Get Mystery Box with random crypto!

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhiba — Abu Hiba (አቡ ሒባ) A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhiba — Abu Hiba (አቡ ሒባ)
የሰርጥ አድራሻ: @abuhiba
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.94K
የሰርጥ መግለጫ

❶. የመልካም ቀደምቶቻችንን ፋና በመከተል እስልምናችንን የምንማማርበት፣
❷. ሐዲስ እና ቁርኣናዊ ፁሁፎች፣
➌. እንዲሁም በየቀኑ አጫጭር የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን ያገኙበታል!
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ:
👇
@AbuHiba45

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-22 05:55:19 ቀዷና ሸዎል
▬ ▬ ▬ ▬
እንደሚታወቀው የሸዎል ፆም ዛሬ አንድ ብለናል፣ ብዙዎች ሸዎል ከዒድ በሓላ ያለችው ስደስቷ ቀን ብቻ ትመስላቸዎለች ነገር ግን አይደለም፣
*
ይህ የያዝነው የሸዎል ወር እስከሚያልቅ ድረስ 6ቱን ቀን መፆም ይቻላል፣ ይሁንእንጅ ብዙ ሰዎች ቀዷ እያለባቸው ሸዎልን ሲያስቀድሙ ይታያል ይህ ስህተት ነው፣

በተለይ እህቶቻችን መጀመሪያ ግዴታ የረመዷን ቀዷችሁን ፁማችሁ ነው ሸዎልን መፆም ያለበችሁ።
||
t.me/Abuhiba
115 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, 02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:27:57 ከሸዋል ወር ስድስት ቀኖች
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

⑧) ሸዕባን
⑨) ረመዷን
     
10) ሸዎል
ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«ማንም ረመዷንን ፆሞ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው።»
عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏«‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ.»

ምንጭ:- ቲርሚዚ (8/78)
||
t.me/AbuHiba
253 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, edited  16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 09:07:33
አል-ሐምዱሊላህ
አሸዋ ሜዳ ሰግደን ተመልሰናል!
አሸዋ ሜዳ ሙስሊሞች ብቻ የሰፈሩበት ሰፈር መሆኑን አስመስክሯል፤ ህዝቡ ጎርፍ በሉት!
:
የአሸዋ ሜዳው ይለያል!
በተለይ ደግሞ ይቺ ማስታወቂያ ተመችታኛለች!

«ከዒድ ሶላት በኋላ አንድም ሰው ሸሪዓና ከሱና የሚፃረር ተክቢራ ከማለት ውጭ ማንም አካል ነሽዳ፣ ድቤ መደብደብ፣ ቢድዓ ተኮር ተግባርና ሌሎችንም ሲል የተገኘ ቀጥታ እርምጃ እንወስዳለን!»
ስቴድየምና ታች ሜዳ ቤቴል አለም ባንክ እዛው¡

አሸዋየ ሰፈራችን ሱና የማይሸፋፈንበት ተውሒድ ግልፅ ተደርጎ የሚነግርበት ሰፈር።
330 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, edited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 06:09:52 ሴቶች እና ዒድ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ሴቶችን በተመለከተ በዒድ ለት ይሁን በሌላ ጊዜ ከቤታቸው እንዴት መውጣት እንዳባቸው በሸሪዐ የታወቀ ነው፡፡
||
እናም ከመገላለጥ እና ሽታ ያላቸውን ነገሮች ተጠቅመው ከመውጣት ተቆጥበዉ ከቤታቸው ወደ መስጊድ ወይም ወደ ዒድ መስገጃ ስፍራ ሊሄዱ ይገባል፡፡
:
«ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለጋብቻ የቀረቡና የደረሱ እንዲሁም በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዒድ ሰላት መስገጃ ቦታ ስፍራ እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠይቀው ነበር:-
«አንዳችን ጅልባብ ባይኖራት ምን ታድርግ?» እርሳቸውም እንዲህ አሉ «እህቷ ጓደኛዋን ታውሳት።»
ሙተፈቅ
:
በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል:-
«ሴቶችን መስጊድ ከመሄድ አትከልክሏቸው ነገር ግን ከቤታቸው ሽታ ያለው ነገርን ተጠቅመው እንዳይወጡ፡፡»

