Get Mystery Box with random crypto!

ሀሁ መፅሐፍት ኦንላይን ሽያጭ( Hahu books online sales)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fanab123 — ሀሁ መፅሐፍት ኦንላይን ሽያጭ( Hahu books online sales)
የቴሌግራም ቻናል አርማ fanab123 — ሀሁ መፅሐፍት ኦንላይን ሽያጭ( Hahu books online sales)
የሰርጥ አድራሻ: @fanab123
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.61K
የሰርጥ መግለጫ

የሚፈልጉትን ማንኛውንም መፅሐፍት ካሉበት ቦታ እናመጣልዎታለን
በ 0911006705 ደዉለዉ ይዘዙን
አድራሻ፡ስታዲየም ናሽናል ታወር ግራዉንድ ላይ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-14 14:03:23
360 views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 14:03:18 አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
+ + + + + + + + + + + + + +
ሰላም ለ’ናንተ ይሁን ውድ ቤተሰብ!!!  የሚፈሩና በይሉኝታ የሚታለፉ ብሎም ጠለቅ ያሉ ርዕሶች ዙሪያ እየተሽከረከረ ሁለንተናዊ ልዕልና ያለው ሰብዕናዊና ሕብረተሰባዊ እድገት እንዲኖር እንደሚተጋ የሚታወቀው ኢ/ር እንዳላማው አራጌ ሁለተኛ መጽሐፉን አሳትሟል። ኢንጅነሩ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምኅንድስና መምህር፣ የነገረ-ሕይወትና የነገረ-ኢትዮጵያ ተመራማሪ ብሎም የኒትሮ ምሕንድስና ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ መስራች መሆኑን መጽሐፉ ላይ የተቀመጠው መረጃ ያሳያል። ኢንጅነሩ በራሱ ማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ እንዳሳወቀን፡ የመጀመሪያ መጽሐፉ ከሆነው «ግንጥል ልዕልና በኢትዮጵያ ልደት» በኋላ በነበሩት ያለፉት አራት አመታት አራት መጽሐፍትን የደረሰ ሲሆን እነኝህን ስራዎች በተከታታይ ሊያቀርብ መዘጋጀቱን አሳውቋል። የእነኝህ ስራዎቹ ቀዳሚ አሁን የታተመው «ራኤል» ቁጥር-1 ነው። ለዚህ ስኬቱ ደራሲውን እንኳን ደስ ያለህ እያልን ከእኛ ጋር አብሮ ለመስራት ስለመረጠንና መጽሐፉን እንድናከፋፍል ስለቻልን ያለንን አክብሮትና የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን።
 
ስለሆነም፡ ሀሁ  መጽሐፍት መደብር መጽሐፉን በያላችሁበት ለማድረስ ዝግጁ መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነው። በሀገሪቷ የተለያዩ ቦታዎች ያላችሁ መጽሐፍት መደብሮች ከዚህ በታች ባለው አድራሻችን መሰረት ብታገኙን መጽሐፉን እናደርሳችኋለን። ከሰኞ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ መጽሐፍት ቤቶች ሁሉ የምናደርስ ይሆናል። እንዲሁም ከስር በተጠቀሱት አድራሻዎች መሰረት በእኛ መደብሮች መጽሐፉን ታገኙታላችሁ። አንብቡት፡ ብዙ እንደምታተርፉበት እምነታችን ነው! ስለ መጽሐፉ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከስር ይመልከቱ↓
 
አድራሻ፦  
መደብር ቁ.1፡ አ.አ. ናሽናል ታዎር
መደብር ቁ.1፡ ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ.  09 11 00 67 05
ሀሁ  መጽሐፍት መደብር - አዲስ አበባ
************
ስለ መጽሐፉ….
********
ደራሲው ስለ ሁለተኛ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፡-
       «ሁለተኛው መጽሐፌ» እንደ ስሙ ‹‹ራኤል›› ነው፤ ምን ማለቴ እንደሁ ስታነ’ቡት ታወቃላችሁ።»
 
