Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ቅዱሳን ዛሬ ከባለፈው የቀጠለውን ክፍል እናያለን መጽሃፍ ቅዱስን በዘመን ከፍለን ማጥናታችን | ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን//Heaven Gift Church//

ሰላም ቅዱሳን ዛሬ ከባለፈው የቀጠለውን ክፍል እናያለን መጽሃፍ ቅዱስን በዘመን ከፍለን ማጥናታችን ፡ነቀፋ የሌለበት ፡እና እውነተኛ የሆነው የቅዱስ እግዚአብሔርን ህይወት ለመኖር ፡በክርስቶስ የተሰራውን እውነት ተረደቶ ለመመላለስ ይጠቅማል ።
የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል
2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy)
15፤ የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
2 Timothy 2 (WEB) - 2 ጢሞቴዎስ
15: Give diligence to present yourself approved by God, a workman who doesn't need to be ashamed, properly handling the Word of Truth.
(study)
የሚለውን ሃሳብ የያዘ ሲሆን
ትክክለኛ የሆነ ኑሮን ለመኖር ይጠቅማል።

መጽሃፍ ቅዱስ በሰጠናችሁ ቻርት መሰረት በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን ብለናል

1.ያለፉት ዘመናት( ኤፌ 2፥11)
2.የአሁኑ ዘመን (ኤፌ2፥13)
3.የወደፊቱ ዘመን (ኤፌ2፥7)

ኤፌ2፥7-14
ኤፌሶን 2 (Ephesians)
6-7፤ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።
8፤ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
10፤ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።
11፤ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤
12፤ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።
13፤ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።
Ephesians 2 (WEB) - ኤፌሶን
7: that in the ages to come he might show the exceeding riches of his grace in kindness toward us in Christ Jesus;
8: for by grace you have been saved through faith, and that not of yourselves; it is the gift of God,
9: not of works, that no one would boast.
10: For we are his workmanship, created in Christ Jesus for good works, which God prepared before that we would walk in them.
11: Therefore remember that once you, the Gentiles in the flesh, who are called "uncircumcision" by that which is called "circumcision," (in the flesh, made by hands);
12: that you were at that time separate from Christ, alienated from the commonwealth of Israel, and strangers from the covenants of the promise, having no hope and without God in the world.
13: But now in Christ Jesus you who once were far off are made near in the blood of Christ.

1.ያለፉት ዘመናት
(ኤፌ 2፥11)
11፤ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤
12፤ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።

በዚህ ዘመን የተጻፈው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል በቀጥታ ተደራሽነቱ፡ለአህዛብ አደለም ነገር ግን ለትምህርታችን ተጽፏል::
ያ ማለት መጽሃፍ ቅዱስን ከመጀመሪያው ጀምረን እስከ የሽግግር ጊዜ እስከምንለው የሐዋርያት ስራ ድረስ በቀጥታ አህዛብን የሚመለከት አደለም ፡ግን ለትምህርት ተጽፈዋል::

አህዛብ ስንል አህዛብ እኛን ማለት ነው ፡ወንጌለልልን በሐዋርያው ጳውሎስ ያገኘነው ማለት ነው።

በነዚህ ዘመናት ለእስራኤል ኪዳን የተገባላት,ቅነሳ የተደረገበት እንደአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን መልእክት ከተደራሽነት አንጻር አይሁድን እንጂ ፡አህዛብን አይመለከትም ሆኖም ግን ለትምህርታችን ተጽፏል ይህም ማለት

ለምሳሌ
ሁለት ጓደኛሞች ቢኖሩ እና አንደኛው ትልቅ ስህተት አድርጎ ቢሂን እና አብረው እያሉ አባትየው መትልጥቶ ያጠፋውን ልጅ ቢቆጣ ፡ወይንም ቢቀጣው ።
ጥፋቱን ያጠፋው ልጅ ቀጥታ ተደራሲ ሲሆን
ሁለተኛው ልጅ ደግሞ ከእሱ የሚማር ይሆናል;:

በመጽሃፍም እንዲህ ነው የሆነ ስለዚህ
በዘመናት መካከል ያለ የተዛባ እውቀት በዚህ መልኩ መስተካከል አለበት::

በብሉይ ኪዳን ቃል እየመዘዙ መተንበይ፡ይሁን ሌላም ሌላም በድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው።

ትክክለኛውን ህይወት መኖር የሚጀምረው ትክክለኛውን እውቀት በመያዝ ነው።

በክርስቶስ ሆኜ አዲስ ፍጥረት ነኝ ለሚል ይሄ በደንብ ሊረዳው ይገባል።

ታዲያ ያለፉት ዘመናት ብለን የምንለው እኛን በቀጥታ የማይመለከተን ከሆነ፡በቀጥታ እኛን ተደራሲ የሚያደርገው ክፍል የትኛው ነው?
===============================
በቀጣይ ሳምንት
ያሁኑ ዘመን ለማን ተጻፈ?የወደፊቱስ ማንን የሚያመለከት ነው?
===============================
ለተጨማሪ ጥያቄዎች-0966222852
Or Inbox us on Telegram (https://t.me/joinchat/AAAAAFMzwMKEzglqqR6tnw)
Powered by እዮብ አበራ
Goodness of Christ Gospel Ministry