Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤል ካሳሁን መኩሪያ ትምህርቶች እና መጣጥፎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnabel — የዲያቆን አቤል ካሳሁን መኩሪያ ትምህርቶች እና መጣጥፎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnabel — የዲያቆን አቤል ካሳሁን መኩሪያ ትምህርቶች እና መጣጥፎች
የሰርጥ አድራሻ: @dnabel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.17K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ልዩ ልዩ መጣጥፎች ፣የድምጽና የምስል ትምህርቶችን የሚጋሩበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው!!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 23:15:33 "በረከትን ሁሉ የተሸከምሽ አንቺን የማይወድ ማን ነው? አንድ ጊዜ ቀምቶ የወረሳቸውን ንብረቶች ሁሉ መልሰሽ ከወሰድሽበትና ባዶውን ካስቀረሽው ከሰይጣን በቀር አንቺን ማን ይጠላል? አንቺን ተስፋ አድርጎ ወደ ሲዖል የወረደ የለም። ያለ አንቺም ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። ያለ ንስሐ እግዚአብሔርን ማየት የሚችል ማን ነው? በአንቺስ ተስፋውን አድርጎ በሰይጣን እጅ የወደቀ ማን ነው? በአንቺ ሳይታጠብ ንጹሕ ሆኖ የተገኘ አለን? በአንቺ ውኃነት ተክሉን አጠጥቶ የደስታን ፍሬ ያልቀጠፈ ማን ነው? በንስሐ እንባ ፊቱን አጥቦ በልቡ እግዚአብሔርን ያላየስ ማን ነው? ለበደለኞች አማላጅ ትሆኝ ዘንድ የተሰጠሻቸው የይቅርታ እናቱ ንስሐ ሆይ፣ አንቺ ብጽዕት ነሽ፤ የመንግሥቱን ቁልፍ ሰጥቶሻልና አንቺ ለምነሽ እግዚአብሔር የሚዘጋው በር የለም"

አባ ዮሐንስ ሳባ (አረጋዊ) (Abba John Saba)

ትርጉም: ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
1.1K viewsedited  20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:45:37 በክንፎቻቸው ተሸፋፍነው በፊቱ የሚቆሙለት ቅዱሳን መላእክት፣ ፈጣሪያቸው "እኔ በምድር ወዳጅ አለኝ። እርሱም አብርሃም ነው" ብሎ በነገራቸው ጊዜ እጅግ በመደነቅ ወደ አብርሃም ሄደው "አብርሃም አርከ እግዚአብሔር"/"አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ"/ እያሉ ዘምረውለት ነበር። በእውነት እግዚአብሔር "ወዳጅ አለኝ" ስላላቸው እንዲህ የተደነቁ መላእክት፣ "እኔ በምድር እናት አለኝ" ሲላቸው ምን ያህል ተገርመው ይሆን? እመቤታችንንስ በምን ዓይነት ቃል አመስግነዋት ይሆን?

በዛሬው እለት የአምላክን እናት ልዩ በሆነ ምስጋና እና እልልታ ያሳረጓት መላእክት፣ በምድር ሳለች "እይዋት የአምላክን እናት በምድር ትመላለሳለች" እያሉ በስስት የሚያይዋትና መምጣቷን የሚጠባበቁ እመቤታቸው ነበረች። ለዚህም ነው አባቶቻችን በሌሊት ማኅሌት "ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፣ ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ" እያሉ ሲወርቡ ያደሩት።

እኛም ንግሥታችንን ወደ ልጇ እልፍኝ ለሸኘንበት፣ መላእክትም እርሷን በደስታ ለተቀበሉባት ለበዓለ ዕርገቷ እንኳን በሰላም አደረሰን!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 16፣ 2014 ዓ.ም.
ኢየሩሳሌም፣ እስራኤል

ቤተሰብ ይሁኑ

https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
2.8K views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 17:53:08 +++ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" +++

ጌታችን ከሐዋርያቱ መካከል "አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንም" ወደ ቅዱሱ የታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ።(ገላ 2፥9) ከተራራውም ጫፍ ሲደርሱ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የመምህራቸው ፊት እንደ ፀሐይ ሲያበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሲሆን ተመለከቱ። እነሆም ከቀደሙት ጻድቃን ታላላቆቹ ሙሴና ኤልያስ በታቦር ተገኝተው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።

