Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-25 19:13:10 Emailing ኢሰመኮ አሸናፊ አካሉ.pdf
7.2K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 19:12:35 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ መዋቅር በፖለቲከኛ አሸናፊ አካሉ ላይ የፈፀመውን እገታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሰጠው ምላሽ!
6.7K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 18:56:26 በአጣዬ ለ10ኛ ጊዜ እየደረሰ ባለው ኹሉንአቀፍ ጥቃት እጅጉን አዝናለሁ።
*
እንደዓውደ ዓመት እየተደጋገመ የሚመጣ፣ መንስዔው ታውቆ ያደረ፣ የእልቂት ተዋናዮች በውል የሚታወቁ እና ግቡም ቢሆን ለሁሉም የታወቀ ነው። የጥቃቱ የትክተት ነጥብ አጣዬ ትሁን እንጂ ሰንሰለቱ ግን እጅግ ብዙ ነው። የእዝ ማዕከሉም ቢሆን ለግምት የቸገረ አይደለም።

እንዲያው በተለምዶ የኦነግ ሸኔ የሽብር ጥቃት ነው የሚባለውም በእኔ እምነት በቂ አይደለም። ይልቁንም መንግስታዊ መዋቅሩ አመራር እየሰጠበት የሚፈፀም የግዛት መስፋፋትን ግቡ ያደረገ በዘመቻ የሚፈፀም ጥቃት ነው የሚለው ገላጭ ነው። በመንግስታዊ መዋቅር በሚዘወረው ዘመቻ ሸኔን ጨምሮ የጋራ የፖለቲካ ግብ ያነገቡ የየራሳቸውን የተጠና ሚና የሚጫወቱ አካላት ሊኖሩ ቢችሉም ዋናዎቹ አዝማቾች ግን በመንግስታዊ መዋቅር የሚገኙ ናቸው።

ሕዝባችን እነዚህን ቀንደኛ አንቃሳቃሾች በመለየት ታግሎ ለፍርድ በማቅረብ መሰል ስውር እጆች ዳግመኛ እንዳነሱ የሚያደርግ ቅጣት ካላገኙ በስተቀር እልቂቱ የመቆም እድሉ የሰለለ ነው። በእሳት እየነደደ ላለ ወገን ስለችግር ምንጭ ማብራራት እፎይታን ባይሰጥም የችግሩን ምንጭ አውቆ ዘላቂ መፍትሔ ካልተበጀ በስተቀር ዛሬ 10 ያልነው የዘመቻ ጥቃት በየዓመቱ ወርኅ እየጠበቀ የመደገም እድሉ ሰፊ ይሆናል።

ይዘገያል እንጂ በሕዝባችን ላይ እልቂትን ያደረሱ ሁሉ ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም!
9.0K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 08:44:11
7.5K views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 08:44:03 በአሸናፊ አካሉ ላይ እገታ የፈፀመው የይልቃል ከፋለ መንግስት!
*
የምዕራብ ጎጃም ዞን የአብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ወንድማችን አሸናፊ አካሉ ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ ከታገተ እነሆ ከሳምንት በላይ ሆኖታል። እስከዛሬ ድረስም ፍርድ ቤት አልቀረበም። በይልቃል ከፋለ የሚመራው የክልሉ መንግስት አሸናፊን ዓባይ ማዶ በሚገኝ የልዩ ኃይል ካምፕ አግቶ ማስቀመጡን ያመነው እንኳን ከስንት ጉትጎታና ጩኸት በኋላ በቅርቡ ነው።

የክልሉ መንግስት የፀጥታ አመራሮች የመንግስት ደመወዝ የሚከፈላቸው አጋቾች ሆነው የሚቀጥሉት እከመቼ ድረስ ነው? ንጹኃን ዜጎችን እያፈኑ ያለፍረድ የሚያግቱበት የሥልጣን ምንጫቸውስ ምንድን ነው? ዛሬ ንጹኃን ዜጎችን አፍኖ ማገትን እንደልከኛ ተግባር የሚቆጥር የነውር ቡድን ነገ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን አፍኖ ላለማገቱስ ምን መተማመኛ ይኖራል? ስለአፈናው አቤቱታ የቀረበላቸው የምርጫ ቦርድና የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንስ ዝምታቸው እስከመቼ ነው?
7.3K views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 08:38:11 በተለይ ለአማራ ሕዝብ 3 የእሁድ ሰንበት መልእክቶች አሉኝ፦

1) አማራ ሆይ፥ በአስተሳሰብም በተግባርም አማራ ሁን።
2) ለኅልውናህ ከአንተ በላይ ስላንተ የሚቆረቆርልህም ሆነ የሚታገልልህ የለም። ይትባሃሉም «ባለቤት ያቀለለውን፥ ባለእዳ አይቀበለውም» ነው።
3) አማራ ሆይ፥ እባክህን የሚታገሉልህንና የምትታገላቸውን በውል ለይ። «በርባን ይፈታ፥ ክርስቶስ» ይሰቀል አካሄድህን በውል መርምረህ ማስተካከል ካልቻልህ ባርነትን ወደህ ፈቅደህ መምረጥህን እወቅ።

ስንደማመጥ፣ ስንተማመንና ስንከባበር ከባዱ ቀላል ይሆናል!
8.5K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 13:34:25
3.5K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 13:34:21 መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ?
*
ሕወኃት አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ነው። የሰላም ስምምነት ፊርማ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ ሕወኃት አሁንም ድረስ አሸባሪነቱ ያልተሰረዘለት ቡድን ነው። አስፈፃሚው አካል በማናለብኝነት የሚሰራውን ሕጎችን የመጣስ በጎ ያልሆነ ልምምድ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመቆጣጠር ሕዝባዊ ኃላፊነት አለበት። ለስነስርዓታዊ ጉዳዮችም ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በላይ ማን ሊጨነቅ ይችላል?

እነዚህ መንግስታዊ ባሕሪያት ሁሉ ግን በብልጽግና መሩ የኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ከመጤፍ የሚቆጠሩ ሆነዋል። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባዔ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ የመቀሌ ጉብኝት የመንግስትነት ወግ ብልሽት ዓይነተኛ ምሳሌ ሆኖ ለትውልድ አብነት ሊጠቀስ የሚችል ነው። መንግስታዊነት ሆይ ወዴት አለሽ? ከዚህ በኋላስ በምክርቤት ጉባዔዎች የስነስርዓት ጥያቄዎችን የማስከበር ሞራላዊ ቅቡልነት ይኖር ይሆን?

(ይኼ የስነስርዓት ጥያቄዬ የሰላም ስምምነቱን ከመቀበል እና አለመቀበል ጋር ግንኙነት የለውም።)
3.6K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 21:22:36 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ «የአማራ ሸኔ» ሲሉ ያሰሙት ንግግር የመብት ጥያቄዎችን በሚያቀርቡና የመንግስትን አግላይና ወገንተኛ አሰራር በሚተቹ የነቁ አማሮች ላይ በቀጣይ መንግስታቸው ሊወስድ የወሰነውን የአፈና ዘመቻ ማስጀመሪያ ፊሽካ አድርጌ እመለከተዋለሁ። ከሰሞኑ በአማራ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ አፈናዎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥላቻ ንግግር ቀዳሚ ንግርቶች ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ ይሆናሉ።
2.6K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 08:32:37
4.2K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