አቡዳውድ ዘግበውታል
300 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, edited  03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 22:25:10 ከዒድ ጠዎት ጀምሮ መፈፀም ያለብን
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ከዒድ ጠዎት ጀምሮ መፈፀም ያለብን ነገሮች:-
①) መታጠብ እራስን ማሰማመር እና ከልብሶች መካከል የተሸለውን እና ቆንጆውን መልበስ፣
:
②) ወደ መስገጃው ከመውጣታችን በፊት ቴምር መብላት (አንድ፤ ሶስት፤ አምስት…) ማለትም
ኢ-ተጋማሽ ቁጥር ያላቸውን ተምሮች በልቶ መውጣት፣
:
③) ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዐት አንስቶ ሰላቱ እስኪጀመር ተክቢራ ማለት፣
:
④) ለኢድ ሰላት ከመውጣት በፊት ዘካተል-ፊጥርን ለተገቢው ወገን መስጠት፣
:
⑤) ሰላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በተቻለ አቅም ኹጥባን ማዳመጥ (ይሁን እንጅ ኹጥባን ማዳመጥ ግዴታ አይደለም)፣
:
⑥) ወደ ዒድ ሰላት ከሄዱበት መንገድ በሌላ መንገድ ቀይሮ መመለስ፣
:
⑦)የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መለዋወጥ፣ እንኳን አደረሳችሁ ስትባሉ «ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሃል አዕማል» ብሎ መመለስ የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት ከሰሃቦች መገኘቱን አረጋግጠዋል፡፡
*
ሚያዚያ 12, 2015 E.C
አቡ ሒባ
||
የቴሌግራም ቻናል:-
t.me/AbuHiba
449 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, edited  19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 22:18:51 በዒደል ፊጥር ቀን ጧት ላይ ወደ መስገጃው ሜዳ ስንወጣ ቴምርን በልቶ መውጣት ሱና ነው
381 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:00:27 ዒድ ሙባረክ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አሰላሙለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ
ኢድኩም-ሙባረክ እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ
:
«ተቀበለላሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሓል አዕማል»
عيد مبارك!
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
كل عام وأنتم بخير...
አቡ ሒባ
||
t.me/AbuHiba
457 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, edited  16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 18:21:48 ➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ክፍል:- 262 1) «ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ፆመኛን ከፀያፍ እና ከውድቅ ንግግር መፅጃ ለሚስኪኖች ደግሞ ምግብ ይሆን ዘንድ ሶደቀተል ፊጥርን ግዴታ አድርገዋል።» ምንጭ:- ሶሒሁል ጃሚዕ (1460) «ﻓﺮﺽَ ﺭﺳﻮﻝُ ﺍﻟﻠﻪِ ﺯﻛﺎﺓَ ﺍﻟﻔِﻄﺮِ ﻃُﻬﺮﺓً ﻟﻠﺼّﺎﺋِﻢِ ﻣﻦ ﺍﻟﻠَّﻐﻮِ ﻭ ﺍﻟﺮَّﻓَﺚِ ﻭﻃُﻌﻤَﺔً ﻟﻠﻤﺴﺎﻛﻴﻦِ .»…
508 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, edited  15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:34:24
መስጅደል-ሐረም 27ኛው ሌሊት

27ኛው ለሊት በመካ የሰጋጆች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺ በላይ መድረሱን አል-ሐረመይን በገጹ አስነበቧል።
ሱብሓነክ!
||
ያ ረ ብ እኛንም ወፍቀን
587 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 12:46:07 ይድረስ!
~
1- ይድረስ ሚስትህን ለፈታኸው፡
ልጆችህን ለዒድ አስበሃቸዋል? ወይስ እነሱንም ከናታቸው ጋር ፈተሃቸዋል?

2- ይድረስ የየቲሞች አጎት ለሆንከው፡
የሟች ወንድምህን ልጆች ትጠይቃለህ? ወይስ ከቀበርከው ወንድምህ ጋር ረስተሃቸዋል?

3- ይድረስ ባሏ የሞተባት እህት ያለችህ :
እህትህን ትኑር ትሙት ጠይቀሀል? በልታለች ወይስ ተርባለች? ወይስ እህትነቷ ቁጥር ብቻ ነው?

ይድረስ ለሁላችን፡

እጃችንን የሚጠብቁ፣ ከኛ የቀረበ ሰው የሌላቸው ቤተሰቦቻችን በምን ላይ ናቸው? በዒድ በምን መልኩ እንዲያስታውሱን እንፈልጋለን? ያቅማችንን ያክል ከልባቸው ውስጥ ደስታ ማስገባት ያሳስበናል? ወይስ ሀዘን ትካዜያቸው ምንም አይመስለንም?!
-
ተነካክቶ ከዐረብኛ የተመለሰ
=
https://t.me/IbnuMunewor
438 viewsYasin Muhammed - አቡ ሒባ, 09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