እንዲሁ፡ የደመወዝ ጎሽሜ «ዓሥራ ሥድሥት» የተሰኘው መጽሐፍ የሽፋን ገጽ ላይ ምስክርነት የሰጠው የ‹‹እግዚእ፡ The Wisdom Compass to Eternal Life›› መጽሐፍ ደራሲ አቤል ጋሼ በተመሳሳይ ዘውግ ውስጥ ስላለውና በብዙ ሀሳቦች ስለታጨቀው ይህ የመኃንዲሱ መጽሐፍ እንዲህ ሲል የሽፋን የጀርባ ሽፋን ገጽ ላይ ምስክርነት ሰጥቷል፡- ↓
//«ይኸ ደራሲ ምሥጢር ይወዳል። ምሥጢር ይፈልጋል፤ ምሥጢር ያገኛል። በምሥጢር ይናገራል። ይፈላሰፋል፣ ይመረምራል። “ግንጥል ጌጥ በኢትዮጵያ” በሚል ኮርኳሪ ጽንሰ ሃሳብ የመጀመሪያ መጽሐፉን ያስነበበን ደራሲ ኢንጂነር እንዳላማው አራጌ፡ ዛሬም “ራኤል” በሚል ሌላ ምሥጢራዊ ጽሁፍ ውስጥ የሚገርሙ የሚታየውንና የማይታየውን አለም ምሥጢራት ኢትዮጵያን ባማከለ ሁኔታ ይዞልን ቀርቧል። ጊዜው እንደሚጠይቀው ደራሲው የትውልዱ ምልክት ነው። አጠያቂ ነው፣ ራሱን ከመንጋ አስተሳሰብ ለይቶ በተሰጠው ችሎታ ስለ ነገረ ፍጥረት፣ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሰውነት ያስባል፡ ይመረምራል። ስለ ሀገሩ መንፈሳዊ ዕጣ ፈንታ ያጠይቃል። ፈጣሪ አለምን የፈጠረባቸውን አይነተኛ እሳቤዎችና ምልክቶች በቁጥር ቀመርና ስሌት ያሰላስላል፤ ጊዜንና የፍጥረትን ብሂል ይመረምራል። በኢትዮጵያ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የተደበቁ ጥንታዊ መጻሕፍትና ድርሳናት ውስጥ ተደብቀው የሚኖሩ ብዙ ምሥጢራት እንዳ’ሉ የሚያምነውና ራሱን “የጥበብ ብላቴና” የሚለው ይህ ደራሲ፡ እነዚህ የጥበብ ዘለላዎችን ከብዙ አለማት ጎትቶ ያመጣና ትረካውንና ፍለጋውን ግን የምሥጢራት ማዕከል ከሆኑት “ቅዱሱ ሀይቅ” በሚለው የጣና ሀይቅ ደሴቶችና የወሎ ቅዱሳን መካናት ላይ ያነጣጥራል። ጠቢባንን ፈልጎ መንፈሳዊ እውቀትን ይጎለጉላል። 
ከዚህ በፊት ጥበብን በመሻት ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ አምቃ የያዘቻቸውን ምሥጢራት የመረመሩት አንጋፋ መርማሪዎችን እነ የኔታ አስረስ የኔሰው፣ እነ መራሪስ አማን በላይ ሌሎችም እንደነሱ ያሉ የሰሯቸውን ሥራዎች አንብቦ ያገኘውን ከርሱ ምልከታና አጠይቆ ጋር አሰናስሎ፡ ይልቁንም በሳይንስ እውቀት ያዳበረውንና ከብዙ ቦታ የለቀማቸውን የጥበብ ነጠብጣቦች፡ በአስገራሚ ትንታኔ ውስጥ አካትቶ ያሳየናል። የዚችን አለም አሰራር በመንፈሳዊ ዓይን ለሚመለከትና “የዚች አለም ምሥጢሯ ምን ይሆን?” ለሚል ተመራማሪ፡ ይህ ድርሰት ብዙ የሚያስብበት ሃሳብን ያቀርብለታል። ኢትዮጵያ ምሥጢር ነች። ሥጦታዋም መንፈሳዊ እሴቶች ናቸው። የእግዚአብሔር የጥብበ ጎተራ ነች ብሎ የሚያሳስብ ጽሁፍ ነው። ፊዚክስ፣ ቲኦሎጅ፣ ስነ ከዋክብት፣ አስትሮኖሚ፣ ነገረ ድኅነት በክርስትና እምነት ... ወዘተ… ሁሉም አብረው በዚህ ጽሁፍ ይ’መረመራሉ። ‹‹ግን ትውልዱ ይኸንን አያውቅም። የኢትዮጵያን ስጦታ ያውቃል?