Get Mystery Box with random crypto!

ቅን እንሁን! **** ቅንነት ብዙ መጥፎ ነገሮችን ወደ በጎ የመቀየር አቅም አለው። ቅንነት ጦርነት | Christian Tadele Tsegaye

ቅን እንሁን!
****
ቅንነት ብዙ መጥፎ ነገሮችን ወደ በጎ የመቀየር አቅም አለው። ቅንነት ጦርነትን ወደ ሰላም፤ መውደቅን ወደ መነሳት፤ ማጣትን ወደ ማግኘት፤ ሽንፈትን ወደ ድል፣…የመቀየር ሙሉ አቅም አለው። ሌላው ቀርቶ ቅንነት ጠላትን ወደ ወዳጅ የመቀየር ልዩ አቅም አለው። ቅንነት የማንወዳቸው ቢሆን እንኳ በቂ ጊዜ ሰጥቶ ከማዳመጥ ይጀምራል።

ቅንነት ራሳችንን በሌሎች ቦታ በማስቀመጥ ስለነገሮች መረዳትን ይጠይቃል። ቅንነት ከግል እውነትና እምነት ይልቅ ለጋራ እምነትና የጋራ እውነት ይወግናል። ቅንነት ብዙ ዓይነትነትን ተፈጥሯዊ ፀጋ እንጂ ስጋትን ያዘለ የመለያየት እጣ እንዳልሆነ መተማመኛ ይሰጠናል። የሀሳብ መለያየት ወደ ጥላቻና አለመግባባት የሚያመራው ቅንነት ሲጓደል ብቻ ነው።

ቅንነት የአንድነት እርሾን ይጥላል። ቅንነት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል። ቅንነት የሻከረውን ያለሰልሳል፤ የደረቀውን ያለመልማል፤ የራቀውንም ያቀርባል። ከምንም በላይ ቅንነት የልብ ውስጣዊ ደስታንና ኅሊናዊ እርካታን ያጎናጽፋል። ሳንሰለች ቅን እንሁን!