Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-30 18:19:10
ከአንከር ሚዲያ ጋር ስለመጋቢት 19ኙ የፓርላማ ውሎ የነበረን ቆይታ።
2.7K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 09:48:03 ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው 11ኛ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች፤
**
አመሰግናለሁ የተከበሩ አፈጉባዔ፤

አመሰግናለሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፤

ጥያቄዬን ከማቅረቤ በፊት ስለጥያቄዬ ትንሽ ማለት እፈልጋለሁ። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዚህ ምክር ቤት እና በተለያዩ መድረኮች ስለእርስዎና ስለሚመሩት የአስፈፃሚ መንግስት ተጠየቅ ሲቀርብብዎ ለተጠየቁ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጠያቂዎችን የሚያጥላላ አስተያየት ሲያራምዱ፤ አለፍ ሲልም ተጠየቅ የቀረበብዎት የወጡበት ብሔርን በመጥላት እንደሆነ አድርገው ምላሽ መስጠትዎ የቅርብ ትዝታ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ቀጥዬ የማቀርብልዎ ጥያቄ ራስዎንና መንግስትዎን የሚመለከት እንጂ ሌላ ማንንም የማይመለከት መሆኑን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። እኔም ጥያቄውን የማቀርብልዎት በብሔር አይደለም። ምላሽ ሲሰጡም የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ የተሼረበ ሴራ ነው የሚል እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ጥያቄዬ የሚከተለው ነው።

የዜጎችን ደኅንነት እና የአገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛ የመንግስት ኃላፊነት ሆኖ ሳለ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፤ ቤታቸው ይፈርሳል፤ ንብረታቸውም ይወድማል። የአገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት አገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርካታ ኪሎሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈጽመዋል። አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ደኅንነትና የአገር ሉዓላዊነት ዋነኛ የስጋት ምንጭ ሆኖ የምናየው ራሱ መንግስትን ነው። እርስዎ በአፍዎ «ኢትዮጵያ አትፈርስም» ቢሉንም በተግባር ግን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት በመንግስትዎ እየተናዱ ነው። የበርካታ አገራት መሪዎቸ መሰል ኃላፊነትን በወጉ ያለመወጣት ጉድለት ሲያሳዩ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው ሥልጣናቸውን ሲለቁ ይታያል። በአገራችንም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመሳሳይ ሕዝባዊ ተጠየቅ ሲቀርብባቸው ሥልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል።

እርስዎስ ሥልጣንዎን በመልቀቅ የመፍትሔው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ? በሰብአዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም የማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳትና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ነዎት?


አመሰግናለሁ!
2.9K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 12:46:33 ልጅ በአባቱ ለመጨከን ተፈጥሮው አልፈቀደለትም!
*
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ ባካሄደው አንደኛ ልዩ ስብሰባ ሕወኃት በ61 ተቃውሞ፤በ5 ተዓቅቦ፤ በአብላጫ ድምጽ የአሸባሪነት ስያሜው ተነስቶለታል።

① በመከላከያ ሰራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ወንጀል የፈፀመና የአገር ክህደት ወንጀል የፈፀመ፤
② በአማራና አፋር ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል እንዲሁም የጦር ወንጀል የፈፀመ፤
③ አሁንም የጦር ነጋሪት እየጎሰመ ያለ፤
④ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ሆኖ ባወጣቸው ሪፖርቶች መሰረት ይቅርታና ምሕረት የማያሰጡ ዓለምአቀፍ ወንጀሎችን መፈፀሙ የተረጋገጠበት፤

ድርጅት ሆኖ ሳለ፤ «ከጋራ የጦርና በሰብአዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት በጋራ ስምምነት እናምልጥ» በሚል የጋራ ስምምነት በሚመስል መልኩ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ቀርቦ ውይይት ሳይደረግና ስምምነቶቹ ስለመፈፀማቸውም ማረጋገጫ ሳይገኝበት፤ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑን ታሪክ መዝግቦታል። ውሳኔውን ተከትሎ በድብብቆሽ ሲከወኑ የነበሩ «ጉንጭ መሳሳሞች» ወደ አደባባይ መተቃቀፎች እንደሚያድጉ ይገመታል።

ልጅ በአባቱ እንደማይጨክን ተናግረን ነበር!
386 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 16:15:23 Channel photo updated
13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:09:19
2.7K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:09:08 የ127ኛ ዓመት የዓድዋ በዓል አከባበርን አስመልክቶ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣
****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የ127ኛ ዓመት የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ዝግጅትን በአንክሮ ሲከታተል ቆይቷል። በዚህም በመንግስት ደረጃ መዋቅራዊና ሥርአታዊ በሆነ መልኩ ታሪክ ለመበረዝ የተሄደበትን ርቀት ተመልከተናል። በዓሉ ለዘመናት ሲከበርበት ከነበረው ምኒልክ አደባባይ ከመቀየር አንስቶ የዓድዋ ድል ዋና አምድ የሆኑ መሪዎችን በተለይም የመሪውን አፄ ሚኒሊክን ሚና ለማሳነስ እና ለማኮሰስ የተደረገው የተቀናጀ መንግስታዊ የበዓል አዘገጃጀት ሂደት እጅግ አሳዛኝ እና በዚህ ዘመን ይደረጋል ተብሎ የማይታሰብ አሳፋሪ ድርጊት ሆኖ አግኝተነዋል።