እነዚህ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ምን ተነጋገሩ? መቼም በጊዜው ከጌታ ጋር ውለው ያድሩ እንደ ነበሩት ተማሪዎቹ ሐዋርያት "አትሙትብን" አይሉትም። በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሱባኤ የያዙለትና ደጅ የጠኑት የድኅነት ተስፋ እናዳይፈጸም "ይቅር አትሙት" እንዴት ይላሉ? ስለዚህ ከብሔረ ሕያዋን የመጣው ኤልያስና ከብሔረ ሙታን የመጣው ሙሴ በአንድ ላይ "በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ስለ መውጣቱ (ስለ መከራው፣ ሞቱ)" ያነጋግሩት ነበር።(ሉቃ 9፥31)

በታቦር ተራራ ላይ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መልእክተኞች ተገናኙ። በባሕር ላይ በእግሩ የተራመደው ጴጥሮስ፣ የኤርትራን ባሕር እጁን ዘርግቶ የከፈለው ሙሴን አየው።(ማቴ 14፥29፣ ዘጸአ 14፥21) የሰማርያ ሰዎች በተቃወሙ ጊዜ "እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው" ያሉ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ከሰማይ እሳት አዝንሞ ሃምሳ አንዱን ወታደሮች ያስበላ ኤልያስን ተመለከቱት።(ሉቃ 9፥54፣ 2ኛ ነገ 1፥10)

ሁለቱ ምስክሮች እንደ ተሰወሩም ወዲያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ዳሶች እንሥራ ብሎ ጌታውን ጠየቀ። ሐዋርያው በዚህ ተራራ ላይ መቅረት የፈለገው ያለ ምክንያት አይደለም። መድኃኒታችን አስቀድሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ዘንድ ብዙ መከራ ይቀበልና ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲነግራቸው ቅዱስ ጴጥሮስ "አይሁንብህ፤ አይድረስብህ" ሲል ሊከላከለው ሞክሮ ነበር። ለዚህም በጊዜ "ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" ተብሎ ተገስጾበታል።(ማር 9፥31-33) ይሁን እንጂ አሁንም ቅዱስ ጴጥሮስ ያለውን ሁሉ እድል ተጠቅሞ ጌታን ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄድና በካህናት አለቆች እጅ ተላልፎ ከመሰጠት ማስቀረት ስለሚፈልግ "ጌታ ሆይ፦ በዚህ(በታቦር ተራራ) መሆን ለእኛ መልካም ነው" ብሎ ተናገረ።

እርሱም ይህን ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። ከደመናው "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ መጣ። ሐዋርያቱ ይህን ድምጽ የሰሙት ሙሴ እና ኤልያስ ከክርስቶስ ተለይተው ከሄዱ፣ እነርሱም ወድቀው ከነበሩበት ከተነሡ በኋላ ነው። ይህም ከደመናው ውስጥ ሲወጣ ስለ ሰሙት ቃል "ለማን የተነገረ ይሆን?" ብለው እንዳይጠይቁና ምስክርነቱ ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ እንዲረዱ ነው። በዚሁም ላይ ደመናው ወርዶ የጋረደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሳይሆን ሐዋርያቱንም ጭምር ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ደመናው ጌታን ብቻ ጋርዶት ቢሆን ኖሮ፣ ሐዋርያቱ "እርሱን ስሙት" የሚለውን ቃል ራሱ ክርስቶስ ለራሱ የተናገረው ሊመስላቸው በቻለ ነበር።

ቅዱስ ጴጥሮስ "አትሙት" ያለው መምህሩን በፍጹም ልቡ ስለሚወደው መሆኑ አያጠራጥርም። ነገር ግን ጴጥሮስ ጌታን የቱንም ያህል ቢወደው፣ ፍቅሩ ግን ከወለደው ከባሕርይ አባቱ ከአብ አይደለም ሊበልጥ ሊነጻጸርም አይችልም። ታዲያ አብ በእርሱ ደስ የሚለው፣ የሚወደው፣ አንድያ ልጁ እንዲሞት ፈቃዱ ከሆነ፣ የአብን ያህል ሊወደው የማችለው አረጋዊው ጴጥሮስ ለምን "አትሙት" እያለ ይቃወማል?!

