Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-21 05:31:23 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን መግለጫ አነበብኩት። መግለጫው በያዛቸው አንኳር ጭብጦች ላይ ላሁኑ ምንም ማለትን አልፈልግም። ለክልሉ መንግስት አመራሮች ግን አንድ መልእክት አለኝ፦ «ኢመደበኛ…ቅብጥርሴ» በሚል ጅምላ ውንጀላና ፍረጃ በግፍ ያሰራችኋቸውን ንጹኃን ሁሉ ከእስር ፍቱ! አልያ ግን ንጹኃንን ከፍርድ ውጭ የሚገድለውና በግፍ አስሮ የሚያሰቃየው የይልቃል ከፋለ መንግስት በመግለጫው «የታሪክ ቆሞቀርና ቁማርተኛ» ብሎ ከወረፋቸው የወንበር ወደረኞቹ የሚለየው አፉን በአማርኛ በመፍታቱ ብቻ ይሆናል።

ከግፍ እንጂ ከግፈኞች አፍ መፍቻ ቋንቋ ጠብ የለንም!
2.9K views02:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:36:06 እግዚአብሔር ግን እግዚአብሔር ነው!
****
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያነጣጠረው የጥፋት ድግስ በአባቶች አርቆ አስተዋይነትና የአመራር ጥበብ፣ በምእመናን እስከመስዋእትነት የዘለቀ ታዛዥነትና ጽናት እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታይ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ኃቅን መሰረት ያደረገ ፍትኃዊ ውግንናና አብሮነት ለጊዜውም ቢሆን ከሽፏል። ቅዱስ ሲኖዶሱና የቤተክርስቲያኗ መዋቅሮች ሁሉ አጋጣሚውን እንደበረከተ መርገም በመውሰድ ውስጣዊ ችግሮችን ዘላቂነት ባለው ሁኔታ የቤተክርስቲያኒቷን ቀኖና አስተምኅሮ በጠበቀ መልኩ እልባት በመስጠት ለየትኛውም ፈትፋች ስውር እጅ ፈጽሞ የማይመች ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ አመራር፣ አሰራርና አደረጃጀት እንደሚፈጥሩ ተስፋ አደርጋለሁ።

በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ የተፈጸመውን ገሀዳዊ ጥቃት ተከትሎ ቅዱሳን አባቶቻችን ጉዳዩን የያዙበት ጥበብ፣ የተግባቦት ክሂል፣ ከምእመናት ጋር የነበረ መስተጋብር፣ ግብ ተኮር ቁርጠኛ አቋምና በሁኔታዎች የማይዋዥቅ ተቋማዊ ዲስፕሊን ለሁላችንም በተለይ ለፖለቲከኞች በጣም በተለይ ደግሞ አገርና ሕዝብ ለሚመሩ በሁሉም ደረጃ ላሉ መኳንንት የአደባባይ አስኳላ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። መንግስት ከሁነቱም፥ ከስህተቱም በቂ ትምህርት ስለመውሰዱ ለተፈፀመው ጥፋት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ምእመናንን በአጠቃላይ፤ የአካልና ሕይወት ጉዳት የደረሰባቸውን በተለይ ይቅርታ በመጠየቅ ተገቢውን ካሳ በመክፈል እንደሚያረጋግጥም ተስፋ አደርጋለሁ።

ሰማእትነት የተቀበሉትን ወገኖቻችን በሙሉ ነፍሳቸውን ከፃድቃን ሰማእታት ጎን ያስቀምጥልን፤ የቆሰሉትን የውሻ ቁስል ያድርግላቸው፤ ያዘኑትን መንፈስ ቅዱስ ያጽናናቸው!
2.1K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 21:32:54 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአሻም ቲቪ ጋር የነበረን ቆይታ።




1.4K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 16:38:13 መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል!
****
«በመንግሥት የጸጥታ አባሎች ተመጣጣኝ ባልሆነ ኃይል አጠቃቀም በጥይት እና በድብደባ የተፈጸሙ ግድያዎች፣ ከሕግ ውጭ የተፈጸሙ እስሮችና የእንቅስቃሴ ገደቦች፣ እንዲሁም ሲኖዶሱ ያቀረበውን የጥቁር መልበስ ጥሪ የተቀበሉ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ እስሮች፣ ከአገልግሎት እና ከሥራ ቦታ ማግለልና ማንገላታት ፍጹም ተገቢ ያልሆኑ እና የዜጎችን በሕይወት የመኖር፣ በነጻነት ኃይማኖታቸውን እና ሐሳባቸውን የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን የሚፃረሩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ናቸው።»

(ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ የተወሰደ።)
2.7K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 09:08:52 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከ፬ ኪሎ ሚዲያ ጋር የነበረን ቆይታ።



3.4K views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 16:58:50
2.7K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 17:51:41 በተለይ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ወንድማዊ መልእክት አለኝ፦ የቅዱስ ሲኖዶስን አቅጣጫ ብቻ በመከተል የአባቶችን ትእዛዝ ፈጽሙ። የተለያዩ እምነቶች ተከታይ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያንም በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን መንግስት ደገፍ ውንብድና በማውገዝ ላሳያችሁት አብሮነት ላቅ ያለ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁ።

ለሁላችንም መከራውን ከአቤሜሌካዊ እንቅልፍ የመንቃት ያድርግልን!
3.0K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 16:05:02 Channel photo updated
13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 19:43:49 የይልቃል ከፋለ መንግስት የአብን የምዕራብ ጎጃም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን አሸናፊ አካሉ አስገድዶ ከሰወረው ከአስራ ምናምን ቀናት በኋላ ነገ በባሕር ዳር ከፍተኛ ፍርድቤት እንደሚያቀርበው ተሰምቷል። በዳኝነት ነፃነት ላይ ያለን የማይዛነፍ አክብሮት እንደተጠበቀ ሆኖ ችሎቱ በትግል ወንድማችን ላይ የተፈፀመበትን ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የይልቃል ከፋለን መንግስት የፀጥታ መዋቅር የውንብድና ድርጊት አጽንዖት ሰጥቶ ተገቢው ማብራሪያ እንዲሰጥበት ማድረግ ይኖርበታል። የአብን አባላትና ደጋፊዎች ለትግል ወንድማችን ያላችሁን አጋርነት ታሳዩ ዘንድም ጥሪ እናቀርባለን።

(ለአባላቱና ደጋፊዎቹ ደኅንነት ግድ የሚለውን አብን በፍፁም መታደስ የሕዝብ፥ ለሕዝቡ፥ በሕዝቡ ሆኖ እንዲቀጥል በላቀ የኃላፊነት መንፈስ በአዲስ መነቃቃት እንድንቆምም ለንቅናቄው አባላትና ደጋፊዎች መልእክት እናስተላልፋለን።)

አብን፥ የአዲሱ ትውልድ የዴሞክራሲ አምበል!
3.1K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 19:43:46
2.9K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