›› ጽሁፉ ትውልዱን ይሞግታል። ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያን ምሥጢር እንዲመረምር በኅሊና ጅራፍ ሊገርፍ ተነስቷል! 777 ቁጥር በመጀመሪያ መጽሐፉ ላይ ጎልቶ እንደወጣው ዛሬም በዚህ መጽሐፍ ይንከባለላል። ሌሎች የቀመር ትንታኔዎችን ተጠቅሞ ሰማያዊውን አለም ከሰው ማንነት ጋር እያሰናሰለ የመጨረሻውን ዘመንና የድኅነትን አንድምታ ያመሰጥራል። ቀመር ለሚወድ ይኸ ደራሲ እስኪጠግብ ድረስ ያጠጣዋል።
ደራሲው ስለክርስትናም ያጠይቃል። “በክርስቶስ ሁሉን እንችላለን” የሚለው ታላቅ አዋጅ እውን እንዲሆን ‹‹መክሊታዊ ክርስትና›› ያስፈልጋል ብሎ ይሰብካል። ብላቴናው ጥረቱ ሁሉ ለሀገሩ አንድ መልካም ነገር ማድረግ እንደሆነ በጽሁፉ ውስጥ መመልከት ይቻላል። በጠቅላላ በድርሰቶቹ ውስጥ እንደሚንጸባረቀው፡ ‹‹እንዴት ከገባንበት አረንቋ እንውጣ?›› የሚል ጭንቀት በውስጡ የሚዝመነመን መሆኑን መገመት አያዳግትም። በጽሁፉ ውስጥ ለሱ መልሱ አንድ ነው። ብላቴናው እንዲህ ይላል፡-
“ከግንጥሉ ‹‹የድኅነት ብቻ ክርስትና›› ወደ ሞገሳማው ‹‹መክሊታዊ ክርስትና›› መሸጋገርና ከቅድስተ ቅዱሳን እልፍኝ መቋደስ አ’ለብን። አሁን ካለንበት ሁለንተናዊ የሰብዕና ቀውስ ለመውጣትና ሀገሪቷን ብሎም ዜጎቿን በትንሳኤው ዘመን ለሚጠበቅባቸው ሀላፊነት ለማዘጋጀት፡ በተድበሰበሰው “ተሀድሷዊ የለውጥ መንገድ” ሳይሆን በትክክለኛዋ “ንስሓዊት የለውጥ መንገድ” መጓዝ አ’ለብን።” 
ይኸ ደራሲ በመንፈሳዊ ቀመር እያሟሸ፣ በአዳዲስ ጽንሰ ሀሳቦች የአመክንዮ ሥርአታችንን ያጭራል። ትውልዱን ይሞግታል። ለሀገር ልዕልና የሚበጀውን መንገድ ይጠቁማል። ግንጥል ጌጥ ይዞ ሀገር እንደማይቆም አጥብቆ ይመክራል። በነፃነት አስበን ወደ ጥበብ-ተዋህዶ እንሻገር ይላል። ‹‹የተሟላ ሀገራዊ ልዕልና እንዴት ይገኛል?›› ያነበበ ሃሳቡን ይ’ረዳል። አንብቦ ደግሞ የራስን አስተሳሰብ ለማዳበር እድል ያገኛል። በርግጥም ይኸንን ጽሁፍ ያነበበ በአያሌው ያተርፍበታል። እኔ ብዙ አትርፌበታለሁ። መልካም ንባብ።»//
********************
ይነበብ!  
ሀሁ  መጽሐፍት መደብር - የመጽሐፉ አከፋፋይ
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
 
