Get Mystery Box with random crypto!

ታናናሽ ወንድሞቼና እህቶቼ፥ ለአገራችሁና ለሕዝባችሁ መልካም ነገርን የማድረግ በጎ ሕልም ካላችሁ፤ | Christian Tadele Tsegaye

ታናናሽ ወንድሞቼና እህቶቼ፥ ለአገራችሁና ለሕዝባችሁ መልካም ነገርን የማድረግ በጎ ሕልም ካላችሁ፤ ነፍስያችሁ ፍትኅን፣ ነፃነትንና እኩልነትን አብዝታ የምትጠማ እና ይህን መጠማታችሁን በትግል ማርካት አብዝታችሁ የምትሹ ከሆነ፥ እንግዲያውስ ወንድማችሁ ልምከራችሁ፤ ከጭቆና በፊት…ከጨቋኝ ኃይሎችም በፊት…በቅድሚያ ሆዳችሁን አሸንፉት። ሆድ መጥፎ ነው።

ታላቅ ያልናቸው በሆድ ፈተና ወድቀው አይተናል። የትግል ቃልኪዳናቸውን በሆዳቸው ቀይረውት፤ የትግል ጓዳቸውንም በከርሳቸው ተክተውት አይተናል። ወደው አይደለም፤ ሆዳቸው አሸንፏቸው… እንታገለዋለን ለሚሉት ወዶ ገብና ተመጽዋች ስላደረጋቸው ነው። እናም ታናናሾቼ…ከሁሉም በፊት ከሆዳችሁ ጋር ግጠሙ። ድሎትን ተጠየፉት። ብልጭልጩን አሸንፉት። ሆዳችሁን ለምንም ነገር እምቢ በሉት። ሰናይ ሰንበት!

ለሰው ልጅ ትልቁ ጠላቱ ሆዱ ነው!