አብ ምትክ የሌለው ልጁ ወልድ ሰው ሆኖ በክፉዎች እጅ ሲንገላታ እና እስከ መስቀል ሞት ሲደርስ እያየ ዝም ያለው ስለማይወደው አይደለም። ዓለም ያለ ልጁ መከራና ሞት ስለማትድን ነው እንጂ። ከዚህ ምን እንማራለን? ዛሬም ወደ መከራ የምንገባ የጸጋ ልጆቹ የምንሆን እኛ ክርስቲያኖች "እግዚአብሔር እንዲህ ስሆን ዝም ያለኝ ስለማይወደኝ ነው" አንበል። ባገኘን ጥቂት የሥጋ መከራና ሕመም የሚበልጠውን የነፍስ ጤና የምንሸምት ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ይላል። ዝም የሚለው መከራችንን ስለማያይ ሳይሆን ከመከራው ጀርባ ያለው ዓላማ ታላቅና የተቀደሰ እንደ ሆነ ስለሚያውቅ ነው።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 13፣ 2014 ዓ.ም.
ደብረ ታቦር፣ እስራኤል

ቤተሰብ ይሁኑ

https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
2.8K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:17:05 +++ አምላካችን እንዲህም ነው +++

ቅዱስ ጴጥሮስ መምህሩና አምላኩ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ልብሱ ከፀሐይ ይልቅ ሲያበራ፣ ነቢያቱ በክብር ተገልጠው ሲመሰክሩለት ቢመለከት "ከዚህ አትውረድ" አለው። ለጴጥሮስ:- እርሱም ፈርቶ እየወደቀ፣ ክርስቶስም በልዕልና እያበራ ቢኖሩ ሁሉ ጊዜ ደብረ ታቦር ቢሆን ምኞቱ ነበር። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም። እርሱ ከፍጥረቱ የራቀ ሉዓላዊ፣ የሚያስፈራ፣ የማይመረመርና የማይነገር ብቻ አይደለም። ለፍጥረቱ ባለው ፍቅር ደግሞ ትሑትም ይሆናል። አሁን የሰውነቱ ብርሃን አስደንግጦት ከእግሩ ስር የወደቀው ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ከጥቂት ቀን በኋላ ግን መድኃኔዓለም እግሮቹን ሊያጥብ የማበሻ ጨርቅ እንደ ታጠቀ ከስሩ እንደሚያጎነብስ መቼ ዐወቀ?!

ጴጥሮስ ሆይ፣ ለምን ከታቦር አትውረድ ትለዋለህ? አንተስ በሰማያት በአባቱ እቅፍ የነበረውን አምላክ በታቦር ያየኸው ሥጋችንን ተዋሕዶ ወደ ምድር በመውረዱ አይደለምን? ለእኛ ሲል ከሰማያት የወረደውን ጌታ "በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" ብለህ በታቦር ልታስቀርብን ነውን? አንተ ቅን ሐዋርያ ሆይ፣ ታቦር ከአምላክህ ጋር የምትኖርበት የዕረፍት ቦታ እንዲሆንልህ ፈለግህ? ይህ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው ከፊትህ የቆመው የእግዚአብሔር በግ እኮ ያለ ቀራንዮም ማረፊያ የለው። ተወው ይውረድልን። ለእኛ አንተ በፊቱ ላይ ያየኸው ብርሃን ብቻ ሳይሆን ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ የሚወዛው የደም ወዝም ያስፈልገናል። ያለ እርሱ አንድንምና።

ጴጥሮስ ሆይ፣ መምህርህን "አትውረድ" ብለህ አትጠይቀው። ካለበት ልዕልና የሚያወርደው እኮ ፍቅር ነው። ለእርሱ "አትውረድ" ማለት "ፍጥረትህን አትውደድ" ከማለት አይተናነስም። አንተ የዋሕ ሐዋርያ "ብትወድስ" ብለህ ትጠይቀዋለህ? እርሱ በመልኩ ከፈጠረው ሰው አስበልጦ የሚወደው ምን ነገር አለ? ላያደርገው አትጠይቀው።