 
335 views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 15:45:45
511 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 15:45:42 "ኦርቶጵያ"
በቄስ ዶክተር ጆን ቢንስ ተፅፎ በራሴላስ ጋሻነህ የተተረጎመ።

ክርስትናና ኢትዮጵያ እንደምን ተዋወቁ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
ለኢትዮጵያ ፓለቲካ፣ ባህል፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ምን አበረከተች? ምንዳዋስ ምን ሆነ?
ቤተ ክርስቲታኒቱ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች? ጥርስ ውስጥ ያስገባት የ 2000 ዓመት ጉዞና መጪው ፈታኝ ጊዜ፣ እንዲሁም ተስፋዋስ ምንድነው? የሚሉትና መሰል ሀገራዊ እና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች በስፋት የተዳሰሱበት መፅሐፍ ነው።

ፀሀፊው ዶክተር ጆን ቢንሰን በካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ጥናት ማዕከል ተጋባዥ ፕሮፌሰር እንዲሁም በካምብሪጅ የምትገኘው የታላቋ ቅድስት ድንግል ማርያም ቄሰ ገበዝ ናቸው።

ብዙ ጊዜ በውጭ ሀገራት ፀሀፊዎች ስለኢትዮጵያ እና ስለ ቤተክርስቲያን የተፃፉ መፃህፍት አንዳንዶቹ ላይ የማስተውለውን የታሪክ ክፍተት አላየሁበትም። እንዲያውም ግሩም በሆነ አተራረክ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክትስቲያን ታሪክ፣ ሥነ-መለኮት፣ ጥነተ ታሪክ፣ አሁናዊ ተግዳሮት፣ መፃኢ ተስፋ እና ለቤተ ክትስቲያኗ ያላቸውንም ልባዊ ፍቅር ያየሁበት ነው።

የእንግሊዘኛውን ቅጂ PDF ከአሳታሚው ለማግኘት ችያለሁ፤ “The Orthodox Church of Ethiopia History” by John Binns
አመሰግናለሁ።
ተርጓሚው በጥሩ ሁኔታ አቅርቦታል።

ነፃ ምልከታዬ ነው።
ሰሞኑን ቦሌ አካባቢ የሚገኝ ጋዝ ስቴሽን ነዳጅ ለመቅዳት ወረፋ ይዤ መፅሀፍ ከሚሸጥ ወንድም ነው የገዛሁት።
አንብቤው ስለወደድኩት በንባብ ክረምታችሁን ዘና እንድትሉበት ለመጋበዝ ነው።

መልካም ቀን!
#እናንብብ! #እናብብ
#readingislife
#history
#ethiopiaorthodoxtewahdochurch
Meseret Mebrate

ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ .09 11 00 67 05
465 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:37:43
412 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:37:28 ሀሁ መጽሐፍ መደብር

ንባብ ለህይወት የመጻሕፍትና የትምህርት ተቋማት አውደርእይ ቁጥር 1 አዳራሽ ላይ እንገኛለን

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል

ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ O2

መግቢያ በነጻ
ለበለጠ መረጃ 0911006705
386 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:36:31
349 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:36:11 የቀን ወጣልን ፖለቲካ ~ መጽሐፍ ይመረቃል!

#Ethiopia | በበሪሁን አዳነ የተፃፈው "የቀን ወጣልን ፖለቲካ" መፅሐፍ ነሃሴ 1/2014 ዓ/ም ጎንደር ከተማ ሮዚዮ ሆቴል ይመረቃል።

በዚህ ፕሮግራም በአንድ በኩል የማኅበረሰቦችን ማንነት ያከበረ እና በሌላ በኩል የአገር አንድነትን ያፀና አንድነት ምን መምሰል እንዳለበት እንዲሁም ስለ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሐሳቦች ይቀርባሉ፥ ውይይትም ይካሄድባቸዋል።

***

"የቀን ወጣልን ፖለቲካ"

በበሪሁን አዳነ

መጽሐፉ የአገራችን ፖለቲካ "የጎርዲያን ቋጠሮ" ሆኗል ስለሚባለው የአገረ መንግሥትና ብሔረ መንግሥት ግንባታ እንዲሁም ከእሱ ጋር ተያይዞ ስለመጣው የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ የሚያትት ነው።

ደራሲው ከዚህ ቀደም (በ2007 ዓ.ም) "በምርኮ የተያዘ ሕዝብ፡- የአውራ ፓርቲ ሥርዓት ወይስ የአፈና አገዛዝ?" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ አብቅቷል።

መጽሐፉ 221 ገጾች የተቀናበረ ሲሆን በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል።
366 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 06:59:12
553 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 06:59:08 ኃያሉ ሊቀ መላእክ ቅዱስ ገብርኤል በሐምሌ ፲፱ ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ ከእሳት ያዳነበት ነው።

