Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ «የአማራ ሸኔ» ሲሉ ያሰሙት ንግግር የመብት ጥያቄዎችን በሚያቀርቡና የመንግ | Christian Tadele Tsegaye

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ «የአማራ ሸኔ» ሲሉ ያሰሙት ንግግር የመብት ጥያቄዎችን በሚያቀርቡና የመንግስትን አግላይና ወገንተኛ አሰራር በሚተቹ የነቁ አማሮች ላይ በቀጣይ መንግስታቸው ሊወስድ የወሰነውን የአፈና ዘመቻ ማስጀመሪያ ፊሽካ አድርጌ እመለከተዋለሁ። ከሰሞኑ በአማራ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ አፈናዎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥላቻ ንግግር ቀዳሚ ንግርቶች ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ ይሆናሉ።