Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን መግለጫ አነበብኩት። መግለጫው በያዛቸው አንኳር ጭብጦች ላይ ላሁ | Christian Tadele Tsegaye

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን መግለጫ አነበብኩት። መግለጫው በያዛቸው አንኳር ጭብጦች ላይ ላሁኑ ምንም ማለትን አልፈልግም። ለክልሉ መንግስት አመራሮች ግን አንድ መልእክት አለኝ፦ «ኢመደበኛ…ቅብጥርሴ» በሚል ጅምላ ውንጀላና ፍረጃ በግፍ ያሰራችኋቸውን ንጹኃን ሁሉ ከእስር ፍቱ! አልያ ግን ንጹኃንን ከፍርድ ውጭ የሚገድለውና በግፍ አስሮ የሚያሰቃየው የይልቃል ከፋለ መንግስት በመግለጫው «የታሪክ ቆሞቀርና ቁማርተኛ» ብሎ ከወረፋቸው የወንበር ወደረኞቹ የሚለየው አፉን በአማርኛ በመፍታቱ ብቻ ይሆናል።

ከግፍ እንጂ ከግፈኞች አፍ መፍቻ ቋንቋ ጠብ የለንም!