2023-02-03 06:00:08
ሰላም ቅዱሳን ክፍል አራት....
እንግዲ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፡ይህ አዱስ ተደርጎ የተፈጠረው ሰው የመንፈስ ፍሬ ደግሞ አልፎም በስጋ ህይወት ላይ የሚገለጥ ህይወት አለው ብለናል።
መነሻ ጥቅስ ፥- ገላ 5፥22
ገላትያ 5 (Galatians)
22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
አዲሱ ሰው እና የመንፈስ ፍሬ
4.ትዕግስት
Greek translation....Makrothymia
English Translation...pacience
አማርኛ ፍቺ.....መታገስ
በክርስትያን ህይወት ውስጥ ባህሪ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ባህሪያችን በተሰራ መጠን በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ጠቃሚነታችን ይጨምራል ለብዙዎችም በረከት እንሆናለን፡፡
ባህሪያችንን ባሳደግን መጠን ደግሞ በእግዚአብሀሔር መንግስት ውስጥ ያለን ተፅእኖ ይጨምራል እግዚአብሄርም ለተጨማሪ ሃላፊነት ያምነናል፡፡ እግዚብሄር ክብሩን ሊገልጥብን በህይወታችን በትጋት ይሰራል፡፡
አንዳንዴ የእግዚአብሔር አሰራርና የኛ አስተሳሰብ አንድ ላይሆን ይችላል፡፡ መታገስ እና እግዚአብሔርን መጠበቅ የሚያስፈልገው የእግዚአብሔር አሰራርና የእኛ ፍላጎት ሁልጊዜ አብሮ ላይሄድ ስለሚችል ነው፡፡
የእግዚአብሔርን እውነተኛውን ነገር ማግኘት ከፈለግን እግዚአብሔርን መከተል አለብን ሌላ መንገድ የለውም፡፡ እግዚአብሔር የራሱ እርምጃ አለው፡፡ እግዚአብሔር በእኛ ፍጥነት አይገባም፡፡ ስለዚህ ነው ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ለመኖርና ለማፍራት ትእግስት ወሳኝ የሚሆነው፡፡
የእግዚአብሔርን እርምጃ ሳንጠብቅ የምናደርገው ነገር የእኛ እንጂ የእርሱ አይሆንም፡፡
በህይወታችን እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን ሰውንም መታገስ ይገባናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ደረጃ እና አመለካከት አለው፡፡ ከሰው ጋር አብሮ ለመኖርና ለማገልገል በዚያም ፍሬያማ ለመሆን ትግስት ይጠይቃል፡፡ ሰው ሁሉ እኛን ይምሰል ማለት ትእቢት ነው፡፡ ሰውን መታገስ ግን ትህትና ነው፡፡
ማንኛውም ሃይል ካለመቆጣጠሪያ መሳሪያው አደገኛ እንደሆነ ሁሉ ባህሪው ያልተሰራ ሰው አደገኛ ነው፡፡ ባህሪው ያላደገ ሰው ራሱን ተቆጣጥሮ ሃይሉን በምን ላይ ማፍሰስ እንዳለበት አያውቅም፡፡ ለዚህ ነው ከሃይል ይልቅ ባህሪ ይበልጣል የሚባለው፡፡
ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። "ምሳሌ 16፡32"
በህይወታችን ልናሳድገው የሚገባን ባህሪ ትግስት ነው፡፡ እግዚአብሔር በህይወታችን በትጋት እየሰራ ያለው ትእግስትን ነው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ "ሮሜ 5፡3-4"
ካለ ትእግስት ግን ምንም ነገር ቢኖረን ከንቱ ነው፡፡ ትእግስት ሙሉ እና ፍፁም ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀን ፍፁም ሰዎች ያደርገናል፡፡
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ
ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ
ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን
ይፈጽም። "ያዕቆብ 1፡2-3"
አዲሱ ሰው በዚ ማንነት ውስጥ የተፈጠረ ደግሞ ያደገ ነው።ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ መሆን ይጠቅማል የምንለው ለዚህ ነው።
ሃገር የምታረፈው ታጋሽ መሪ ሲኖር ነው፡ቤተሰብ የሚያርፈው ታጋሽ ሰው መሆን ስንችል ነው፡ሁሉ በዚህ መንፈስ ሲሆን ብዙ ሰላም ይበዛል።ይህን ለማግኘት ደግሞ በክርስቶስ ሆኖ አዲስ ማንነት መያዝ ያስፈልጋል ።
===============================
በቀጣይ ሳምንት
አዲሱ ሰው እና የመንፈስ ፍሬ
ክፍል 5.ቸርነት (Kindness)
===============================
ብሩካን ናችሁ
Goodness of Christ Gospel Ministry
Powered by እዮብ አበራ
#የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ትዕግስት#....
900 viewsEjob @ JS, edited 03:00