በሌላ በኩል በዕለቱ በመንግስት ደረጃ ቦታ በመቀየር በዓሉን ለማክበር መሞከሩ ሳያንስ በዓሉን በታሪክ ሲከበር በነበረበት ሚኒሊክ አደባባይ ለማክበር በተሰበሰበው ሕዝብ ላይ የተፈፀመው ነውረኛ ድርጊት ከባንዳነት የማይተናነስ አፀያፊ የታሪክ ኩነት ሆኖ ተመዝግቧል።

ከኢትዮጵያ አልፎ የጥቁር ሕዝብ ሁሉ የኩራት ምንጭ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል እንደወትሮው በምንሊክ አደባባይ ሕዝብ ተስብስቦ እንዳያከብረው በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች አላስፈላጊ ኃይል የተቀላቀላበት እርምጃ የተነሳ በመስተጓጎሉ ንቅናቄያችን ድርጊቱን በፅኑ ያወግዛል!

ግብር ከፋይ ዜጎች የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በፈለጉበት ስፍራ እንዳያከብሩ የሚከለክላቸው ሕግ የለም። የመንግስት ድርሻ ዜጎች በነፃነት ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና ሰላምና ደህንነትን ማስከበር ነው!

መንግሥት በእጁ ያለው ሉዓላዊ ስልጣን ከዜጎች በውክልና ያገኘውና ግብር የሚሰብስብበት በመሆኑ የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት የመጠበቅና ማስጠበቅ ግዴታ ያለበት ከመሆኑም በተጨማሪ ከሕግ አግባብ ውጭ የትኛውንም አይነት አመለካከት እና እምነቱን አስገድዶ በዜጎች ላይ መጫን እንደማይችል ሊገነዘበው ይገባል!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የዛሬውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከባበር በተመለከተ ከሕግ እና ሥርአት ውጭ ሕዝብ በፈለገው ስፍራ እንደፈቀደው እንዳያከብር መንግሥት የፈጠረውን እክል በፅኑ ያወግዛል። ከኢትዮጵያውያን አልፎ ለጥቁር ሕዝብ ሁሉ መመኪያ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዚህ ደረጃ የውርደት እና መከፋት ስሜት በሚፈጥር ድባብ እንዲያልፍ መደረጉ እጅግ አሳዝኖናል። መንግሥት ሆነ ብሎ ከሳምንት በፊት የጀመረው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን የሚያደበዝዝ ሸፍጥ የወለደው የታሪክ ብረዛ ስራና ከፋፋይ የዘረኝነት ፖለቲካ የተነሳ በድምቀት፣ በኩራት እና አልበገር-ባይ ኢትዮጵያዊ ወኔ መከበር የነበረበት የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በዚህ ሁኔታ በጭስ ቦንብ እና ዱላ የጸጥታ ኃይሎች ያለርህራሄ ዜጎችን ወደሚያጠቁበት ትራጄዲ መቀየሩ ጥልቅ መከፋትን ይፈጥራል። የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በየአደባባዩ የተገኘው ዜጋ ላይ ፍፁም አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ ከመውሰድ አልፈው በቤተክርስቲያን ውስጥ የጭስ ቦንብ በመወርወር በቅዳሴ ሥነ ሥርአት ላይ በነበሩ ምእመናን እና ካህናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል::የዳግማዊ ምኒሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህር የነበረው የአብን አባል ሚሊዮን ወዳጀ ከመንግስት ጸጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት ተገድሏል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህን ሕገወጥ ድርጊት በፅኑ ያወግዛል!

ስለሆነም:-

፩. መንግስት የፈፀመውን ሕገወጥ ድርጊት በማመን ሕዝብን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ና እንዲህ አይነት ሕገወጥ ድርጊት በድጋሜ እንደማይከሰት ማረጋገጫ እንዲሰጥ እናሳስባለን::

፪. ይኸ ሕገወጥ ድርጊት እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጡ ባለስልጣናት እና የተሳተፉ የጸጥታ ኃይሎች ተለይተው ለሕግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን!