የክርስቲያኖች አምላክ እንደዚህ ነው። በአምላክነት ባሕርይው ልዑል ቢሆንም በመግቦቱ ግን ትሑት፣ በደስታ ጊዜ የማይለይ፣ በመከራ ጊዜም ሰው እስከ መሆን ደርሶ የሚዛመድ፣ የሰውን እግር የሚያጥብ፣ ስለ ሰው በመስቀል እርቃኑን የሚውል ነው። ይህ ለዚህ ዓለም ፈላስፎች ለጆሮ እንኳን የሚቀፍ ቢሆንባቸውም የእኛ የክርስቲያኖቹ አምላክ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ነው።

እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሰን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 12፣ 2014 ዓ.ም.
ጥብርያዶስ፣ እስራኤል

ቤተሰብ ይሁኑ

https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
3.0K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 20:02:17
4.1K views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 12:24:29 የቀረበላትን ምግብ ከመብላት ይልቅ ትጫወትበት የነበረች ልጁን አባት ‹‹የእኔ ልጅ ምግቡን ለምን አትበይም?›› ሲል ጠየቃት፡፡ ልጁም ‹‹አልራበኝም›› ብላ መለሰች፡፡ አባትየውም ‹‹ማደግ የምትፈልጊ ከሆነ እኮ የግድ መብላት አለብሽ›› አላት፡፡ ትንሽዋም ልጅ ‹‹አባቴ እኔ ማደግ አልፈልግም፡፡ ምክንያቱም ትልቅ ከሆንኩ ማርጀቴ ካረጀሁ ደግሞ መሞቴ አይቀርም፡፡ እኔ ደግሞ መሞት አልፈልግም!›› አለች፡፡(Anthony M.C እንደ ተረኩት)

የዚህችን ልጅ መልስ ስናነብ ፈገግ ብለን ይሆናል፡፡ ግን እውነት ዕድሜ መጨመራችን ወደ ሞት የሚያቀርበን ከሆነ ማደጋችን ምን ጥቅም አለው? ለሞት ከሆነ ለምን እናድጋለን?

እኛ ክርስቲያኖች ማደግ ወደ ሞት ለመቅረብ የሚደረግ እርምጃ እንደ ሆነ ብቻ አናስብም፡፡ ይልቅ ማደግ ከሞት በኋላ ለሚኖረን ሰማያዊ ሕይወት የምንዘጋጅበት ሂደት ነው፡፡ በዚህ ምድር አንድ ቀን ውለን ባደርን ቁጥር ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊው ሕይወት ለመሸጋገር የእለት ዕድሜ እየቀነስን እንሄዳለን፡፡ ዕድሜያችን ሲገፋ እርሱ ወደ አዘጋጀልን ስፍራ ሄደን ከክርስቶስ ጋር ለመኖር እየተቃረብን መሆኑን ስለምናውቅ ደስ ይለናል፡፡

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 04፣ 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

ቤተሰብ ይሁኑ

https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
4.5K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:20:32 'ወፌ ሰንብታ.....'

"ወፌ ሰንብታ ሰንብታ፥
መጣች ለፍልሰታ፥
ሀገርሽ የት ነው? ኤፍራታ፥
አሳድሪኝ ማታ፤

ይናፍቀኛል ሌሊት፥
የሰማይ እልፍኝ ሌሊት፥
ወፌ የ'ኔ እመቤት፤ (×2)

በክንፍሽ ጥላ ጋርደሽኝ፥
ከልጅሽ ስፍራ ወስደሽኝ፥
እንዳልቆምብሽ በግራ፥ እንዳያሰቃየኝ መከራ፥
ወፌ ነፍሴን አደራ፨ (×4)"
=====================

እያሉ እናቶቻችን በዝማሬ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ይቀበላሉ፨

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላም እና በጤና አደረሰን!



4.8K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 02:13:52

3.7K views23:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 22:47:04
5.2K views19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 17:37:56 +++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++

ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቅ ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።

ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ15 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።

አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።

የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!

(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም.
ዝዋይ (ብፁዕነታቸው ብዙ ሥራ በሠሩበት ክፍለ አገር ሆኜ)

ቤተሰብ ይሁኑ

https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
4.8K viewsedited  14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