 5 (Galatians)
22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
Galatians 5 (WEB) - ገላትያ
22: But the fruit of the Spirit is love, joy, peace, patience, kindness, goodness, faithfulness,
23: gentleness, and self-control. Against such things there is no law.

ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው።ይህ አዲስ ፍጥረት ደግሞ የመንፈስ ፍሬዎች አሉት ከእነዚህም መካከል
ሁለተኛ የመንፈስ ፍሬ ብለን ያልነውን (ደስታ) ነው ብለናል ።ይህም የመንፈስ ፍሬ ቋሚ እንጂ በሁኔትዎች የሚፍረከረክ አደለም።
አማርኛ ---ደስታ
English---joy
Greek ------Chara
የሚለውን ፍቺ የሚይዝ ሲሆን ፡ጊዜያዊ የሆነ ፍሬ ሳይሆን ፡ከውስጥ የሆነ ደስታ፡ጥልቅ የሆነ የደስታ መንፈስ ፡በራስ መተማመን እሰከሚታይ ድረስ ያለ ማለት ነው።ይሄኛው አይነት ደስታ ሰዎች በሚያደርጉልን በጎ ነገር የሚመጣ ሳይሆን ለአዲሱ ሰው ፡እግዚአብሔር በቋሚነት የሰጠው ነው።እግዚአብሔር የሚታወቅበት ትልቁ ማንነት "ደስታ " ነው ።
ሮሜ 14 (Romans)
17፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት ....
የመንግስት መታወቂያው በመንፈስ ቅዱስ የሚሆን ደስታ ነው፡ይህን ደስታ ፡በአዱሱ ሰው ውስጥ አሳድሮታል።
እግዚአብሔር ለልጆቹ ወይም ለአዲሱ ሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የሚሰጠው ነው።
ሐዋ. ሥራ 13 (Acts)
52፤ በደቀ መዛሙርትም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።
Acts 13 (WEB) - ሐዋ. ሥራ
52: The disciples were filled with joy with the Holy Spirit.
በዚህ መልኩም ለደቀመዛሙርቱ ሲሞላቸው እናያለን።
1 Thessalonians 1 (WEB) - 1 ተሰሎንቄ
6: You became imitators of us, and of the Lord, having received the word in much affliction, with joy of the Holy Spirit,

ይህን ህይወት የተካፈለ ስለሆነ
የሚመጣ ሁሉ አያሳዝነውም የሚሄድም አያሳዝነውም፡ቋሚ በሆነ ደስታ ውስጥ ነው ሚኖረው አዲሱ ሰው።

ሰዎች ብዙ ጊዜ እከሌ ደስታዬን ቀማኝ ፡ደስታዬን ነጠቀኝ ሲል እንሰማለን ፡የሚቀማ ሰላም ካለክ አዲስ ፍጥረት ሆነክ ቋሚ ደስታ ያዝ ፡ይህ ደስታ በምንም ሁኔታ ውስጥ ሁን በውስጥክ ያለው ደስታ
ሐሴት ውስጥ እንድትሆን/ኚ ያደርጋል::

ስለዚህ እናተም በዚህ ቋሚ የደስታ ህይወት እንጂ ጊዜያዊ በሆነ የደስታ ህይወት ውስጥ እንድትሆኑ የጌታ መሻት አድለም ።
ለዚህ ነው በክርስቶስ መሆን ይጠቅማል ምንለው።
==============================
በቀጣይ ሳምንት
አዲሱ ሰው እና የመንፈስ ፍሬ
ክፍል ሶስት:- ሰላም(peace)
ሰላምን በዘፈን መልክ ስላዋዛሃት ወይም ፡በግጥም መልክ ስለገጠምካት የምትገኝ ሳትሆን ሰላም ራሱ እግዚአብሔር ነው።

አዲሱ ሰው በክርስቶስ ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር ስለታረቀ የራሱ የፈጣሪው "ሰላም"ነው ያለው።
ከክፍል 3 የተወሰደ፡በቀጣይ ሳምንት ይጠብቁን
===============================
ብሩካን ናችሁ
Goodness of Christ Gospel Ministry
እዮብ አበራ!