በዚህ አጋጣሚ መንግስት በተቀናጀ ሁኔታ ታሪክን በመበረዝ እና በማፈራረስ ከታሪኳ የተፋታች አገርን ለመገንባት የሚያደርገውን ያልተቀደሰ ጉዞ እንዲያቆም እናሳስባለን። በዛሬው እለት በነፃነት በዓል ላይ በመገኘቱ ምክንያት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ ውድ ሕይወቱን በግፍ ለተነጠቀው ወንድማችን ጥልቅ ሃዘናችንን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም
2.7K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 10:21:55
1.8K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 10:21:50 የአድዋ ድል የዓለምን ታሪክ ስርነቀል በሆነ መንገድ የቀየረ አባቶቻችን ያስመዘገቡት ገድል ነው። ድሉ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የፀረ ቅኝ ግዛት ተጋድሎ ላደረጉ መላው የሰው ልጆች ሁሉ ነው። ድሉ የሰብአዊ እኩልነትን በደም ማኅተም ያረጋገጠ በዚህ መንፈስ ውስጥ ላሉ የዓለም ሰዎቸ ሁሉ ድላችን ብለው ክብርና ድምቀት የሚሰጡት ነው። በዚህም መላው ኢትዮጵያውያን ስለአድዋ ድል ቀደምቶቻችንን በትውልድ ሁሉ ልንዘክራቸውና ልናመሰግናቸው ይገባል።

በመሪዎቻችን ስብእና ዙሪያ ክርክር ሊኖረን ይችል ይሆናል። አድዋን አንስተን ግን ዳግማዊ አጤ ምኒሊክን አለማውሳት አይቻለንም። አጤውን መጥላት ይቻል ይሆናል፤ ያለ ምኒሊክ ግን አድዋ የሚባል ድል የለም። የንጉሰ ነገስቱን ምስል ከአድዋ ድል በዓል አከባበር ምስሎች ዝርዝር ፍቆ፤ በቦታው ያልነበሩ አሁን በሥልጣን ላይ ያሉ ግለሰቦችን ምስል መተካት፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ራት በሰበሰባቸው ሐዋሪያት ምስል ውስጥ የራስን ምስል በጌታችን ኢየሱስ ቦታ በአርትዖት የመተካት ያህል ነውር ነው። ወይንም ትንሳኤን ለማክበር በተሰቀለው ኢየሱስ ምስል ፋንታ የየራሳችንን ፎቶ የመደረት ያህል ኑፋቄ ነው።

በዚህ ረገድ የማዝነውም የማፍረውም ይህን በሚያደርጉ ሰዎች አይደለም፤ ይልቁንም በአጤ ምኒሊክ ፋንታ ምስላቸው የአድዋን ድል እንዳስገኙ ተቆጥሮ ሲታተም በዝምታ የተባበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ክፉኛ አዝኜባቸዋለሁ። እንዴት በሳቸው ደረጃ ያለ ሰው መሰለ ነውሮችነ በዝምታ ይተባበራል? ከበዓሉ አከባበር ጋር ተያይዞ በፀጥታ አካላት በኩል በዜጎች ላይ የሚፈፀመውን አፈና፣ ውርክቢያና እንግልትስ ለምን ማስቆም አቃተቸው? የአድዋን ድል በእስር፣ ድብድብና እንግልት ማክበርስ በዓሉን የማክበር ትሩፋቱን አያሳጣውም ወይ? በዚህ መልኩ የሚከበር የድል ቀንስ ከባርነት በምን ይለያል?

ልቦና ይስጠን፤ ልቡና ይስጣችሁ!
1.8K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 06:36:10
1.8K views03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 06:36:05 ምሳሩ ሌላ ቢሆንም እጀታው ግን ከኛው ነበር!
*
ዘመነ ካሴ ከሕዝብ ክብር እና ማኅበራዊ ስነልቦና በላይ የግል ክብርና ስም በበለጠባቸው የአማራ ክልል አመራሮቸ ድክመት በተለይም በርእሰ መስተዳደር ይልቃለ ከፋለ (ዶ/ር) ስንፍና በግፍ የታሰረ ወንድማችን ነው።

ጉዳዩን በንግግር ለመፍታት የተደረጉ ውይይቶችንና የተደረሰባቸው ስምምነቶችን ሳይቀር አብረውት ለሚሰሩ አመራሮችም ሆነ ትእዛዝ ለሚያወርዱለት የፌዴራል ባለስልጣናት በወቅቱ ባለማድረሱ ነው የ«ሕግ ማስከበር ዘመቻ» የሚባለው ማሳደድ የተጀመረው። በዚህ የተነሳ ርእሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በተለይም በመረጠው አካባቢ ሕዝብ ልጆች ላይ ከሕግ ውጭ ለተፈፀሙ ግድያዎቸና ጅምላ እስሮች ኃላፊነቱን ይወስዳል።

የወንዜ ጅብ ይብላኝ ፖለቲካ ድሮ ቀረ፤ የየትም ሰፈር ጅብ እንዲበላኝ አልፈቅድም የሚል ትውልድ ላይ ነን!
1.8K views03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