Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ቅዱሳን ዛሬ ከባለፈው የቀጠለውን ክፍል እናያለን መጽሃፍቅዱስ በዘመን ከፍሎ ካልተጠና | ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን//Heaven Gift Church//

ሰላም ቅዱሳን
ዛሬ ከባለፈው የቀጠለውን ክፍል እናያለን
መጽሃፍቅዱስ በዘመን ከፍሎ ካልተጠና ፡እንደተደራሲ ማግኘት የሚገባንን ህይወት እና የተካፈልነውን ህይወት መኖር ያስቸግረናል ስለሆነም መነሻ አድርገን
2ጢሞ 2፥15 /1ቆሮ 15፥3-4...መጽሃፍ እንደሚል አንስተናል::

ሃዋርያው ጳውሎስ ፡የማያሰፍር ሰራተኛ ለመሆን መጽሃፍ በሚገባ ከፋፍሎ እንዲያጠና ለጢሞቲዮስ ሲያስረዳው እናያለን::
ከዚያም ባሻገር በዚሁ ክፍል ላይ ሙታን ትንሳኤ ሆኗል በሚል የስህተት ትምህርት ሄሚኖስ እና ፊልጦስ ለእምነት የሚሆንን እውቀት ሲያበላሹ እናያለን::

አንድ አገልጋይ "መተተኛይቱ በህይወት እንድትኖር አትፍቀድላት "የሚል አውድ ያልጠበቀ ጥቅስ በማንበቡ እየዞረ መተተኛ ሰዎችን ሲገል ነበር::
በዘመኑ ሄዶ እውነቱን ካልተረዳ ልክ ያልሆነ አድራጎት ነው።ሰዎች እንዲገደሉ የጌታ ፈቃድ አደለም ፡ለማን ተጻፈ ብለን ማሰብ ይጠበቅብናል።

ስለዚህ በክፍል 2 ጊዜታችን
1 ያለፉት ዘመናት የሚባል እንዳለ እና የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሉ (ከዘፍ-ሚል/ማቴ-ዩሐ) ድረስ የሚገኘው ክፍል ያለፉት ዘመናትን የሚጠቁም እና ለትምህርታችን የተጻፉ ናቸው ብለና ቀጥታ እኛን የሚመለከት እንዳለሆነ አንስተናል::

የአሁን ዘመን
ኤፌ 2፥13
የአሁን ዘመን የምንለው በቀጥታ ተደራሲ የሚሆነው ለአህዛብ (ለእኛ ነው ደግሞም ለትምህርታችን ነው)
የሚጀምረውም(ከሐዋ ስራ ም 15 እስከ ፊሊሞና መጽሃፍ )ይሆናል::
በተለምዶ አጠራሩ "የጸጋ ወንጌል"የሚባልበት ዘመን ነው።
እዚህ ዘመን ላይ ጸጋ እና ሰላም በግልጽ የተገለጠበት፡የበዛበት ዘመን ይባላል(ሮሜ 11፥25)
ወንጌል ላልተገረዙት የሚል እንቅስቃሴ የታየበት(ገላ 2፥7)
የጸጋ ወንጌል የሚል እንቅስቃሴ የተጀመረበት (20፥24)
በማየት ሳይሆን በእምነት የሚንቀሳቀስበት ዘመን ማለት ነው::

የአሁኑ ዘመን በአጠቃ ላይ (REVLATION OF MYSTERY) ሚስጥር የተገለጠበት ዘመን ማለት ነው።
ይህ ዘመን ላይ ሁሉ ተጠቅልሎ የሚሰራው ለመልካም ፡ይህ ዘመን የሚሰራው በክርስቶስ ላይ ባለን እምነት እንጂ የነህምያ መጽሃፍ ተጠቅሶ በሚተነበይ ትንቢት ወይንም፡ዘይት ምርት ስራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች የሚሰራልህ/ሽ ህይወት የለም ::

ሰው ቸርች ሄዶ፡ወይንም ከወድሞች ጋር ሲሆን የሚገለጥ የክርስቶስ የጸጋ ህይወት እንጂ በየቤተክርስቲያን እየዞርክ ትንቢትየምትቀበልበት ህይወት አደለም::

ወደረፍት የገባ ህይወት መድረክ ላይ በሚያገለግል አንድ ጸጋ በሚሰራበት ሰው አዲስ ህይወት አይሰጠውም ህይወቱ በእናንተ ይሰራል በገንዘብ የሚገዛ ፈውስ የለም ፍውውሱ በእናንተ ይሰራል የአሁኑ ዘመን ህይወት ጸጋው አብልጦኑ የሚሰራበት ነው
ትግል ሳይሆን ህይወት ሰጪው መንፈስ እንዲሰራ በማመን የሚገለጥ ህይወት እንጂ አቶ እከሌ የጸለዩበትን ዘይት በመጠታት የሚሰራ ህይወት አደለም::

የክብር ተስፋ ያለው እየሱስ በእናንተ ውስጥ ሆኖ የሚሰራበት ዘመን ነው፡ታዲያ ይህ ዘመን በዚህ መልኩ ከተረዳን እንዴት እንመላለስ?....ይቀጥላል
===============================
በቀጣይ ሳምንት
የወደፊት ዘመን(ኤፌ 2፥7)
===============================
ለተጨማሪ ጥያቄዎች-0966222852
Or Inbox us on Telegram (https://t.me/joinchat/AAAAAFMzwMKEzglqqR6tnw)
Powered by እዮብ አበራ
Goodness of Christ Gospel Ministry