Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-10-23 05:55:56 የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም የሰሜኑ ችግር ከሁለት ፓርቲዎች (ከብልጽግናና ከሕወኃት) በላይ ነው። በዚህ መነሻነት በአገር አንድነትና የሕዝብ ደኅንነት ላይ የተጋረጠው ተጨባጭ አደጋ ዘለቄታዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ከተፈለገ፥ ሁሉንአቀፍ ውይይቶችና ድርድሮች አስፈላጊ ናቸው።

Ethiopia's current situation, especially the conflict in the North, is beyond both Prosperity and TPLF; the two hostile parties. Hence, anyone who dares for lasting solution to the conflict that risks territorial integrity of Ethiopia and safety of its people shall consider all inclusive peace discussions, dialogues and negotiations.
8.9K views02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 23:32:42 https://friendtok.com/MarheirGebrye
8.8K views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 23:30:54 በዚህ እንወዳጅ።
8.4K views20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 06:46:16 ታናናሽ ወንድሞቼና እህቶቼ፥ ለአገራችሁና ለሕዝባችሁ መልካም ነገርን የማድረግ በጎ ሕልም ካላችሁ፤ ነፍስያችሁ ፍትኅን፣ ነፃነትንና እኩልነትን አብዝታ የምትጠማ እና ይህን መጠማታችሁን በትግል ማርካት አብዝታችሁ የምትሹ ከሆነ፥ እንግዲያውስ ወንድማችሁ ልምከራችሁ፤ ከጭቆና በፊት…ከጨቋኝ ኃይሎችም በፊት…በቅድሚያ ሆዳችሁን አሸንፉት። ሆድ መጥፎ ነው።

ታላቅ ያልናቸው በሆድ ፈተና ወድቀው አይተናል። የትግል ቃልኪዳናቸውን በሆዳቸው ቀይረውት፤ የትግል ጓዳቸውንም በከርሳቸው ተክተውት አይተናል። ወደው አይደለም፤ ሆዳቸው አሸንፏቸው… እንታገለዋለን ለሚሉት ወዶ ገብና ተመጽዋች ስላደረጋቸው ነው። እናም ታናናሾቼ…ከሁሉም በፊት ከሆዳችሁ ጋር ግጠሙ። ድሎትን ተጠየፉት። ብልጭልጩን አሸንፉት። ሆዳችሁን ለምንም ነገር እምቢ በሉት። ሰናይ ሰንበት!

ለሰው ልጅ ትልቁ ጠላቱ ሆዱ ነው!
11.9K views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 19:03:09



ከፋና ቲቪ ጋር ስለምክርቤትና ምክርቤታዊ አሰራሮች የነበረን ቆይታ።
2.6K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 06:26:34
ድሩፃ!

ደመራው ሲቃጠል፤
ጠላትን እንደጠል፤
ከፊታችን ያርግፍ፣
ደሞ እንደደቦቱ፤
ተቃጥሎ በእሳቱ፤
መከራችን ይለፍ።

እንጎሮጎባሽ ትግራይ!
እንጎሮጎባሽ አማራ!
ድሩፃ ድሩፃ ኢትዮጵያ!

የመስቀሉ ጌታ፤
አንድም ሳይቀንሰን፣
በፍቅር በጤና፤
ዓመቱን ያድርሰን!
2.0K views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 09:00:03
እንጎሮጎባሽ ኢትዮጵያ!

ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለደመራ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይባርክ!
3.0K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 08:23:46 ውሎ አድሮም ቢሆን በአማራ ብሔርተኝነት ትግል ሰልፍ ውስጥ ባሉ ተዋናዮች ዘንድ ያለው ልዩነት የመስመር ልዩነት ሆኖ እንዲህ ፍጥጥ ብሎ መውጣቱን ወድጄዋለሁ። ሰው በሚያምንበት መስመር መታገሉን ትግላችን የሚያከብረውና እውቅና የሚሰጠውም ስለሆነ ከዚህ አንፃር ያሉ የአሰላለፍ ግራጫዎች እየጠሩ መሄዳቸው ለሕዝባችንም ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል።

በትግል መስመራችን ውስጥ ወንድማማችነትን ለሕግ ትርጉም፣ ዳኝነትና ብይን የምናቀርበው አልነበረም፤ አይደለም፤ አይሆንምም። የወንድማማችነት መንፈስና እሴት ላይ ጥያቄ ያለው አካል በአንድ የፖለቲካ ትግል መስመር በተለይም ደግሞ በብሔርተኝነት የትግል መስመር ላይ ሊገኝ ግን አይችልም። በየሰልፋችን እንሁን። ይኸው ነው!
3.6K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 11:38:44
3.5K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 11:38:37 ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴን በጠዋት ሰባታሚት ተገኝተን ጎበኘነው። ከሁሉም አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች አርበኛውን ለመጠየቅ ወረፋ ተሰድረዋል። ፍተሻውን አልፈን ወደ ውስጥ ስንገባ አርበኛው ልክ እንደባለቅኔ ቀደምቶቹ ወንበር ዘርግቶ ጠያቂዎቹን ፈገግታ እየመገበ ወኔ ያስዘርፋል።

የአርበኝነት መዓዛውን ታጥነው የሚወጡ ውርዝው ሁሉ ፊታቸው ወዝቶ ሲወጡ ተመልክተናል። ስንገባ እንደሁልጊዜው በፈገግታ ተቀበለን። በርቱ ብሎን በርትተን ተመለስን። ከወጣን በኋላ አንድ ወቅት ለእንዲህ ዓይነት «ደግ ቀን» የከተብናትን አስታውሰን ፈገግ አልን። አብረን ፈገግ እንበል

የሚስቅ ሰው…
ብፁዕ ነው፣
እግዜር የቀደሰው፣
ጥርሱ ያከበረው፡፡
በድቅድቅ ጨለማ…
ሳቁን እየሞቀ፣
ብሶቱን ያመቀ፡፡
በመከራ መሀል…
በፈገግታ ምሽግ፣
ሀዘኑን ‘ሚሸሽግ፡፡
በፈተና ጊዜ…
በጥርሱ ብልጭታ፣
ክፉን ድል ሚመታ፡፡
የሚስቅ ሰው…
ፃድቅ ነው!

መልካም ቅዳሜ!
3.5K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