ቅድስት ኢየሉጣ በሮም ግዛት በሚገኝ አንጌቤን በሚባል አገር በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በክርስትና ሃይማኖትና በበጎ ምግባር ጸንታ ትኖር የነበረች ደግ ሴት ናት፡፡ ቂርቆስ የሚባል ሕፃን ልጅም ነበራት፡፡ ይህቺ ቅድስት የዘመኑን አረማዊ መኰንን እለእስክንድሮስን በመፍራቷ ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ በተሰደደች ጊዜ መኰንኑ እነርሱ ከሚገኙበት ሀገር ገብቶ ክርስቲያኖችን እያሳደደ መግደል ጀመረ፡፡ የንጉሡ ወታደሮችም እግዚአብሔርን እንዲክዱ፤ ለጣዖት እንዲሰግዱ ቅድስት ኢየሉጣንና ቅዱስ ቂርቆስን አስፈራሯቸው፡፡ ቅዱሳኑ ግን ሃይማኖታቸውን ለመለወጥ ፈቃደኛ አልሆኑም ነበር፡፡ በዚህም መኰንኑ ተቈጥቶ በዓይንና በአፍንጫቸው ውስጥ ጨውና ሰናፍጭ በመጨመር፣ በጋሉ የብረት ችንካሮች በመቸንከርና መላ ሰውነታቸውን በመብሳት በብዙ ዓይነት መሣሪያ አሠቃያቸው፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የጋሉ ብረቶችን እንደ ውኀ ያቀዘቅዝላቸው፤ ሥቃያቸውንም ያቀልላቸው ነበር፡፡

በሌላ ጊዜም በገመድ አሳሥሮ ንጉሡ ሲያስጨንቃቸው ከቆየ በኋላ ራሳቸውን ከቆዳቸው ጋር አስላጭቶ እሳት አነደደባቸው፡፡ ዳግመኛም ከትከሻቸው እስከ እግራቸው ድረስ በሚደርሱ ችንካሮች ቸነከራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ከሥቃያቸው አድኗቸዋል፡፡ አሁንም ቀኑን ሙሉ በልዩ ልዩ የሥቃይ መሣሪያዎች ቢያስጨንቃቸውም የእግዚአብሔር ኃይልና የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አልተለያቸውም ነበርና ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም፡፡ እንደ ገናም በመጋዝ ሰንጥቀው በብረት ምጣድ በቆሏቸው ጊዜ ጌታችን ከሞት አስነሣቸውና በመኰንኑ ፊት ድንቅ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከተአምራቱ መካከልም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ የመኰንኑን ጫማ በጸሎት ወደ በሬነት እንዲቀየር ማድረጉ ተጠቃሽ ሲሆን፣ መኰንኑ በተአምራቱ ተቈጥቶ የቅዱስ ቂርቆስን ምላስ አስቈርጦታል፤ ጌታችንም ምላሱን አድኖለታል።

ዳግመኛም በፈላ የጋን ውኃ ውስጥ ቅዱሳን ቂርቆስና ኢየሉጣን ሊጨምሯቸው ሲሉ ቅድስት ኢየሉጣ በፈራች ጊዜ ቅዱስ ቂርቆስ ‹‹እናቴ ሆይ አትፍሪ፤ አናንያ፣ ዓዛርያና ሚሳኤልን ከእሳት ነበልባል ያዳናቸው እግዚአብሔርእኛንም ከዚህ የፈላ ውኀ ያድነናል›› እያለ ያረጋጋትና በተጋድሎዋ እንድትጸና ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ተያይዘው ወደ ጋኑ ውስጥ ገቡ፡፡ ውኀም እንደ ውርጭ ቀዘቀዘ፡፡ ደግሞም ወታደሮቹ መንኰራኵር ባለበት የብረት ምጣድ ውስጥ አስገብተው ሥጋቸው እስኪቈራረጥ ድረስ በጎተቷቸው ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል አድኗቸዋል፡፡ በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተቀብለው በመንፈቀ ሌሊት አንገታቸውን ተቈርጠው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ እስከ ሞት ድረስ በታመኑበት ተጋድሏቸውም ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወትን አክሊል ተቀብለዋል።
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሐምሌ፣ ድርሳነ ገብርኤል፣ ገድለ ቂርቆስ ወኢየሉጣ

የቅዱስ ገብርኤል፣ ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ ጸሎታቸው፣ ምልጃቸው አይለየን!

ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 09 11 00 67 05/09 24 40 84 61
485 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