Get Mystery Box with random crypto!

ምሳሩ ሌላ ቢሆንም እጀታው ግን ከኛው ነበር! * ዘመነ ካሴ ከሕዝብ ክብር እና ማኅበራዊ ስነልቦና | Christian Tadele Tsegaye

ምሳሩ ሌላ ቢሆንም እጀታው ግን ከኛው ነበር!
*
ዘመነ ካሴ ከሕዝብ ክብር እና ማኅበራዊ ስነልቦና በላይ የግል ክብርና ስም በበለጠባቸው የአማራ ክልል አመራሮቸ ድክመት በተለይም በርእሰ መስተዳደር ይልቃለ ከፋለ (ዶ/ር) ስንፍና በግፍ የታሰረ ወንድማችን ነው።

ጉዳዩን በንግግር ለመፍታት የተደረጉ ውይይቶችንና የተደረሰባቸው ስምምነቶችን ሳይቀር አብረውት ለሚሰሩ አመራሮችም ሆነ ትእዛዝ ለሚያወርዱለት የፌዴራል ባለስልጣናት በወቅቱ ባለማድረሱ ነው የ«ሕግ ማስከበር ዘመቻ» የሚባለው ማሳደድ የተጀመረው። በዚህ የተነሳ ርእሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በተለይም በመረጠው አካባቢ ሕዝብ ልጆች ላይ ከሕግ ውጭ ለተፈፀሙ ግድያዎቸና ጅምላ እስሮች ኃላፊነቱን ይወስዳል።

የወንዜ ጅብ ይብላኝ ፖለቲካ ድሮ ቀረ፤ የየትም ሰፈር ጅብ እንዲበላኝ አልፈቅድም የሚል ትውልድ ላይ ነን!