Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔር ግን እግዚአብሔር ነው! **** በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያነ | Christian Tadele Tsegaye

እግዚአብሔር ግን እግዚአብሔር ነው!
****
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያነጣጠረው የጥፋት ድግስ በአባቶች አርቆ አስተዋይነትና የአመራር ጥበብ፣ በምእመናን እስከመስዋእትነት የዘለቀ ታዛዥነትና ጽናት እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታይ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ኃቅን መሰረት ያደረገ ፍትኃዊ ውግንናና አብሮነት ለጊዜውም ቢሆን ከሽፏል። ቅዱስ ሲኖዶሱና የቤተክርስቲያኗ መዋቅሮች ሁሉ አጋጣሚውን እንደበረከተ መርገም በመውሰድ ውስጣዊ ችግሮችን ዘላቂነት ባለው ሁኔታ የቤተክርስቲያኒቷን ቀኖና አስተምኅሮ በጠበቀ መልኩ እልባት በመስጠት ለየትኛውም ፈትፋች ስውር እጅ ፈጽሞ የማይመች ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ አመራር፣ አሰራርና አደረጃጀት እንደሚፈጥሩ ተስፋ አደርጋለሁ።

በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ የተፈጸመውን ገሀዳዊ ጥቃት ተከትሎ ቅዱሳን አባቶቻችን ጉዳዩን የያዙበት ጥበብ፣ የተግባቦት ክሂል፣ ከምእመናት ጋር የነበረ መስተጋብር፣ ግብ ተኮር ቁርጠኛ አቋምና በሁኔታዎች የማይዋዥቅ ተቋማዊ ዲስፕሊን ለሁላችንም በተለይ ለፖለቲከኞች በጣም በተለይ ደግሞ አገርና ሕዝብ ለሚመሩ በሁሉም ደረጃ ላሉ መኳንንት የአደባባይ አስኳላ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። መንግስት ከሁነቱም፥ ከስህተቱም በቂ ትምህርት ስለመውሰዱ ለተፈፀመው ጥፋት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ምእመናንን በአጠቃላይ፤ የአካልና ሕይወት ጉዳት የደረሰባቸውን በተለይ ይቅርታ በመጠየቅ ተገቢውን ካሳ በመክፈል እንደሚያረጋግጥም ተስፋ አደርጋለሁ።

ሰማእትነት የተቀበሉትን ወገኖቻችን በሙሉ ነፍሳቸውን ከፃድቃን ሰማእታት ጎን ያስቀምጥልን፤ የቆሰሉትን የውሻ ቁስል ያድርግላቸው፤ ያዘኑትን መንፈስ ቅዱስ ያጽናናቸው!